Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዩኤል 1:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እህሉ ጠፍቶአልና፥ ወይኑም ደርቆአልና፥ ዘይቱም ጐድሎአልና እርሻው ምድረ በዳ ሆኖአል፥ ምድሪቱም አልቅሳለች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ዕርሻዎች ባዷቸውን ቀርተዋል፤ ምድሩም ደርቋል፤ እህሉ ጠፍቷል፤ አዲሱ የወይን ጠጅ ዐልቋል፤ ዘይቱም ተሟጧል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እህሉ ጠፍቶአልና፥ ወይኑም ደርቆአልና፥ ዘይቱም ጐድሎአልና እርሻው ምድረ በዳ ሆኖአል፥ ምድሪቱም አልቅሳለች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እርሻዎች ባዶአቸውን ቀርተዋል፤ እህል ጠፍቶአል፤ የወይን ተክሎች ደርቀዋል፤ ዘይትም ጠፍቶአል፤ ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እር​ሻው ምድረ በዳ ሆኖ​አል፤ ምድ​ሪ​ቱም ታል​ቅስ፤ እህሉ ጠፍ​ቶ​አ​ልና፥ ወይ​ኑም ደር​ቆ​አ​ልና፥ ዘይ​ቱም ጐድ​ሎ​አ​ልና።

参见章节 复制




ኢዩኤል 1:10
19 交叉引用  

ምድርንም ባረስህ ጊዜ እንግዲህ ኂይልዋን አትሰጥህም፤ በምድርም ላይ ኮብላይና ተቅበዝባዥ ትሆናለህ።


የኔምሬም ውኆች ይደርቃሉ፥ ሣሩም ደርቋል፥ ለጋውም ጠውልጓል፥ ልምላሜውም ሁሉ የለም።


ስለ ወይኑም ጠጅ በአደባባይ ጩኸት ይሆናል፥ ደስታ ሁሉ ጨልሞአል፥ የምድርም ሐሤት ፈርሶአል።


የወይን ጠጅ አለቀሰች፥ የወይን ግንድ ደከመች፥ ልባቸው ደስ ያለው ሁሉ ተከዙ።


ባድማ አድርገውታል፥ ፈርሶም ወደ እኔ ያለቅሳል፥ ምድር ሁሉ ባድማ ሆናለች በልቡም የሚያስባት የለም።


ምድሪቱ የምታለቅሰው፥ የአገሩ ሣርስ ሁሉ የሚደርቀው እስከ መቸ ነው? የተቀመጡባት ሰዎች፦ ፍጻሜያችንን አያይም ብለዋልና ስለ ክፋታቸው እንስሶችና ወፎች ጠፍተዋል።


ሐሤትና ደስታ ከፍሬያማው እርሻና ከሞዓብ ምድር ጠፍተዋል፥ ጠጁን ከመጥመቂያው አጥፍቻለሁ፥ ጠማቂውም በእልልታ አይጠምቅም፥ እልልታቸውም እልልታ አይሆንም።


ስለዚህ ምድሪቱ ታለቅሳለች፥ በእርስዋም የሚቀመጡ ሁሉ ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች ጋር ይደክማሉ፥ የባሕሩም ዓሦች ያልቃሉ።


አውድማውና መጥመቂያው አይመግባቸውም፥ ጉሽ ጠጅም ይጐድልባታል።


ወይኑ ደርቆአል፥ በለሱም ጠውልጎአል፥ ሮማኑና ተምሩ እንኰዩም የምድርም ዛፎች ሁሉ ደርቀዋል፥ ደስታም ከሰው ልጆች ዘንድ ርቆአል።


በተሃ ወይን ጠጃችሁ ከአፋችሁ ተወግዶአልና እናንተ ሰካራሞች፥ ነቅታችሁ አልቅሱ፥ እናንተም የወይን ጠጅ የምትጠጡ ሁሉ፥ ዋይ በሉ።


እግዚአብሔርም መልሶ ሕዝቡን፦ እነሆ፥ እህልንና ወይንን ዘይትንም እሰድድላችኋለሁ፥ እናንተም በእርሱ ትጠግባላችሁ፥ ከእንግዲህም ወዲያ በአሕዛብ መካከል መሰደቢያ አላደርጋችሁም።


ጕልበታችሁም በከንቱ ያልቃል፤ ምድራችሁም እህልዋን አትሰጥም፥ የምድርም ዛፎች ፍሬአቸውን አይሰጡም።


ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥


እኔም በምድርና በተራሮች፥ በእህልና በወይንም፥ በዘይትና ምድርም በምታበቅለው ላይ፥ በሰዎችና በእንስሶችም ላይ፥ እጅም በሚደክምበት ሁሉ ላይ ድርቅን ጠርቻለሁ።


እነሆ፥ ክንዳችሁን እገሥጻለሁ፥ የመሥዋዕታችሁንም ፋንድያ በፊታችሁ ላይ እበትናለሁ፥ ከእርሱም ጋር በአንድነት ትወሰዳላችሁ።


跟着我们:

广告


广告