Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 8:22 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 በገለዓድ የሚቀባ መድኃኒት የለምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለምን? የወገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለ ምን አልሆነም?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 በገለዓድ የሚቀባ መድኀኒት የለምን? ወይስ በዚያ ሐኪም አልነበረምን? ለሕዝቤ ቍስል፣ ለምን ፈውስ አልተገኘም?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 በገለዓድ የሚቀባ መድኃኒት የለምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለምን? የወገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለምን አልሆነም?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 በገለዓድ የቅባት መድኃኒት የለምን? ሐኪሞችስ በዚያ አይገኙምን? ታዲያ ሕዝቤ የማይፈወሱት ስለምንድን ነው?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 በገ​ለ​ዓድ መድ​ኀ​ኒት የለ​ምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለ​ምን? የወ​ገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለ ምን አል​ሆ​ነም?

参见章节 复制




ኤርምያስ 8:22
17 交叉引用  

እንጀራም ሊበሉ ተቀመጡ ዓይናቸውንም አንሥተው አዩ፥ እነሆም የእስማኤላውያን ነገዶች ወደ ግብፅ ለመውረድ ከገለዓድ መጡ ግመሎቻቸውም ሽቱና በለሳን ከርቤም ተጭነው ነበር።


እስራኤልም አባታቸው እንዲህ አላቸው፦ ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህንን አድርጉ ከተመሰገነው ከምድሩ ፍሬ በዓይበታችሁ ይዛችሁ ሂዱ ለዚያም ሰው እጅ መንሻ ጥቂት በለሳን ጥቂት ማር ሽቱ፥ ከርቤ፥ ተምር፥ ለውዝ ውሰዱ።


በውኑ ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ነፍስህስ ጽዮንን ጠልታታለችን? ስለ ምን መታኸን? ፈውስስ ስለ ምን የለንም? ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፥ መልካምም አልተገኘም፥ ፈውስን በተስፋ ተጠባበቅን፥ እነሆም፥ ድንጋጤ ሆነ።


እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ቤት እንዲህ ይላልና፦ አንተ በእኔ ዘንድ እንደ ገለዓድና እንደ ሊባኖስ ራስ ነህ፥ ነገር ግን በእርግጥ ምድረ በዳ ማንም የማይቀመጥባቸውም ከተሞች አደርግሃለሁ።


ድንግሊቱ የግብጽ ልጅ ሆይ፥ ወደ ገለዓድ ውጪ የሚቀባንም መድኃኒት ውሰጂ፥ መድኃኒትን ያበዛሽው በከንቱ ነው፥ መዳን የለሽም።


ባቢሎን በድንገት ወድቃ ጠፍታለች፥ አልቅሱላት፥ ትፈወስም እንደ ሆነ ለቍስልዋ መድኃኒት ውሰዱላት።


በጕድጓድ ውኃ እንደሚፈልቅ፥ እንዲሁ ክፋትዋ ከእርስዋ ዘንድ ይፈልቃል፥ ግፍና ቅሚያ በእርስዋ ዘንድ ይሰማል፥ ደዌና ቍስልም ሁልጊዜ በፊቴ አለ።


ተወግተው ስለ ሞቱ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን አለቅስ ዘንድ ራሴ ውኃ፥ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ!


ኢየሩሳሌምንም የፍርስራሽ ክምር የቀበሮም ማደሪያ አደርጋታለሁ፥ የይሁዳንም ከተሞች ሰው የማይቀመጥባት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።


ሜም። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ? በምንስ እመስልሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ አጽናናሽ ዘንድ በምን አስተካክልሻለሁ? ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፥ የሚፈውስሽ ማን ነው?


ይሁዳና የእስራኤል ምድር ነጋዴዎችሽ ነበሩ፥ የሚኒትን ስንዴ ጣፋጭም እንጕቻ፥ ማር ዘይትም በለሳንም ስለ አንቺ ሸቀጥ ይነግዱ ነበር።


የሮቤልና የጋድ ልጆችም እጅግ ብዙ እንስሶች ነበሩአቸው፤ እነሆም፥ የኢያዜር ምድርና የገለዓድ ምድር ለእንስሶች የተመቸ ስፍራ እንደ ነበረ ባዩ ጊዜ፥


ከአሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፥ ትዳርዋንም ሁሉ ለባለመድኃኒቶች ከስራ ማንም ሊፈውሳት አልተቻለውም።


跟着我们:

广告


广告