ኢዩኤል 2:23 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 እናንተ የጽዮን ልጆች፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር የፊተኛውን ዝናብ በጽድቅ ሰጥቶአችኋልና፥ እንደ ቀድሞውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ አዝንቦላችኋልና በእርሱ ደስ ይበላችሁ፥ ለእርሱም እልል በሉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም23 የጽዮን ሰዎች ሆይ፤ ደስ ይበላችሁ፤ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ሐሤት አድርጉ፤ የበልግን ዝናብ፣ በጽድቅ ሰጥቷችኋልና፤ እንደ ቀድሞውም፣ የበልግንና የጸደይን ዝናብ በብዛት ልኮላችኋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 እናንተ የጽዮን ልጆች፥ ጌታ አምላካችሁ ቀድሞ የሚደርሰውን ዝናብ ስለ ጽድቅ ሰጥቶአችኋልና፥ እንደ በፊትም ቀዳሚውንና የኋለኛውን ዝናብ አዝንቦላችኋልና በእርሱ ደስ ይበላችሁ፥ ለእርሱም እልል በሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 “እናንተ የጽዮን ሕዝብ ሆይ! በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤትም አድርጉ፤ እርሱ በትክክል ፈርዶ እንደ ወትሮው በበጋና በክረምት ወራት በቂ ዝናብ ሰጥቶአችኋል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 እናንተ የጽዮን ልጆች ሆይ! በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤትም አድርጉ፤ ምግብን በጽድቅ ሰጥቶአችኋልና፥ እንደ ቀድሞውም የበልጉንና የመከሩን ዝናብ ያዘንብላችኋልና። 参见章节 |