Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 8:21 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በሕዝቤ ሴት ልጅ ስብራት እኔ ተሰብሬአለሁ ጠቍሬማለሁ፥ አድናቆትም ይዞኛል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ሕዝቤ ሲቈስል፣ እኔም ቈሰልሁ፤ አለቀስሁ፤ ድንጋጤ ያዘኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በሕዝቤ ሴት ልጅ ስብራት እኔ ተሰብሬአለሁ ጠቁሬአለሁም፤ ፍርሀትም ይዞኛል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ሕዝቤ በመሰበሩ የእኔም ልብ ተሰብሮአል፤ ፍርሀትም ይዞኝ አለቅሳለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በሕ​ዝቤ ሴት ልጅ ስብ​ራት እኔ ወድቄ ተሰ​ብ​ሬ​አ​ለሁ፤ ጠቍ​ሬ​ማ​ለሁ፤ ራስ ማዞ​ርም ይዞ​ኛል፤ ምጥ እን​ደ​ያ​ዛ​ትም ሴት በመ​ከ​ራው እጨ​ነ​ቃ​ለሁ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 8:21
14 交叉引用  

ንጉሡንም፦ “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ! የአባቶቼ መቃብር ያለባት ከተማ ተፈትታለችና፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋልና ፊቴ ስለ ምን አይዘን?” አልሁት።


እንደዚህም ብለህ ትነግራቸዋለህ፦ የወገኔ ልጅ ድንግሊቱ በታላቅ ስብራትና እጅግ ክፉ በሆነ ቍስል ተሰብራለችና ዓይኖቼ ሌሊትና ቀን ሳያቋርጡ እንባ ያፍስሱ።


ይሁዳ አለቀሰች፥ ደጆችዋም ባዶ ሆኑ በምድርም ላይ ጨለሙ፥ የኢየሩሳሌም ጩኸት ከፍ ከፍ ብሎአል።


እኔም አንተን ተከትዬ እረኛ ከመሆን አልቸኰልሁም፥ የመከራንም ቀን አልወደድሁም፥ አንተ ታውቃለህ፥ ከከንፈሬ የወጣው በፊትህ ነበረ።


አንጀቴ! አንጀቴ! ልቤ በጣም ታምሞአል፥ በውስጤም ልቤ ታውኮብኛል፥ ነፍሴ ሆይ፥ የመለከትን ድምፅና የሰልፍን ውካታ ሰምተሻልና ዝም እል ዘንድ አልችልም።


መከሩ አልፎአል፥ በጋው ሄዶአል፥ እኛም አልዳንነም።


ተወግተው ስለ ሞቱ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን አለቅስ ዘንድ ራሴ ውኃ፥ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ!


አሌፍ። በቍጣው በትር መከራ ያየ ሰው እኔ ነኝ።


ከፊታቸው አሕዛብ ይንቀጠቀጣሉ፥ የሰውም ፊት ሁሉ ይጠቍራል።


ሲቀርብም ከተማይቱን አይቶ አለቀሰላት፥


跟着我们:

广告


广告