Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዩኤል 2:20 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 የሰሜንንም ሠራዊት ከእናንተ ዘንድ አርቃለሁ፥ ወደ በረሃና ወደ ምድረ በዳ፥ ፊቱን ወደ ምሥራቁ ባሕር ጀርባውንም ወደ ምዕራቡ ባሕር አድርጌ አሳድደዋለሁ፥ እርሱም ትዕቢትን አድርጎአልና ግማቱ ይወጣል፥ ክርፋቱም ይነሣል አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 “የሰሜንን ሰራዊት ከእናንተ አርቃለሁ፤ ፊቱን ወደ ምሥራቁ ባሕር፣ ጀርባውንም ወደ ምዕራቡ ባሕር በማድረግ፣ ወደ ደረቀውና ወደ ባድማው ምድር እገፋዋለሁ፤ ግማቱ ይወጣል፤ ክርፋቱም ይነሣል።” በርግጥ እርሱ ታላቅ ነገር አድርጓል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 የሰሜንንም ሠራዊት ከእናንተ ዘንድ አርቃለሁ፥ ወደ በረሃና ወደ ምድረ በዳ፥ ፊቱን ወደ ምሥራቁ ባሕር ጀርባውንም ወደ ምዕራቡ ባሕር አድርጌ አሳድደዋለሁ፥ እርሱም ብዙ ነገር አድርጎአልና ግማቱ ይወጣል፥ ክርፋቱም ይነሣል አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ከሰሜን የሚመጣባችሁን የአንበጣ መንጋ ከእናንተ አርቅላችኋለሁ፤ ወደ በረሓና ወደ ምድረ በዳም አባርርላችኋለሁ፤ ግንባር ቀደም የሆኑትን ወደ ሙት ባሕር፥ በስተኋላ ያሉትን ወደ ሜዲቴራኒያን ባሕር እሰድላችኋለሁ፤ በዚያም በድናቸው ይከረፋል፤ በእርግጥ እኔ እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አድርጌላችኋለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 የሰ​ሜ​ን​ንም ሠራ​ዊት ከእ​ና​ንተ ዘንድ አር​ቃ​ለሁ፤ ወደ በረ​ሃና ወደ ምድረ በዳ እሰ​ደ​ዋ​ለሁ፤ ፊቱን ወደ መጀ​መ​ሪ​ያው ባሕር፥ ጀር​ባ​ው​ንም ወደ ኋለ​ኛው ባሕር አድ​ርጌ አሳ​ድ​ደ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ትዕ​ቢ​ትን አድ​ር​ጎ​አ​ልና ግማቱ ይወ​ጣል፤ ክር​ፋ​ቱም ይነ​ሣል።”

参见章节 复制




ኢዩኤል 2:20
15 交叉引用  

አዛሄልም “ይህን ታላቅ ነገር አደርግ ዘንድ እኔ ውሻ ባሪያህ ምንድር ነኝ?” አለ። ኤልሳዕም “አንተ በሶርያ ላይ ንጉሥ እንድትሆን እግዚአብሔር አሳይቶኛል፤” አለው።


እግዚአብሔርም ከምዕራብ ዐውሎ ነፋሱን አስወገደ፤ አንበጣዎቹንም ወስዶ በኤርትራ ባሕር ውስጥ ጣላቸው፤ አንድ አንበጣም በግብፅ ዳርቻ ሁሉ አልቀረም።


እንደ ክምርም አድርገው ሰበሰቡአቸው፤ ምድርም ገማች።


ከእነርሱም የተገደሉት ይጣላሉ። የሬሳቸውም ግማት ይሸታል፥ ተራሮችም ከደማቸው የተነሣ ይርሳሉ።


የምሥራቁም ድንበር በሐውራን በደማስቆና በገለዓድ በእስራኤልም ምድር መካከል ዮርዳኖስ ይሆናል። ከሰሜኑ ድንበር ጀምሮ እስከ ምሥራቁ ባሕር እስከ ታማር ድረስ የምሥራቁ ድንበር ይህ ነው።


በግብጽ እንደ ነበረው ቸነፈርን ሰደድሁባችሁ፥ ጐበዛዝቶቻችሁን በሰይፍ ገደልሁ፥ ፈረሶቻችሁንም አስማረክሁ፥ የሰፈራችሁንም ግማት ወደ አፍንጫችሁ አወጣሁ፥ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር።


በዚያም ቀን የሕይወት ውኃ ከኢየሩሳሌም ይወጣል፥ እኵሌታው ወደ ምሥራቁ ባሕር፥ እኵሌታውም ወደ ምዕራቡ ባሕር ይሄዳል፥ ይህ በበጋና በክረምት ይሆናል።


ስለ እናንተ ነቀዙን እገሥጻለሁ፥ የምድራችሁንም ፍሬ አያጠፋም፥ በእርሻችሁም ያለው ወይን ፍሬውን አያረግፍም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


የእግራችሁ ጫማ የምትረግጣት ስፍራ ሁሉ ለእናንተ ትሆናለች፤ ከምድረ በዳም ከሊባኖስም ከታላቁም ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ባሕር ድረስ ዳርቻችሁ ይሆናል።


跟着我们:

广告


广告