Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዩኤል 1:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የእህሉ ቍርባንና የመጠጡ ቍርባን ከእግዚአብሔር ቤት ተወግዶአል፥ የእግዚአብሔርም አገልጋዮች ካህናቱ አለቀሱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የእህል ቍርባንና የመጠጥ ቍርባን፣ ከእግዚአብሔር ቤት ተቋርጧል፤ በእግዚአብሔርም ፊት የሚያገለግሉ፣ ካህናት ያለቅሳሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የእህሉ ቁርባንና የመጠጡ ቁርባን ከጌታ ቤት ተወግዶአል፥ የጌታ አገልጋዮች ካህናቱ አለቀሱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በእግዚአብሔር ቤት መባ ሆኖ የሚቀርብ እህልም ሆነ የወይን ጠጅ በመታጣቱ፥ የእግዚአብሔር አገልጋዮች የሆኑት ካህናት ያለቅሳሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 መሥ​ዋ​ዕ​ቱና የመ​ጠጡ ቍር​ባን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ተወ​ግ​ዶ​አል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሠ​ውያ የም​ታ​ገ​ለ​ግሉ ካህ​ናቱ፥ አል​ቅሱ።

参见章节 复制




ኢዩኤል 1:9
10 交叉引用  

ለእኛ ግን አምላካችን እግዚአብሔር ነው፤ አልተውነውም፤ የእግዚአብሔርም አገልጋዮች የአሮን ልጆች ካህናቱ፥ ሌዋውያኑም በሥራቸው ከእኛ ጋር ናቸው።


አንተም ወንድምህን አሮንን ከእርሱም ጋር ልጆቹን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይተህ ካህናት ይሆኑልኝ ዘንድ ወደ አንተ አቅርብ፤ አሮንን የአሮንንም ልጆች፥ ናዳብን አብዩድንም አልዓዛርንም ኢታምርንም፥ አቅርብ።


እናንተ ግን የእግዚአብሔር ካህናት ትባላላችሁ፥ ሰዎቹም የአምላካችን አገልጋዮች ብለው ይጠሩአችኋል፥ የአሕዛብን ሀብት ትበላላችሁ፥ በክብራቸውም ትመካላችሁ።


ዔ። የሚያጽናናኝ ነፍሴንም የሚያበረታት ከእኔ ርቆአልና ስለዚህ አለቅሳለሁ፥ ዓይኔ፥ ዓይኔ ውኃ ያፈስሳል። ጠላት በርትቶአልና ልጆቼ ጠፍተዋል።


ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓልም የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች አለቀሱ፥ በሮችዋ ሁሉ ፈርሰዋል ካህናቶችዋም እየጮኹ ያለቅሳሉ፥ ደናግሎችዋም ተጨነቁ እርስዋም በምሬት አለች።


ለእግዚአብሔርም የወይን ጠጅን ቍርባን አያፈስሱም፥ መሥዋዕታቸውም ደስ አያሰኘውም፥ የኀዘንም እንጀራ ይሆንላቸዋል፥ የሚበላውም ሁሉ ይረክሳል፥ እንጀራቸውም ለሰውነታቸው ይሆናል እንጂ ወደ እግዚአብሔር ቤት አይገባም።


የእህሉ ቍርባንና የመጠጡ ቍርባን ከአምላካችሁ ቤት ቀርቶአልና እናንተ ካህናት፥ ማቅ ታጥቃችሁ አልቅሱ፥ እናንተም የመሠዊያ አገልጋዬች፥ ዋይ በሉ፥ እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች፥ ኑ፥ ሌሊቱን ሁሉ በማቅ ላይ ተኙ።


ከዓይናችን ፊት ምግብ፥ ከአምላካችንም ቤት ደስታና እልልታ የጠፋ አይደለምን?


የሚመለስና የሚጸጸት እንደ ሆነ፥ ለአምላካችሁም ለእግዚአብሔር የእህልና የመጠጥ ቍርባን የሚሆነውን በረከት የሚያተርፍ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?


የእግዚአብሔርም አገልጋዬች ካህናት ከወለሉና ከመሠዊያው መካከል እያለቀሱ፦ አቤቱ፥ ለሕዝብህ ራራ፥ አሕዛብም እንዳይነቅፉአቸው ርስትህን ለማላገጫ አሳልፈህ አትስጥ፥ ከአሕዛብ መካከል፦ አምላካቸው ወዴት ነው? ስለ ምን ይላሉ? ይበሉ።


跟着我们:

广告


广告