Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዩኤል 3:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በሕዝቤም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፥ ወንድ ልጅን ለጋለሞታ ዋጋ ሰጡ፥ ሴት ልጅን ለወይን ጠጅ ሸጡ፥ ጠጡም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በሕዝቤ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፤ ወንዶች ልጆችን በዝሙት ዐዳሪዎች ለወጡ፤ ወይን ጠጅ ለመጠጣትም፣ ሴቶች ልጆችን ሸጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በሕዝቤም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፥ ወንድ ልጅን ለጋለሞታ ዋጋ ሰጡ፥ ሴት ልጅን ለወይን ጠጅ ሲሉ ሸጡ፥ ጠጡም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የማረኩአቸውን ሕዝቤንም ለመከፋፈል ዕጣ ተጣጥለዋል፤ አመንዝራ ሴቶችን ለማግኘት ወንዶች ልጆችን ሰጡ፤ ወይን ጠጅ ለመጠጣትም ሴቶች ልጆችን ባሪያ አድርገው ሸጡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በሕ​ዝ​ቤም ላይ ዕጣ ተጣ​ጣሉ፤ ወንድ ልጅን ለአ​መ​ን​ዝ​ሮች ዋጋ ሰጡ፤ ሴት ልጅ​ንም ለወ​ይን ጠጅ ሸጡ፤ ጠጡም።

参见章节 复制




ኢዩኤል 3:3
8 交叉引用  

በድሀ አደጉ ላይ ዕጣ ትጣጣላላችሁ፥ ለወዳጆቻችሁም ጕድጓድ ትቈፍራላችሁ።


ያዋንና ቶቤል ሞሳሕም ነጋዴዎችሽ ነበሩ፥ የሰዎችን ነፍሳትና የናሱን ዕቃ ስለ አንቺ ሸቀጥ ይነግዱ ነበር።


በተሃ ወይን ጠጃችሁ ከአፋችሁ ተወግዶአልና እናንተ ሰካራሞች፥ ነቅታችሁ አልቅሱ፥ እናንተም የወይን ጠጅ የምትጠጡ ሁሉ፥ ዋይ በሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጻድቁን ስለ ብር፥ ችጋረኛውንም ስለ አንድ ጥንድ ጫማ ሽጠውታልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የእስራኤል ኃጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።


በፊቱ አንጻር በቆምህ ቀን፥ አሕዛብ ጭፍራውን በማረኩበት፥ እንግዶችም በበሩ በገቡበት፥ በኢየሩሳሌምም ዕጣ በተጣጣሉበት ቀን አንተ ደግሞ ከእነርሱ እንደ አንዱ ነበርህ።


ቀረፋም ቅመምም የሚቃጠልም ሽቱ ቅባትም ዕጣንም የወይን ጠጅም ዘይትም የተሰለቀ ዱቄትም ስንዴም ከብትም በግም ፈረስም ሰረገላም ባሪያዎችም የሰዎችም ነፍሳት ነው።


跟着我们:

广告


广告