Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 6:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በጕድጓድ ውኃ እንደሚፈልቅ፥ እንዲሁ ክፋትዋ ከእርስዋ ዘንድ ይፈልቃል፥ ግፍና ቅሚያ በእርስዋ ዘንድ ይሰማል፥ ደዌና ቍስልም ሁልጊዜ በፊቴ አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የውሃ ጕድጓድ ውሃ እንደሚያመነጭ፣ እርሷም እንዲሁ ክፋቷን ታፈልቃለች። ዐመፅና ጥፋት በውስጧ ይስተጋባል፤ ሕመሟና ቍስሏ ዘወትር ይታየኛል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በጉድጓድ ውኃ እንደሚፈልቅ፥ እንዲሁ ክፋትዋ ከእርሷ ውስጥ ይፈልቃል፤ ግፍና ቅሚያ በእርሷ መካከል ይሰማል፥ ደዌና ቁስልም ሁልጊዜ በፊቴ አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ጒድጓድ ውሃን እንደሚያፈልቅ፥ ኢየሩሳሌምም የክፋት ሁሉ መፍለቂያ ናት፤ በእርስዋ የሚሰማው የግፍና የጥፋት ጩኸት ብቻ ነው፤ ዘወትር የሚታይባትም ሕመምና ቊስል ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በጕ​ድ​ጓድ ውኃ እን​ደ​ሚ​ፈ​ልቅ፥ እን​ዲሁ ክፋቷ ከእ​ር​ስዋ ዘንድ ይፈ​ል​ቃል፤ ግፍና ቅሚያ በእ​ር​ስዋ ዘንድ ይሰ​ማል፤ ደዌና ቍስ​ልም ሁል​ጊዜ በፊቷ አለ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 6:7
24 交叉引用  

ከእግር ጫማ አንስቶ እስከ ራስ ድረስ ጤና የለውም፥ ቍስልና እበጥ የሚመግልም ነው፥ አልፈረጠም፥ አልተጠገነም፥ በዘይትም አልለዘበም።


ክፉዎች ግን እንደሚንቀሳቀስ ባሕር ናቸው፥ ጸጥ ይል ዘንድ አይችልምና፥ ውኆቹም ጭቃና ጕድፍ ያወጣሉና።


ድሮቻቸውም ልብስ አይሆኑላቸውም፥ በሥራቸውም አይሸፈኑም፥ ሥራቸውም የበደል ሥራ ነው፥ የግፍም ሥራ በእጃቸው ነው።


በተናገርሁ ቍጥር እጮኻለሁ፥ ግፍና ጥፋት ብዬ እጮኻለሁ፥ የእግዚአብሔር ቃል ቀኑን ሁሉ ስድብና ዋዛ ሆኖብኛልና።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስብራትህ የማይፈወስ ቍስልህም ክፉ ነው።


ትጠገን ዘንድ ክርክርህን የሚፈርድልህ የለም፥ ቍስልህንም የሚፈውስ መድኃኒት የለህም።


ሕመምህ የማይፈወስ ሆኖአልና ስለ ስብራትህ ለምን ትጮኻለህ? በደልህ ታላቅ ስለሆነ ኃጢአትህም ስለ በዛ፥ ይህን አድርጌብሃለሁ።


ከፊቴ አስወግዳት ዘንድ ይህች ከተማ ከሠሩአት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ቍጣዬንና መዓቴን ለማነሣሣት ሆናለችና፥


በገለዓድ የሚቀባ መድኃኒት የለምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለምን? የወገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለ ምን አልሆነም?


ደምዋ በውስጥዋ አለ። በተራቈተ ድንጋይ ላይ አደረገችው እንጂ በአፈር ይከደን ዘንድ መሬት ላይ አላፈሰሰችውም፥ መዓቴን አወጣ ዘንድ፥


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል አለቆች ሆይ፥ ይብቃችሁ፥ ግፍንና ብዝበዛን አስወግዱ፥ ፍርድንና ጽድቅንም አድርጉ፥ ቅሚያችሁን ከሕዝቤ ላይ አርቁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ግፍ ወደ ክፋት ብትር ተነስቶአል ከእነርሱና ከብዛታቸው ከሀብታቸውም ምንም አይቀርም፥ የሚያለቅስላቸውም የለም።


ምድር ደም ባመጣው በደል፥ ከተማም በግፍ ተሞልታለችና ሰንሰለት ሥራ።


ለዓመፀኛይቱና ለረከሰች ለአስጨናቂይቱም ከተማ ወዮላት!


跟着我们:

广告


广告