Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 7:31 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 እኔም ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ያለችውን የቶፌትን መስገጃዎች ሠረተዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 እኔ ያላዘዝኋቸውን፣ ከቶም ያላሰብሁትን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት አቃጥለው ለመሠዋት በሄኖም ልጅ ሸለቆ የቶፌትን መስገጃ ኰረብቶች ሠሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 እኔም ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት ለማቃጠል፥ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ያሉትን የቶፌት መስገጃዎችን ሠረተዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት እያቃጠሉ መሥዋዕት አድርገው ለማቅረብ በሂኖም ሸለቆ ውስጥ ‘ቶፌት’ ተብሎ የሚጠራ መሠዊያ ሠርተዋል፤ ይህም እኔ ያላዘዝኳቸውና በፍጹምም ያላሰብኩት ነገር ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 እኔም ያላ​ዘ​ዝ​ሁ​ት​ንና በልቤ ያላ​ሰ​ብ​ሁ​ትን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ሳት ያቃ​ጥሉ ዘንድ በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ያለ​ች​ውን የቶ​ፌ​ትን መሥ​ዊ​ያ​ዎች ሠር​ተ​ዋል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 7:31
23 交叉引用  

ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት አሳለፉአቸው፤ ምዋርተኞችና አስማተኞችም ሆኑ፤ ያስቈጡትም ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር ለማድረግ ራሳቸውን ሸጡ።


ማንም ሰው ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን ለሞሎክ በእሳት እንዳያሳልፍ በሄኖም ልጆች ሸለቆ የነበረውን ቶፌትን ርኩስ አደረገው።


በዚያም የነበሩትን የኮረብታውን መስገጃዎች ካህናት ሁሉ በመሠዊያዎቹ ላይ ገደላቸው፤ የሰዎቹንም አጥንት በመሠዊያዎቹ ላይ አቃጠለ። ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሰ።


ደግሞም በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ዐጠነ፤ እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት እንዳሳደዳቸው እንደ አሕዛብም ክፉ ልማድ ልጆቹን በእሳት አቃጠለ።


በሄኖምም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ልጆቹን በእሳት አሳለፈ፤ ሞራ ገላጭም ሆነ፤ አስማትም አደረገ፤ መተተኛም ነበረ፤ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቍዮችንም ሰበሰበ፤ ያስቈጣውም ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደረገ።


ከቀድሞም ጀምሮ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅታለች፥ ለንጉሥም ተበጅታለች፥ ጥልቅና ሰፊም አድርጎአታል፥ እሳትና ብዙ ማገዶ ተከምሮአል፥ የእግዚአብሔርም እስትንፋስ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃጥለዋል።


እናንተ በአድባር ዛፎች መካከል በለመለመም ዛፍ ሁሉ በታች በፍትወት የምትቃጠሉ፥ እናንተም በሸለቆች ውስጥ በዓለትም ስንጣቂዎች በታች ሕፃናትን የምታርዱ፥ የዓመፅ ልጆችና የሐሰት ዘር አይደላችሁምን?


በካርሲት በር መግቢያ አጠገብ ወዳለው ወደ ሄኖም ልጅ ሸለቆ ሂድ፥ በዚያም የምነግርህን ቃል ተናገር፥


አንቺስ፦ አልረከስሁም በአሊምንም አልተከተልሁም እንዴት ትያለሽ? በቈላ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ፥ ያደረግሽውንም እወቂ፥ በመንገድም ላይ እንደ ተለቀቀች እንደ ፈጣን ግመል ሆነሻል፥


ያረክሱትም ዘንድ ስሜ በተጠራበት ቤት ውስጥ ርኵሰታቸውን አኖሩ።


ይሁዳን ወደ ኃጢአት እንዲያገቡት፥ ይህንን ርኵሰት ያደርጉ ዘንድ፥ እኔ ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን ነገር፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለሞሎክ በእሳት ያሳልፉ ዘንድ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ያሉትን የበኣልን የኮረብታውን መስገጃዎች ሠሩ።


ለእኔም የወለድሻቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወስደሽ መብል ይሆኑ ዘንድ ሠዋሽላቸው።


እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ እንዲያውቁ አጠፋቸው ዘንድ፥ ማኅፀን የሚከፍተውን ሁሉ በእሳት ባሳለፉ ጊዜ፥ በመባቸው አረከስኋቸው።


ቍርባናችሁን ባቀረባችሁ ጊዜ፥ ልጆቻችሁንም በእሳት ባሳለፋችሁ ጊዜ፥ እስከ ዛሬ ድረስ በጣዖቶቻችሁ ትረክሳላችሁን የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ከእናንተስ ዘንድ እጠየቃለሁን? እኔ ሕያው ነኛና ከእናንተ ዘንድ አልጠየቅም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥


ከዘርህም ለሞሎክ በእሳት አሳልፈህ አትስጥ፥ የአምላክህንም ስም አታርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


እግዚአብሔርስ በሺህ አውራ በጎች ወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋልን? ወይስ የበኵር ልጄን ስለ በደሌ፥ የሆዴንም ፍሬ ስለ ነፍሴ ኃጢአት እሰጣለሁን?


እግዚአብሔር የሚጠላውን ርኵሰት ሁሉ እነርሱ ለአማልክቶቻቸው አድርገዋልና፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ደግሞ ለአማልክቶቻቸው በእሳት ያቃጥሉአቸዋልና አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እንዲሁ አታድርግ።


ሄዶም ሌሎች አማልክትን ያመለከ፥ እኔ ላላዘዝኋቸው ለፀሐይና ለጨረቃ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ የሰገደ ቢገኝ፥ ቢያወሩልህም ብትሰማም፥


ወንድ ልጁን ሴት ልጁን በእሳት የሚያሳልፍ፥ ምዋርተኛም፥ ሞራ ገላጭም፥


ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ አጠገብ ኢየሩሳሌም ወደምትባለው ወደ ኢያቡሳዊው ወደ ደቡብ ወገን ወጣ፥ ድንበሩም በራፋይም ሸለቆ ዳር በሰሜን በኩል ባለው በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በምዕራብ ወገን ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ወጣ፥


跟着我们:

广告


广告