Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 8:13 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ፈጽሜ አጠፋችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በወይን ላይ ፍሬ፥ በበለስ ዛፍ ላይ በለስ አይሆንም፥ ቅጠልም ይረግፋል፥ የሚያልፉባቸውንም ሰጠኋቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ ‘ያመረቱትን ሁሉ እወስድባቸዋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በወይን ተክል ላይ የወይን ፍሬ አይኖርም፤ በበለስ ዛፍ ላይ የበለስ ፍሬ አይገኝም፤ ቅጠሎቻቸውም ይረግፋሉ። የሰጠኋቸው በሙሉ፣ ከእነርሱ ይወሰድባቸዋል።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ፈጽሜ አጠፋችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ በወይን ላይ ፍሬ፥ በበለስ ዛፍ ላይ በለስ አይሆንም፥ ቅጠልም ይረግፋል፤ የሰጠኋቸሁም ይጠፋባቸዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 “ገበሬ ሰብሉን እንደሚሰበስብ ሕዝቤን ልሰበስብ ፈለግኹ፤ እነርሱ ግን ዘለላ እንደሌለው የወይን ተክል ፍሬ አልባ እንደ ሆነ የበለስ ዛፍና ቅጠሉ እንደ ረገፈ ተክል ሆኑብኝ፤ በዚህ ምክንያት የሰጠኋቸውን ምድር ባዕዳን እንዲወስዱባቸው አደረግሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 አዝ​መ​ራ​ቸ​ውን ይሰ​በ​ስ​ባሉ፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነገር ግን በወ​ይን ላይ ፍሬ፥ በበ​ለስ ዛፍ ላይ በለስ የለም፤ ቅጠ​ልም ይረ​ግ​ፋል፤ ሰጠ​ኋ​ቸው፤ አለ​ፈ​ባ​ቸ​ውም።

参见章节 复制




ኤርምያስ 8:13
25 交叉引用  

ከወይኑ ቦታ አሥር ጥማድ በሬ ካረሰው አንድ የባዶስ መሥፈሪያ ብቻ ይወጣል፥ አንድ የቆሮስ መሥፈሪያ ዘር አንድ የኢፍ መሥፈሪያ ብቻ ይሰጣል።


በጾሙ ጊዜ ጸሎታቸውን አልሰማም፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን ባቀረቡ ጊዜ አልቀበላቸውም፥ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም አጠፋቸዋለሁ አለኝ።


ስለዚህ እግዚአብሔር በስሜ ትንቢት ስለሚናገሩ ነቢያት፦ በዚህች አገር ሰይፍና ራብ አይሆንም ስለሚሉ ስላላክኋቸው ነቢያት እንዲህ ይላል፦ እነዚያ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ።


በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ ሙቀትም ሲመጣ እንደማይፈራ ቅጠሉም እንደሚለመልም፥ በድርቅ ዓመትም እንደማይሠጋ ፍሬውንም እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል።


መከርህንና እንጀራህን ይበላሉ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህንም ይበሉአቸዋል፥ በጎችህንና ላሞችህንም ይበላሉ፥ ወይንህንና በለስህንም ይበላሉ፥ የምትታመናቸውን የተመሸጉ ከተሞችን በሰይፍ ይደበድባሉ።


እንግዲህም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ቍጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ፥ በሰውና በእንስሳ ላይ፥ በዱር ዛፎችና በምድር ፍሬ ላይ ይፈስሳል፥ ይነድዳል፥ አይጠፋምም።


ስለዚህ ቍጣዬን አፈሰስሁባቸው፥ በመዓቴም እሳት አጠፋኋቸው፥ መንገዳቸውንም በራሳቸው ላይ መለስሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


አሁንም ውሽሞችዋ እያዩ ነውርዋን እገልጣለሁ፥ ከእጄም ማንም አያድናትም።


ወይኔን ባዶ ምድር አደረገው፥ በለሴንም ሰበረው፥ ባዶም አደረገው፥ ጣለውም፥ ቅርንጫፎቹም ነጡ።


ጕልበታችሁም በከንቱ ያልቃል፤ ምድራችሁም እህልዋን አትሰጥም፥ የምድርም ዛፎች ፍሬአቸውን አይሰጡም።


ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥


እኔም በምድርና በተራሮች፥ በእህልና በወይንም፥ በዘይትና ምድርም በምታበቅለው ላይ፥ በሰዎችና በእንስሶችም ላይ፥ እጅም በሚደክምበት ሁሉ ላይ ድርቅን ጠርቻለሁ።


በእጃችሁ ሥራ ሁሉ ላይ በዋግና በአረማሞ በበረዶም መታኋችሁ፥ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር።


ስለ እናንተ ነቀዙን እገሥጻለሁ፥ የምድራችሁንም ፍሬ አያጠፋም፥ በእርሻችሁም ያለው ወይን ፍሬውን አያረግፍም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና፦ ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች።


ፀሐይ ከትኵሳት ጋር ይወጣልና፥ ሣርንም ያጠወልጋልና፥ አበባውም ይረግፋልና፥ የመልኩም ውበት ይጠፋልና፤ እንዲሁ ደግሞ ባለ ጠጋው በመንገዱ ይዝላል።


跟着我们:

广告


广告