Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 7:28 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 አንተም፦ የአምላኩን የእግዚአብሔርን ቃል ያልሰማ፥ ተግሣጽንም ያልተቀበለ ሕዝብ ይህ ነው፥ እውነት ጠፍቶአል ከአፋቸውም ተቈርጦአል ትላቸዋለህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ስለዚህ እንዲህ በላቸው፤ ‘ይህ ሕዝብ አምላኩን እግዚአብሔርን ያልታዘዘ፣ ምክሩን ያልተቀበለ ወገን ነው፤ እውነት ጠፍቷል፤ ከአንደበታቸውም ሸሽቷል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 አንተም፦ “የአምላኩን የጌታን ድምፅ ያልሰማ፥ ተግሣጽንም ያልተቀበለ ሕዝብ ይህ ነው፤ እውነት ጠፍቶአል ከአፋቸውም ታጥቶአል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ይህ ሕዝብ ለእኔ ለአምላኩ የማይታዘዝና ከቅጣቱም ሥነ ሥርዓትን መማር የማይፈልግ ሆኖአል፤ በዚህ ምክንያት እውነት ጨርሳ ጠፍታለች፤ ስለ እርስዋ በአንደበቱ የሚያነሣ እንኳ የለም።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 አን​ተም፦ የአ​ም​ላ​ኩን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ያል​ሰማ፥ ተግ​ሣ​ጽ​ንም ያል​ተ​ቀ​በለ ሕዝብ ይህ ነው፤ እው​ነት ጠፍ​ቶ​አል፤ ከአ​ፋ​ቸ​ውም ተቈ​ር​ጦ​አል ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 7:28
21 交叉引用  

ዓመጸኛ ወገንና የእግዚአብሔርን ሕግ ለመስማት የማይወድዱ የሐሰት ልጆች ናቸውና፥


ቃሌንም ይሰሙ ዘንድ እንቢ ወዳሉ ወደ አባቶቻቸው ኃጢአት ተመለሱ፥ ያመልኩአቸውም ዘንድ እንግዶችን አማልክት ተከተሉ፥ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት ከአባቶቻቸው ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳን አፈረሱ።


እነርሱ ግን አልሰሙም ጆሮአቸውን አላዘነበሉም፥ እንዳይሰሙና እንዳይገሠጹም አንገታቸውን አደነደኑ።


ልጆቻችሁን በከንቱ ቀሥፌአቸዋለሁ፥ ተግሣጽን አልተቀበሉም፥ ሰይፋችሁ እንደሚሰብር አንበሳ ነቢያቶቻችሁን በልቶአል።


ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ወደ እኔ መለሱ፥ እኔም በማለዳ ተነሥቼ ሳስተምራቸው ተግሣጽን ይቀበሉ ዘንድ አልሰሙም።


በኢየሩሳሌም መንገድ እየተመላለሳችሁ ሩጡ፥ ተመልከቱም፥ እወቁም፥ በአደባባይዋም ፈልጉ፥ ፍርድን የሚያደርገውን እውነትንም የሚሻውን ሰው ታገኙ እንደሆነ ይቅር እላታለሁ።


አቤቱ፥ ዓይንህ እውነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል ነገር ግን አላዘኑም፥ ቀጥቅጠሃቸውማል ነገር ግን ተግሣጽን እንቢ አሉ፥ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፥ ይመለሱ ዘንድ እንቢ አሉ።


እኔም፦ የመለከቱን ድምፅ አድምጡ ብዬ ጠባቆችን ሾምሁባችሁ፥ እነርሱ ግን፦ አናደምጥም አሉ።


እነርሱ ሁሉ እጅግ ዓመፀኞች ናቸው፥ በጠማማነት ይሄዳሉ፥ ናስና ብረት ናቸው፥ ሁሉ ርኵሰትን ያደርጋሉ።


ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ነፍሴ ከአንቺ እንዳትለይ፥ አንቺንም ባድማና ወና እንዳላደርግሽ፥ ተግሣጽን ተቀበዪ።


እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እውነትና ምሕረት እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድር ስለሌለ እግዚአብሔር በምድሩ ላይ ከሚኖሩ ጋር ክርክር አለውና የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።


ድምፅን አልሰማችም፥ ተግሣጽንም አልተቀበለችም፥ በእግዚአብሔርም አልታመነችም፥ ወደ አምላክዋም አልቀረበችም።


እኔም፦ ይፈሩኛል፥ ተግሣጽንም ይቀበላሉ፥ ካዘዝኋትም ሁሉ ከዓይንዋ ምንም አይጠፋም ብዬ ነበር፥ እነርሱ ግን በማለዳ ተነሥተው ድርጊታቸውን ሁሉ አረከሱ።


跟着我们:

广告


广告