Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 8:15 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፥ መልካምም አልተገኘም፥ መጠገንን በተስፋ ተጠባበቅን፥ እነሆም፥ ድንጋጤ ሆነ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሰላምን ተስፋ አደረግን፤ መልካም ነገር ግን አልመጣም፤ የፈውስ ጊዜን ተመኘን፤ ነገር ግን ሽብር ብቻ ሆነብን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፥ መልካምም አልተገኘም፤ መፈወስን በተስፋ ተጠባበቅን፥ እነሆም፥ ድንጋጤ ሆነ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ሰላምና ፈውስ የምናገኝበት ጊዜ ይመጣልናል ብለን ተስፋ አድርገን ነበር፤ በዚህ ፈንታ ሽብር በመምጣቱ ምኞታችን ከንቱ ሆኖ ቀረ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ሰላ​ምን በተ​ስፋ ተጠ​ባ​በ​ቅን፤ ለይ​ቅ​ር​ታም ጊዜ መል​ካም ነገ​ርን አጣን፤ እነ​ሆም ድን​ጋጤ ሆነ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 8:15
9 交叉引用  

ነገር ግን በጎነትን በተጠባበቅሁ ጊዜ ክፉ ነገር መጣችብኝ፥ ብርሃንን በትዕግሥት ጠበቅሁ፥ ጨለማም መጣ።


በወናዎች ኮረብቶች ሁሉ ላይ በዝባዦች መጥተዋል፥ የእግዚአብሔር ሰይፍ ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይበላልና፥ ለሥጋ ለባሽ ሁሉ ሰላም የለም።


በውኑ ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ነፍስህስ ጽዮንን ጠልታታለችን? ስለ ምን መታኸን? ፈውስስ ስለ ምን የለንም? ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፥ መልካምም አልተገኘም፥ ፈውስን በተስፋ ተጠባበቅን፥ እነሆም፥ ድንጋጤ ሆነ።


እኔም፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ፥ አንተ ሰይፍ እስከ ነፍስ ድረስ በደረሰ ጊዜ፦ ሰላም ይሆንላችኋል ብለህ ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን እጅግ አታለልህ አልሁ።


የጠላት ሰይፍና ድንጋጤ ከብበዋችኋልና ወደ ሜዳ አትውጡ በመንገድም ላይ አትሂዱ።


የሕዝቤንም ሴት ልጅ ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ፥ ሰላም ሳይሆን፦ ስለም ሰላም ይላሉ።


ጥፋት መጥቶአል፥ ሰላምም ይሻሉ እርሱም አይገኝም።


ክፉ ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ እስከ ኢየሩሳሌም በር ድረስ ወርዶአልና በማሮት የምትቀመጠው በጎነትን ትጠባበቃለች።


ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ያን ጊዜ ምጥ እርጕዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል ከቶም አያመልጡም።


跟着我们:

广告


广告