Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዩኤል 3:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ይህን በአሕዛብ መካከል አውጁ፥ ለሰልፍ ተዘጋጁ፥ ኃያላንን አስነሡ፥ ሰልፈኞች ሁሉ ይቅረቡ ይውጡም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በሕዝቦች መካከል ይህን ዐውጁ፤ ለጦርነት ተዘጋጁ፤ ተዋጊዎችን አነሣሡ፤ ጦረኞችም ሁሉ ቀርበው ያጥቁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ይህን በአሕዛብ መካከል አውጁ፥ ለጦርነት ተዘጋጁ፥ ኃያላንን አስነሡ፥ ጦረኖች ሁሉ ይቅረቡ ይውጡም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “ይህን ለአሕዛብ ሁሉ ዐውጁ፤ ለጦርነት ተዘጋጁ፤ ጀግኖችን ቀስቅሱ፤ ጦረኞቻችሁ ሁሉ ተሰብስበው ለጦርነት ይሰለፉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 “ይህን በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ዐውጁ፤ ለሰ​ልፍ ተዘ​ጋጁ፤ ኀያ​ላ​ንን አስ​ነሡ፤ ሰል​ፈ​ኞች ሁሉ ይቅ​ረቡ፤ ይው​ጡም።

参见章节 复制




ኢዩኤል 3:9
16 交叉引用  

እናንተ አሕዛብ ሆይ፥ ቅረቡ፥ ስሙ፥ እናንተ ወገኖች ሆይ፥ አድምጡ፤ ምድርና ሙላዋ፥ ዓለምና ከእርስዋ የሚወጣ ሁሉ ይስሙ።


አሕዛብ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ በሩቅም ላሉ ደሴቶች አውሩና፦ እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስበዋል፥ እረኛም መንጋውን እንደሚጠብቅ ይጠብቀዋል በሉ።


በአሕዛብ መካከል ተናገሩ አውሩም፥ ዓላማውንም አንሡ፥ አውሩ፥ አትደብቁ፦ ባቢሎን ተወሰደች፥ ቤል አፈረ፥ ሜሮዳክ ደነገጠ፥ ምስሎችዋ አፈሩ፥ ጣዖታትዋ ደነገጡ በሉ።


ፍላጾችን ሳሉ ጋሻዎችንም አዘጋጁ፥ እግዚአብሔር ያጠፋት ዘንድ አሳቡ በባቢሎን ላይ ነውና የሜዶንን ነገሥታት መንፈስ አስነሥቶአል፥ የእግዚብሔር በቀል የመቅደሱ በቀል ነውና።


በምድር ላይ ዓላማን አንሡ በአሕዛብም መካከል መለከት ንፉ፥ አሕዛብንም አዘጋጁባት፥ የአራራትንና የሚኒን የአስከናዝንም መንግሥታት ሰብስቡባት አለቃንም በላይዋ አቁሙ፥ እንደ ጠጕራም ኩብኩባ ፈረሶችን በላይዋ አውጡ።


በእርስዋ ላይ ሰልፍ አዘጋጁ ተነሡ፥ በቀትርም እንውጣ። ቀኑ መሽቶአልና፥ የማታውም ጥላ ረዝሞአልና ወዮልን።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእነርሱ ላይ እንደማመጣህ በዚያች ዘመን ብዙ ዓመት ትንቢት በተናገሩ በባሪያዎቼ በእስራኤል ነቢያቶች በቀደመው ዘመን ስለ እርሱ የተናገርሁ አንተ ነህን?


አንተና ወደ አንተ የተሰበሰቡ ወገኖችህ ሁሉ ተዘጋጁ፥ አንተም ራስህን አዘጋጅተህ አለቃ ሁናቸው።


እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚያስቱ ነቢያት እንዲህ ይላል፥ በጥርሳቸው ሲነክሱ በሰላም ይሰብካሉ፥ በአፋቸው ግን አንዳች በማይሰጥ ሰው ላይ ሰልፍን ያስቡበታል።


አሕዛብን ሁሉ አናውጣለሁ፥ በአሕዛብ ሁሉ የተመረጠውም ዕቃ ይመጣል፥ ይህንም ቤት በክብር እሞላዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


አሕዛብንም ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ ለሰልፍ እሰበስባለሁ፥ ከተማይቱም ትያዛለች፥ ቤቶችም ይበዘበዛሉ፥ ሴቶችም ይነወራሉ፥ የከተማይቱም እኵሌታ ለምርኮ ይወጣል፥ የቀረው ሕዝብ ግን ከከተማ አይጠፋም።


እግዚአብሔርም ይወጣል፥ በሰልፍም ቀን እንደ ተዋጋ ከእነዚያ አሕዛብ ጋር ይዋጋል።


跟着我们:

广告


广告