Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 11:44 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ፤ ፈቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበር። ኢየሱስም፦ “ፍቱትና ይሂድ ተዉት” አላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 የሞተውም ሰው እጅና እግሩ በቀጭን ስስ ጨርቅ እንደ ተጠቀለለ፣ ፊቱም በሻሽ እንደ ተጠመጠመ ወጣ። ኢየሱስም “መግነዙን ፍቱለትና ይሂድ” አላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 ሞቶ የነበረውም ሰው እጆቹና እግሮቹ እንደ ተገነዙ ወጣ፤ ፈቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ። ኢየሱስም “ፍቱትና ይሂድ፤ ተዉት፤” አላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 ሟቹ አልዓዛርም እጆቹና እግሮቹ በመገነዣ እንደ ተገነዙ ከመቃብሩ ወጣ፤ ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበር፤ ኢየሱስም “ፍቱትና ተዉት ይሂድ!” አላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 ሞቶ የነ​በ​ረ​ውም እንደ ተገ​ነዘ፥ እጁ​ንና እግ​ሩ​ንም እንደ ታሰረ፥ ፊቱም በሰ​በን እንደ ተጠ​ቀ​ለለ ወጣ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እን​ግ​ዲ​ህስ ፍቱ​ትና ተዉት ይሂድ” አላ​ቸው።

参见章节 复制




ዮሐንስ 11:44
20 交叉引用  

እግዚአብሔርም፤ ብርሃን ይሁን ኣለ፤ ብርሃንም ሆነ።


ከሲኦል እጅ እታደጋቸዋለሁ፥ ከሞትም እቤዣቸዋለሁ፥ ሞት ሆይ፥ ቸነፈርህ ወዴት አለ? ሲኦል ሆይ፥ ማጥፋትህ ወዴት አለ? ርኅራኄ ከዓይኔ ተሰወረች።


ይህንም ማንም እንዳያውቅ አጥብቆ አዞአቸው፦ የምትበላውን ስጡአት አላቸው።


ሌላውም መጥቶ፦ ጌታ ሆይ፥ በጨርቅ ጠቅልዬ የጠበቅኋት ምናንህ እነሆ፤


የሞተውም ቀና ብሎ ተቀመጠ ሊናገርም ጀመረ፥ ለእናቱም ሰጣት።


እኔና አብ አንድ ነን።”


ኢየሱስ፦ “ድንጋዩን አንሡ” አለ። የሞተውም እኅት ማርታ፦ “ጌታ ሆይ፥ ከሞተ አራት ቀን ሆኖታልና አሁን ይሸታል” አለችው።


ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ፦ “አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና” ብሎ ጮኸ።


የኢየሱስንም ሥጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልምድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት።


ዝቅም ብሎ ቢመለከት የተልባ እግሩን ልብስ ተቀምጦ አየ፥ ነገር ግን አልገባ።


ደግሞም በራሱ የነበረውን ጨርቅ ለብቻው በአንድ ስፍራ ተጠምጥሞ እንደ ነበረ እንጂ ከተልባ እግሩ ልብስ ጋር ተቀምጦ እንዳልነበረ አየ።


አብ ሙታንን ይንደሚያነሣ ሕይወትም እንደሚሰጣቸው፥ እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣቸዋል።


እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሙታን የእግዚአብሔር ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።


እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር፥ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል።


ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።


እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም፥ ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል።


跟着我们:

广告


广告