Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 7:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እንግዲህም አልሰማህምና ስለዚህ ሕዝብ አትጸልይ ስለ እነርሱም ልመናና ጸሎት አታድርግ፥ አትማልድላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 “እንግዲህ ስለማልሰማህ፣ ለዚህ ሕዝብ አትጸልይ፤ ልመና አታቅርብ፤ አትማጠን፤ አትማልድላቸውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 “እንግዲህም አልሰማህምና ስለዚህ ሕዝብ አትጸልይ ስለ እነርሱም ልመናና ጸሎት አታድርግ፤ አትማልድላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ኤርምያስ ሆይ! ስለ ነዚህ ሕዝብ አትጸልይ፤ ስለ እነርሱ በመጸለይም አትጩኽ፤ ስለማልማለድህ ስለ እነርሱ ልትማልደኝ አያስፈልግም፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “ስለ​ዚህ ሕዝብ አንተ አት​ጸ​ልይ፤ ይቅር እላ​ቸው ዘንድ አት​ማ​ል​ደኝ፤ የእ​ነ​ር​ሱን ነገር አል​ሰ​ማ​ህ​ምና ትለ​ም​ን​ላ​ቸው ዘንድ ወደ እኔ አት​ምጣ።”

参见章节 复制




ኤርምያስ 7:16
14 交叉引用  

የዮዳሄ ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ ነበረ፥ የዳዊትም ልጆች አማካሪዎች ነበሩ።


አሁንም ቁጣዬ እንዲቃጠልባቸው እንዳጠፋቸውም ተወኝ፤ አንተንም ለታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ አለው።


እጃችሁንም ወደ እኔ ብትዘረጉ ዓይኔን ከእናንተ እሰውራለሁ፥ ልመናንም ብታበዙ አልሰማችሁም፥ እጆቻችሁ ደም ተሞልተዋል።


አንተም ስለዚህ ሕዝብ አትጸልይ፥ ከመከራቸው የተነሣ ወደ እኔ በጮኹ ጊዜ አልሰማቸውምና ስለ እነርሱም ጩኸትና ልመና አታድርግ።


እግዚአብሔርም እንደዚህ አለኝ፦ ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አይዘነብልም፥ ከፊቴ ጣላቸው፥ ይውጡ።


አንቺ እኔን ጥለሻል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ወደ ኋላሽም ተመልሰሻል፥ ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቼ አጥፍቼሻለሁ፥ ከይቅርታ ደክሜአለሁ።


ለነፍሴ ጕድጓድ ቈፍረዋልና በውኑ በመልካም ፋንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም እናገር ዘንድ ቍጣህንም ከእነርሱ እመልስ ዘንድ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስብ።


ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች፥ በላይም ሰማይ ይጠቍራል፥ ተናግሬአለሁና፥ አስቤአለሁም፥ አልጸጸትም ከእርሱም አልመለስም።


እነርሱስ በይሁዳ ከተሞች ውስጥና በኢየሩሳሌም አደባባይ ላይ የሚያደርጉትን አታይምን?


የዚያን ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉ፥ እርሱም አይሰማቸውም፥ ሥራቸውንም ክፉ አድርገዋልና በዚያን ጊዜ ፊቱን ከእነርሱ ይሰውራል።


አጠፋቸው ዘንድ፥ ስማቸውንም ከሰማይ በታች እደመስስ ዘንድ ተወኝ፤ አንተንም ከእነርሱ ለሚበረታና ለሚበዛ ሕዝብ አደርግሃለሁ ብሎ ተናገረኝ።


ማንም ወንድሙን ሞት የማይገባውን ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይለምን፥ ሞትም የማይገባውን ኃጢአት ላደረጉት ሕይወት ይሰጥለታል። ሞት የሚገባው ኃጢአት አለ፤ ስለዚያ እንዲጠይቅ አልልም።


跟着我们:

广告


广告