Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዩኤል 1:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከተምች የቀረውን አንበጣ በላው፥ ከአንበጣም የቀረውን ደጎብያ በላው፥ ከደጎብያም የቀረውን ኩብኩባ በላው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከአንበጣ መንጋ የተረፈውን፣ ትልልቁ አንበጣ በላው፤ ከትልልቁ አንበጣ የተረፈውን፣ ኵብኵባ በላው፤ ከኵብኵባ የተረፈውን፣ ሌሎች አንበጦች በሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከተምች የቀረውን አንበጣ በላው፥ ከአንበጣም የቀረውን ደጎብያ በላው፥ ከደጎብያም የቀረውን ኩብኩባ በላው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከተምች መንጋ የተረፈውን ሰብል፥ የሚርመሰመስ የአንበጣ መንጋ በላው፤ ከዚያ የተረፈውን እንደ ውሽንፍር የሚገርፍ የአንበጣ መንጋ አጠፋው፤ ከዚያም የተረፈውን ኲብኲባ በላው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከተ​ምች የቀ​ረ​ውን አን​በጣ በላው፤ ከአ​ን​በ​ጣም የቀ​ረ​ውን ደጎ​ብያ በላው፤ ከደ​ጎ​ብ​ያም የቀ​ረ​ውን ኩብ​ኩባ በላው።

参见章节 复制




ኢዩኤል 1:4
19 交叉引用  

“በምድር ላይ ራብ፥ ወይም ቸነፈር፥ ወይም ዋግ፥ ወይም አረማሞ፥ ወይም አንበጣ፥ ወይም ኩብኩባ ቢሆን፥ የሕዝብህም ጠላት የአገሩን ቀበሌዎች ከብቦ ቢያስጨንቃቸው፥ መቅሠፍትና ደዌ ሁሉ ቢሆን፥


“በምድር ላይ ራብ ወይም ቸነፈር ወይም ዋግ ወይም አረማሞ ወይም አንበጣ ወይም ኩብኩባ ቢሆን፥ ጠላቶቻቸውም የአገሩን ከተሞች ከብበው ቢያስጨንቁአቸው፥ ማናቸውም መቅሠፍትና ደዌ ቢሆን፥


ዝናብ እንዳይወርድ ሰማያቱን ብዘጋ፥ ወይም ምድሪቱን ይበላ ዘንድ አንበጣን ባዝዘው፥ ወይም በሕዝብ ላይ ቸነፈር ብሰድድ፥


ሕዝቤን ለመልቀቅ እንቢ ብትል ግን፥ እነሆ ነገ በአገርህ አንበጣዎችን አመጣለሁ፤


የምድሩንም ፊት ይሸፍኑታልና ምድሩን ለማየት አይቻልም፤ ከበረዶውም አምልጦ የተረፈላችሁን ትርፍ ይበሉታል፤ ያደገላችሁንም የእርሻውን ዛፍ ሁሉ ይበሉታል፤


አንበጣ እንደሚሰበሰብ ምርኮአችሁ ትሰበሰባለች፥ ኩብኩባም እንደሚዘልል ሰዎች ይዘልሉበታል።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል በራሱ ምሎአል፦ በእውነት ሰዎችን እንደ አንበጣ እሞላብሻለሁ፥ እነርሱም ጩኸት ያነሡብሻል።


በምድር ላይ ዓላማን አንሡ በአሕዛብም መካከል መለከት ንፉ፥ አሕዛብንም አዘጋጁባት፥ የአራራትንና የሚኒን የአስከናዝንም መንግሥታት ሰብስቡባት አለቃንም በላይዋ አቁሙ፥ እንደ ጠጕራም ኩብኩባ ፈረሶችን በላይዋ አውጡ።


የሰደድሁባችሁ ታላቁ ሠራዊቴ አንበጣና ደጎብያ ኩብኩባና ተምች የበላቸውን ዓመታት እመልስላችኋለሁ።


በዋግና በአረማሞ መታኋችሁ፥ የአታክልቶቻችሁንም ብዛት ወይኖቻችሁንም በለሶቻችሁንም ወይራዎቻችሁንም ተምች በልቶአል፥ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፥ እነሆም፥ የኋለኛው ሣር በሚበቅልበት መጀመሪያ ላይ አንበጣን ፈጠረ፥ እነሆም፥ ከንጉሡ አጨዳ በኋላ የበቀለ የገቦ ነበረ።


ስለ እናንተ ነቀዙን እገሥጻለሁ፥ የምድራችሁንም ፍሬ አያጠፋም፥ በእርሻችሁም ያለው ወይን ፍሬውን አያረግፍም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


እጅግ ዘር ወደ እርሻ ታወጣለህ፤ አንበጣም ይበላዋልና ጥቂት ትሰበስባለህ።


ዛፍህን ሁሉ የምድርህንም ፍሬ ኩብኩባ ይወርሰዋል።


跟着我们:

广告


广告