Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 8:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እንግዲህ ይህ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ዘወትር ስለ ምን ወደ ኋላው ይመለሳል? ተንኰልን ይዞአል ሊመለስም እንቢ ብሎአል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ታዲያ፣ ይህ ሕዝብ ለምን ፊቱን አዙሮ ወደ ኋላ ይሄዳል? ለምንስ ኢየሩሳሌም ዘወትር ወደ ኋላ ትመለሳለች? ተንኰልን የሙጥኝ ብለው ይዘዋል፤ ሊመለሱም ፈቃደኛ አይደሉም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እንግዲህ ይህ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ዘወትር ስለምን ወደ ኋላው ይመለሳል? ተንኰልን አጥብቀው ይዘዋል፥ ለመመለስም እንቢ ብለዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ታዲያ ሕዝቤ ወደ እኔ በመመለስ ፈንታ እንደ ራቃችሁ የምትቀሩት ስለምንድነው? ወደ እኔ መመለስን እምቢ ብላችሁ ወደ ጣዖት አዘነበላችሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሕዝቤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስለ ምን ወደ ኋላ​ቸው ተመ​ለሱ? ዐመ​ፅን ዐም​ፀ​ዋል፥ መመ​ለ​ስ​ንም እንቢ ብለ​ዋል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 8:5
26 交叉引用  

እምቢ ብትሉ ግን ብታምፁም፥ ሰይፍ ይበላችኋል፥ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።


ባለ ራእዮችን፦ አትመልከቱ ይላሉ፥ ነቢያትንም፦ ጣፋጩንና አታላዩን ነገር እንጂ ቅኑን ነገር አትንገሩን፥


አመድ ይበላል፥ የተታለለ ልብ አስቶታል፥ ነፍሱን ለማዳን አይችልም፥ ወይም፦ በቀኝ እጄ ሐሰት አለ አይልም።


አቤቱ፥ ኃጢአታችን ብዙ ነውና፥ በአንተም ላይ ኃጢአት ሠርተናልና ኃጢአታችን ይመሰክርብናል ነገር ግን ስለ ስምህ ብለህ አድርግ።


በውኑ ቆንጆ ጌጥዋን ወይስ ሙሽራ ዝርግፍ ጌጥዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን የማይቈጠር ወራት ረስቶኛል።


እስከ ፍጻሜስ ድረስ ይጠብቀዋልን? እነሆ፥ እንዲህ ብለሽ ተናገርሽ፥ እንደ ተቻለሽም መጠን ክፉን ነገር አደረግሽ።


ቀፎ ወፎችን እንደሚሞላ፥ እንዲሁ ቤታቸው ሽንገላን ሞልታለች፥ እንዲሁም ከብረዋል ባለ ጠጎችም ሆነዋል።


አቤቱ፥ ዓይንህ እውነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል ነገር ግን አላዘኑም፥ ቀጥቅጠሃቸውማል ነገር ግን ተግሣጽን እንቢ አሉ፥ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፥ ይመለሱ ዘንድ እንቢ አሉ።


ስለዚህ ኃጢአታቸው በዝቶአልና፥ የክዳታቸውም ብዛት ጸንቶአልና ስለዚህ አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰብራቸዋል፥ የበረሀም ተኵላ ያጠፋቸዋል፥ ነብርም በከተሞቻቸው ላይ ይተጋል፥ ከዚያም የሚወጣ ሁሉ ይነጠቃል።


እኔም፦ የመለከቱን ድምፅ አድምጡ ብዬ ጠባቆችን ሾምሁባችሁ፥ እነርሱ ግን፦ አናደምጥም አሉ።


ምድር ሆይ፥ ስሚ፥ እነሆ፥ ቃሌን ስላልሰሙ ሕጌንም ስለ ጣሉ፥ በዚህ ሕዝብ ላይ የአሳባቸውን ፍሬ፥ ክፉን ነገር አመጣባቸዋለሁ።


ማደሪያህ በሽንገላ መካከል ነው፥ ከሽንገላም የተነሣ እኔን ያውቁኝ ዘንድ እንቢ ብለዋል፥ ይላል እግዚአብሔር።


እስራኤልም ሁሉ ሕግህን ተላልፈዋል፥ ቃልህንም እንዳይሰሙ ፈቀቅ ብለዋል፥ በእርሱ ላይ ኃጢአት ሠርተናልና በእግዚአብሔር ባሪያ በሙሴ ሕግ የተጻፈው መሐላና እርግማን ፈሰሰብን።


ወደ እኔ ይመለሱ ዘንድ አልወደዱምና ወደ ግብጽ ምድር ይመለሳሉ፥ አሦርም ንጉሣቸው ይሆናል።


ሕዝቤም ከእኔ ይመለሱ ዘንድ ወደዱ፥ ወደ ላይም ቢጠሩአቸው ማንም ከፍ ከፍ ያደርጋቸው ዘንድ አይችልም።


አሁንም ኃጢአትን ይሠሩ ዘንድ ጨመሩ፥ በብራቸውም ለራሳቸው ቀልጦ የተሠራ ምስልን፥ እንደ ጥበባቸውም ጣዖታትን ሠርተዋል፥ ሁሉም የሠራተኛ ሥራ ናቸው። ስለ እነርሱም፦ የሚሠው ሰዎች እምቦሳውን ይሳሙ ይላሉ።


እስራኤል እንደ እልከኛ ጊደር እንቢ ብሎአል፥ እግዚአብሔርስ በሰፊው ቦታ እንደ ጠቦት ያሰማራዋልን?


እነርሱ ግን ደንደሳቸውን አዞሩ እንጂ መስማትን እምቢ አሉ፥ እንዳይሰሙም ጆሮአቸውን አደነቈሩ።


ነገር ግን ሕይወት እንዲሆንላችሁ ወደ እኔ ልትመጡ አትወዱም።


ለሚናገረው እምቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ በምድር ላስረዳቸው እምቢ ባሉ ጊዜ ካላመለጡ፥ ከሰማይ ከመጣው ፈቀቅ የምንል እኛስ እንዴት እናመልጣለን?


ነገር ግን እስክመጣ ድረስ ያላችሁን ጠብቁ።


跟着我们:

广告


广告