Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 6:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰው ወይኑን እንደሚቃርም፥ እንዲሁ ከእስራኤል የቀሩትን ፈጽሞ ይቃርሙአቸዋል፥ እጅህንም እንደ ለቃሚ ወደ እንቅብ ዘርጋ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የወይን ፍሬ ተሟጦ እንደሚቃረም፣ ከእስራኤል የተረፉትን እንዲሁ ይቃርሟቸው። ወይን ለቃሚ እንደሚለቅም፣ እጅህን ወደ ቅርንጫፎቹ ደጋግመህ ዘርጋ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ሰው ወይኑን እንደሚለቅም፥ እንዲሁ ከእስራኤል የተረፉትን ፈጽሞ ይለቅሙአችኋል፤ እጅህንም እንደ ለቃሚ በቅርንጫፎቹ ላይ ዳግመኛ ዘርጋ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከእስራኤል የተረፉትን የወይን ዘለላን እንደሚለቅም ሰው ልቀሙ፤ መላልሳችሁ ወይንን እንደሚለቅም ሰው እጃችሁን በቅርንጫፎቹ ላይ ዘርጉ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰው ወይ​ንን እን​ደ​ሚ​ቃ​ርም፥ እን​ዲሁ ከእ​ስ​ራ​ኤል የቀ​ሩ​ትን ይቃ​ር​ሙ​አ​ቸ​ዋል፤ እጅ​ህን እንደ ወይን ለቃሚ ወደ እን​ቅብ ዘርጋ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 6:9
7 交叉引用  

በምጐበኛቸውም ዓመት በዓናቶት ሰዎች ላይ ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁና ማንም ከእነርሱ የሚቀር የለም።


እነሆ፥ ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እሰድዳለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እነርሱም ያጠምዱአቸዋል፥ ከዚያም በኋላ ብዙ አዳኞችን እሰድዳለሁ፥ እነርሱም ከየተራራውና ከየኮረብታው ሁሉ ከየድንጋዩም ስንጣቂ ውስጥ ያድኑአቸዋል።


ወይን ለቃሚዎች ቢመጡብህ፥ ቃርሚያውን አይተውልህምን? ሌቦችስ በሌሊት ቢመጡ፥ የሚያጠፉት እስኪበቃቸው ድረስ አይደለምን?


እኔም ባሳደድኋቸው ስፍራ ሁሉ የቀሩ፥ ከዚህች ክፉ ወገን የተረፉ ቅሬታዎች ሁሉ፥ ከሕይወት ይልቅ ሞትን ይመርጣሉ።


በእሳትም ላይ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከመሠዊያው ወጥቶ ስለታም ማጭድ ያለውን፦ ዘለላዎቹ ፈጽመው በስለዋልና ስለታሙን ማጭድህን ስደድና በምድር ያለውን የወይን ዛፍ ዘለላዎች ቍረጥ ብሎ በታላቅ ድምፅ ጠራ።


跟着我们:

广告


广告