Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዩኤል 2:21 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ምድር ሆይ፥ እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አድርጎአልና አትፍሪ፥ ደስም ይበልሽ፥ እልልም በዪ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ምድር ሆይ፤ አትፍሪ፤ ደስ ይበልሽ፤ ሐሤትም አድርጊ፤ በርግጥ እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አድርጓል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ምድር ሆይ፥ ጌታ ታላቅ ነገር አድርጎአልና አትፍሪ፥ ደስም ይበልሽ፥ እልልም በዪ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “ምድር ሆይ አትፍሪ፤ እግዚአብሔር ስላደረገልሽ ታላቅ ነገር ደስ ይበልሽ! ሐሤትም አድርጊ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 “ምድር ሆይ! አት​ፍሪ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነገር አድ​ር​ጎ​አ​ልና ፈጽሞ ደስ ይበ​ልሽ፤ ሐሤ​ትም አድ​ርጊ።

参见章节 复制




ኢዩኤል 2:21
21 交叉引用  

ከዚህ ነገር በኍላም የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፥ እንዲህ ሲል፤ አብራም ሆይ፥ አትፍራ፤ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤ ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው።


ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ደስ ይላቸዋል፥ በረሃውም ሐሤት ያደርጋል እንደ ጽጌ ረዳም ያብባል።


እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፥ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፥ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።


ሰማያት ሆይ፥ እግዚአብሔር አድርጎታልና ዘምሩ፥ እግዚአብሔር ያዕቆብን ተቤዥቶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ ይከበራልና አንተ የምድር ጥልቅ ሆይ፥ ጩኽ፥ እናንተም ተራሮች አንተም ዱር በአንተም ያለ ዛፍ ሁሉ፥ እልል በሉ።


አታፍሪምና አትፍሪ፥ አትዋረጂምና አትደንግጪ፥ የሕፃንነትሽንም እፍረት ትረሺዋለሽ፥ የመበለትነትሽንም ስድብ ከእንግዲህ ወዲህ አታስቢም።


እናንተም በደስታ ትወጣላችሁ በሰላምም ትሸኛላችሁ፥ ተራሮችና ኮረብቶች በፊታችሁ እልልታ ያደርጋሉ፥ የሜዳም ዛፎች ሁሉ ያጨበጭባሉ።


ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመልስልሃለሁ፥ አንተም የማታውቀውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ።


ለዘላለምም ለእኔ እንድትሆኚ አጭሻለሁ፥ በጽድቅና በፍርድ በምሕረትና በርኅራኄ አጭሻለሁ።


የሰሜንንም ሠራዊት ከእናንተ ዘንድ አርቃለሁ፥ ወደ በረሃና ወደ ምድረ በዳ፥ ፊቱን ወደ ምሥራቁ ባሕር ጀርባውንም ወደ ምዕራቡ ባሕር አድርጌ አሳድደዋለሁ፥ እርሱም ትዕቢትን አድርጎአልና ግማቱ ይወጣል፥ ክርፋቱም ይነሣል አለ።


ብዙ መብል ትበላላችሁ፥ ትጠግቡማላችሁ፥ ከእናንተም ጋር ተአምራትን የሠራውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ስም ታመሰግናላችሁ፥ ሕዝቤም ለዘላለም አያፍርም።


እንዲሁ ዳግመኛ ለኢየሩሳሌምና ለይሁዳ ቤት በዚህ ወራት በጎነትን አደርግ ዘንድ አስቤአለሁ፥ አትፍሩ።


እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ከፈጠረው ጀምሮ፥ ከሰማይ ዳር እስከ ዳርቻዋ ድረስ ከቶ እንዲህ ያለ ታላቃ ነገር ወይም እንደ እርሱ ያለ ተሰምቶ እንደሆነ ከአንተ በፊት የነበረውን የቀደመውን ዘመን ጠይቅ።


አሁንም ቁሙ፥ እግዚአብሔርም በዓይናችሁ ፊት ወደሚያደርገው ወደዚህ ታላቅ ነገር ተመልከቱ።


ብቻ እግዚአብሔርን ፍሩ፥ ያደረገላችሁንም ታላቅ ነገር አይታችኋልና በፍጹም ልባችሁ በእውነት አምልኩት።


跟着我们:

广告


广告