Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 9:21 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ሕፃናቱን ከመንገድ ጕልማሶቹንም ከአደባባይ ያጠፉ ዘንድ ሞት ወደ መስኮታችን ደርሶአል ወደ አዳራሻችንም ውስጥ ገብቶአል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ሞት በመስኮቶቻችን ገብቷል፤ ወደ ምሽጎቻችንም ዘልቋል፤ ሕፃናትን ከየመንገዱ፣ ወጣቶችን ከየአደባባዩ ጠራርጎ ወስዷል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ሕፃናቱን ከመንገድ ጉልማሶቹንም ከአደባባይ ለማጥፋት ሞት ወደ መስኮታችን ደርሶአል ወደ ንጉሥ ቅጥሮቻችን ውስጥ ገብቶአል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ሞት በየመስኮቶቻችን ገብቶአል፤ በየቤተ መንግሥታችንም ውስጥ ገብቷል፤ ልጆችን በየመንገዱ፥ ጐልማሶችንም በየአደባባዩ ቀሥፎአል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ሕፃ​ና​ቱ​ንም በመ​ን​ገድ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቹ​ንም በአ​ደ​ባ​ባ​ዮ​ቻ​ችን ያጠፋ ዘንድ ሞት በመ​ስ​ኮ​ቶ​ቻ​ችን ወደ ሀገ​ራ​ችን ገብ​ቶ​አ​ልና።

参见章节 复制




ኤርምያስ 9:21
17 交叉引用  

ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጕልማሶቻቸውን በቤተመቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ ጕልማሳውንና ቈንጆይቱን ሽማግሌውንና አሮጌውን አልማረም፤ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።


ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፥


በአገርም ደጆች ውስጥ በመንሽ አበጥሬአቸዋለሁ፥ የወላድ መካን አድርጌአቸዋለሁ፥ ሕዝቤንም አጥፍቼአለሁ፥ ከመንገዳቸውም አልተመለሱም።


ስለዚህ ልጆቻቸውን ለራብ ስጥ፥ ለሰይፍም እጅ አሳልፈህ ስጣቸው፥ ሚስቶቻቸውም የወላድ መካንና መበለቶች ይሁኑ፥ ወንዶቻቸውም በሞት ይጥፉ፥ ጕልማሶቻቸውም በሰልፍ ጊዜ በሰይፍ ይመቱ።


አሁንም የእስራኤል አምላክ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከይሁዳ ወገን ቅሬታ እንዳይቀርላችሁ፥ ወንድንና ሴትን፥ ብላቴናንና ሕፃንን ከመካከላችሁ ታጠፉ ዘንድ ይህን ታላቅ ክፋት በራሳችሁ ላይ ለምን ታደርጋላችሁ?


ስለዚህ ጐበዛዝትዋ በአደባባይዋ ላይ ይወድቃሉ፥ በዚያም ቀን ሰልፈኞችዋ ሁሉ ይጠፋሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።


ስለዚህ በእግዚአብሔር ቍጣ ተሞልቻለሁ፥ ከመታገሥ ደክሜአለሁ፥ በሜዳ በሕፃናት ላይ በጕልማሶችም ጉባዔ ላይ በአንድነት አፍስሰው፥ ባል ከሚስቱ ጋር ሽማግሌውም ከጎበዙ ጋር ይያያዛልና።


ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ከዚህ ሕዝብ ፊት ዕንቅፋቶችን አደርጋለሁ፥ አባቶችና ልጆች በአንድነት ይሰናከሉባቸዋል፥ ጎረቤትና ባልንጀራም ይጠፋሉ።


የዚህም ሕዝብ ሬሳ ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል፥ የሚያስፈራራቸውም የለም።


በወደዱአቸውና ባመለኩአቸው፥ በተከተሉአቸውና በፈለጉአቸው፥ በሰገዱላቸውም በፀሐይና በጨረቃ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጉአቸዋል፥ አያከማቹአቸውም አይቀብሩአቸውምም፥ በምድርም ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ።


በከተማም ያኰበኵባሉ፥ በቅጥሩም ላይ ይሮጣሉ፥ ወደ ቤቶችም ይወጣሉ፥ እንደ ሌባም በመስኮቶች ይገባሉ።


የእስራኤል ድንግል ወደቀች፥ ከእንግዲህም ወዲህ አትነሣም፥ በምድርዋ ላይ ተጣለች፥ የሚያስነሣትም የለም።


እንዲህም ይሆናል፥ አሥር ሰዎች በአንድ ቤት ውስጥ ቢቀሩ እነርሱ ይሞታሉ።


በእግዚአብሔርም ላይ ኃጢአት ሠርተዋልና እንደ ዕውር እስኪሄዱ ድረስ ሰዎችን አስጨንቃለሁ፥ ደማቸውም እንደ ትቢያ፥ ሥጋቸውም እንደ ጕድፍ ይፈስሳል።


跟着我们:

广告


广告