Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 13:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ጊዜው ልክ ከፋሲካ በዓል በፊት ነበረ፤ ኢየሱስም ይህን ዓለም ትቶ ወደ አብ የሚሄድበት ጊዜ እንደ ደረሰ ዐወቀ። በዓለም የነበሩትን፣ የራሱ የሆኑትን ወደዳቸው፤ በፍጹም ፍቅሩም ወደዳቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን፥ የወደዳቸውን እስከ መጨረሻው ወደዳቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እነሆ፥ ጊዜው ከአይሁድ ፋሲካ በዓል በፊት ነበር፤ ኢየሱስ ይህን ዓለም ትቶ ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት መድረሱን ዐወቀ። በዚህ በዓለም ያሉትን የራሱን ወገኖች ወዶአቸው ነበር፤ እስከ መጨረሻም ወደዳቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከፋ​ሲካ በዓል አስ​ቀ​ድሞ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከዚህ ዓለም ወደ ላከው ወደ አብ ይሄድ ዘንድ ጊዜው እንደ ደረሰ ባወቀ ጊዜ በዓ​ለም ያሉ​ትን የወ​ደ​ዳ​ቸ​ውን ወገ​ኖ​ቹን ፈጽሞ ወደ​ዳ​ቸው።

参见章节 复制




ዮሐንስ 13:1
44 交叉引用  

እግዚአብሔርም ከሩቅ ተገለጠልኝ እንዲህም አለኝ፦ በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ፥ ስለዚህ በቸርነት ሳብሁሽ።


ከዚያ ወዲያ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጥቶ፦ እንግዲህስ ተኙ ዕረፉም፤ እነሆ፥ ሰዓቲቱ ቀርባለች የሰው ልጅም በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል።


በመቅደስ ዕለት ዕለት ከእናንተ ጋር ስሆን እጆቻችሁን አልዘረጋችሁብኝም፤ ይህ ግን ጊዜያችሁና የጨለማው ሥልጣን ነው አላቸው።


የሚወጣበትም ወራት በቀረበ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ፊቱን አቀና፥


የአይሁድም ፋሲካ ቀርቦ ነበር። ብዙ ሰዎችም ራሳቸውን ያነጹ ዘንድ ከፋሲካ በፊት ከአገሩ ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ።


ኢየሱስስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል፦ “የሰው ልጅ ይከብር ዘንድ ሰዓቱ ደርሶአል።


ይሁዳ ከረጢቱን የያዘ ስለ ሆነ፥ ኢየሱስ፦ ለበዓሉ የሚያስፈልገንን ግዛ፥ ወይም ለድሆች ምጽዋት እንዲሰጥ ያለው ለአንዳንዱ መስሎአቸው ነበርና።


ኢየሱስ አብ ሁሉን በልጁ እንደ ሰጠው ከእግዚአብሔር እንደ ወጣ ወደ እግዚአብሔርም እንዲሄድ አውቆ፥


እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ፥ እንደ ወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።


እኔ እሄዳለሁ ወደ እናንተም እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ። የምትወዱኝስ ብትሆኑ ከእኔ አብ ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር።


ነገር ግን አብን እንድወድ ዓለም ሊያውቅ፥ አብም እንዳዘዘኝ፥ እንዲሁ አደርጋለሁ። ተነሡ፤ ከዚህ እንሂድ።


ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ደግሞ ዓለምን እተወዋለሁ ወደ አብም እሄዳለሁ።”


ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ ዓኖቹን አነሣና እንዲህ አለ፦ “አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደርሶአል፤ ልጅህ ያከብርህ ዘንድ፥ በሥጋም ሁሉ ላይ ሥልጣን እንደ ሰጠኸው፥ ለሰጠኸው ሁሉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸው ዘንድ ልጅህን አክብረው።


እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉም።


እኔንም የወደድህበት ፍቅር በእነርሱ እንድትሆን እኔም በእነርሱ፥ ስምህም አስታወቅኋቸው አስታውቃቸውማለሁ።”


አሁንም፥ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።


ኢየሱስም የሚመጣበትን ሁሉ አውቆ ወጣና፦ “ማንን ትፈልጋላችሁ” አላቸው።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ፦ “ተጠማሁ” አለ።


የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።


የአይሁድ በዓልም ፋሲካ ቀርቦ ነበር።


ስለዚህ ሊይዙት ይፈልጉ ነበር፤ ነገር ግን ጊዜው ገና ስላልደረሰ ማንም እጁን አልጫነበትም።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ጊዜዬ ገና አልደረሰም፥ ጊዜያችሁ ግን ዘወትር የተመቸ ነው።


ኢየሱስ በመቅደስ ሲያስተም በግምጃ ቤት አጠገብ ይህን ነገር ተናገረ፤ ጊዜው ገና አልደረሰምና ማንም አልያዘውም።


በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።


እርሱም ደግሞ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድትሆኑ እስከ ፍጻሜ ድረስ ያጸናችኋል።


የመጀመሪያ እምነታችንን እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ፥ የክርስቶስ ተካፋዮች ሆነናልና፤


እኛም የምንደፍርበትን የምንመካበትን ተስፋ እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ ቤቱ ነን።


በእምነትና በትዕግሥትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ፥ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን።


ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ።


እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።


跟着我们:

广告


广告