Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 7:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 መጻተኛውንና ድሀ አደጉን መበለቲቱንም ባትገፉ፥ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን ባታፈስሱ፥ ክፉም ሊሆንባችሁ እንግዶችን አማልክት ባትከተሉ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 መጻተኛውንና ድኻ አደጉን፣ መበለቲቱንም ባትጨቍኑ፣ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደም ባታፈስሱ፣ የሚጐዷችሁን ሌሎች አማልክት ባትከተሉ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 መጻተኛውንና ድሀ አደጉን መበለቲቱንም ባትጨቊኑ፥ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን ባታፈስሱ፥ ክፉም እንዳይሆንባችሁ እንግዶችን አማልክት ባትከተሉ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 መጻተኞችን፥ እናትና አባት የሞቱባቸውን ልጆችና፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በመጨቈን አትበዝብዙ፤ በዚህች ምድር የሚኖሩ ንጹሓን የሆኑ ሰዎችን በግፍ አትግደሉ፤ እንዳትጠፉም ለሐሰተኞች አማልክት አትስገዱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 መጻ​ተ​ኛ​ው​ንና ድሃ​አ​ደ​ጉን፥ መበ​ለ​ቲ​ቱ​ንም ባት​ገፉ፥ በዚ​ህም ስፍራ ንጹሕ ደምን ባታ​ፈ​ስሱ፥ ክፉም ሊሆ​ን​ባ​ችሁ እን​ግ​ዶ​ችን አማ​ል​ክት ባት​ከ​ተሉ፤

参见章节 复制




ኤርምያስ 7:6
37 交叉引用  

ልጁንም በእሳት አሳለፈ፤ ሞራ ገላጭም ሆነ፤ አስማትም አደረገ፤ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም ሰበሰበ፤ ያስቈጣውም ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደረገ።


እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉ፥ ንጹሑን ደም ለማፍሰስ ይፈጥናሉ፥ አሳባቸው የኃጢአት አሳብ ነው፥ ጕስቍልናና ቅጥቃጤ በመንገዳቸው አለ።


ቃሌን ይሰሙ ዘንድ እንቢ የሚሉ፥ በልባቸውም እልከኝነት የሚሄዱ፥ ያመልኩአቸውና ይሰግዱላቸው ዘንድ ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ እነዚህ ክፉ ሕዝብ አንዳች እንዳማትረባ እንደዚች መታጠቂያ ይሆናሉ።


ትተውኛልና፥ ይህንም ስፍራ እንግዳ አድርገውታልና፥ እነርሱና አባቶቻቸውም ለማያውቋቸው ለሌሎች አማልክት ዐጥነዋልና የይሁዳም ነገሥታት ይህን ስፍራ በንጹህ ደም ሞልተዋልና፥


ልጆቻችሁን በከንቱ ቀሥፌአቸዋለሁ፥ ተግሣጽን አልተቀበሉም፥ ሰይፋችሁ እንደሚሰብር አንበሳ ነቢያቶቻችሁን በልቶአል።


በእጆችሽም የንጹሐን ድሆች ደም ተገኝቶአል፥ በእነዚህ ሁሉ ላይ በግልጥ አገኘሁት እንጂ በስውር ፈልጌ አላገኘሁትም።


ነገር ግን ይህን ቃል ሁሉ በጆሮአችሁ እናገር ዘንድ በእውነት እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛልና ብትገድሉኝ ንጹሕ ደምን በራሳችሁና በዚህች ከተማ በሚኖሩባትም ላይ እንድታመጡ በእርግጥ እወቁ።


ከግብጽም ኦርዮን አውጥተው ወደ ንጉሡ ወደ ኢዮአቄም ይዘውት መጡ፥ እርሱም በሰይፍ ገደለው ሬሳውንም ክቡራን ባልሆኑ ሰዎች መቃብር ጣለው።


ደግሞም፦ እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፥ ሥራችሁንም አሳምሩ፥ ታመልኩአቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፥ ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠሁት ምድር ትቀመጣላችሁ እያልሁ በማለዳ ተነሥቼ ባሪያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ልኬባችሁ ነበር፥ እናንተ ግን ጆሮአችሁን አላዘነበላችሁም እኔንም አልሰማችሁኝም።


ወፍረዋል ሰብተውማል፥ ክፋታቸውንም ያለ ልክ አብዝተዋል፥ የድሀ አደጎች ነገር መልካም እንዲሆን አልተምዋገቱላቸውም፥ የችግረኞችንም ፍርድ አልፈረዱላቸውም።


መንገዳችሁንና ሥራችሁን ፈጽማችሁ ብታሳምሩ፥ በሰውና በጎረቤቱ መካከል ቅን ፍርድ ብትፈርዱ፥


ትሰርቃላችሁ፥ ትገድላላችሁ፥ ታመነዝራላችሁ፥ በሐሰትም ትምላላችሁ፥ ለበኣልም ታጥናላችሁ፥ የማታውቋቸውንም እንግዶች አማልክት ትከተላላችሁ፥


ሜም። የጻድቃንን ደም በውስጥዋ ስላፈሰሱ ስለ ነቢያቶችዋ ኃጢአትና ስለ ካህናቶች በደል ነው።


በተራራም ላይ ባይበላ ዓይኞቹንም ወደ እስራኤል ቤት ጣዖታት ባያነሣ የባልንጀራውንም ሚስት ባያረክስ አደፍም ወዳለባት ሴት ባይቀርብ፥


በአንቺ ውስጥ አባትንና እናትን አቃለሉ፥ በመካከልሽ በመጻተኛው ላይ በደልን አደረጉ፥ በአንቺ ውስጥ ድሀ አደጉንና መበለቲቱን አስጨነቁ።


በአገራችሁ ውስጥ ከእናንተ ጋር እንግዳ ቢቀመጥ ግፍ አታድርጉበት።


እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ሰው ባልንጀራውን አያታልል፥ ነገር ግን አምላክህን ፍራ።


ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፥ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ሕዝቡም ሁሉ መልሰው፦ ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን አሉ።


ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ አለ። እነርሱ ግን፦ እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ አሉ።


መርገምም፥ የአምላካችሁን የእግዚአብሕርን ትእዛዝ ባትሰሙ፥ ዛሬ ካዘዝኋችሁ መንገድ ፈቀቅ ብትሉ፥ ሌሎችንም የማታውቍቸውን አማልክት ብትከተሉ ነው።


የመጻተኛውንና የድሀ አደጉን ፍርድ አታጣምምባቸው፤ የመበለቲቱን ልብስ ለመያዣ አትውሰድባት።


በመጻተኛ በድሀ አደጉም በመበለቲቱም ላይ ፍርድን የሚያጣምም ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።


አምላክህንም እግዚአብሔርን ብትረሳ፥ ሌሎችንም አማልክት ብትከተል ብታመልካቸውም ብትሰግድላቸውም፥ ፈጽሞ እንድትጠፉ እኔ ዛሬውኑ እመሰክርባችኋለሁ።


ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።


跟着我们:

广告


广告