Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 6:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ዛፎችዋን ቍረጡ፥ በኢየሩሳሌምም ላይ አፈርን ደልድሉ፥ ይህች ከተማ የምትቀሠፍ ናት፥ መካከልዋ ሁሉ ግፍ ብቻ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “ዛፎቹን ቍረጡ፤ በኢየሩሳሌም ዙሪያ የዐፈር ድልድል ሥሩ። ይህች ከተማ ቅጣት ይገባታል፤ ግፍን ተሞልታለችና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ “ዛፎችዋን ቁረጡ፥ በኢየሩሳሌምም ላይ አፈርን ደልድሉ፤ ይህች ከተማ የምትቀሠፍ ናት፤ በመካከልዋ ያለው ነገር ሁሉ ግፍ ብቻ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ዛፎችን ቊረጡ፤ በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደምሽግ ሆኖ የሚያገለግል ዐፈር ቈልሉ፤ እርስዋ በግፍ የተሞላች ስለ ሆነ መቀጣት የሚገባት ከተማ ናት፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ኀያል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ዛፎ​ች​ዋን ቍረጡ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ላይ ኀይ​ልን አፍ​ስሱ ይህች ከተማ የሐ​ሰት ከተማ ናት፤ መካ​ከ​ልዋ ሁሉ ግፍ ብቻ ነው።

参见章节 复制




ኤርምያስ 6:6
15 交叉引用  

ስለዚህም እግዚአብሔር ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ወደዚች ከተማ አይመጣም፥ ፍላጻንም አይወረውርባትም፥ በጋሻም አይመጣባትም፥ የአፈርንም ድልድል አይደለድልባትም።


በተናገርሁ ቍጥር እጮኻለሁ፥ ግፍና ጥፋት ብዬ እጮኻለሁ፥ የእግዚአብሔር ቃል ቀኑን ሁሉ ስድብና ዋዛ ሆኖብኛልና።


ዓይንህና ልብህ ግን ለስስት ንጹሕ ደምንም ለማፍሰስ ዓመፅንና ግፍንም ለመሥራት ብቻ ነው።


እነሆ የአፈር ድልድል፥ ሊይዙአትም እስከ ከተማይቱ ድረስ ቀርበዋል፥ ከሰይፍና ከራብ ከቸነፈርም የተነሣ ከተማይቱ ለሚዋጉአት ለከለዳውያን እጅ ተሰጥታለች፥ የተናገርኸውም ሆኖአል፥ እነሆም፥ አንተ ታየዋለህ።


ከፊቴ አስወግዳት ዘንድ ይህች ከተማ ከሠሩአት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ቍጣዬንና መዓቴን ለማነሣሣት ሆናለችና፥


የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለአፈር ድልድልና ለምሽግ ስለ ፈረሱ ስለዚህች ከተማ ቤቶች፥ ስለ ይሁዳም ነገሥታት ቤቶች እንዲህ ይላልና፦


ኢየሩሳሌምም በተያዘች ጊዜ፥ በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ በዘጠነኛው ዓመት በአሥረኛው ወር የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ከበቡአት፥


በውኑ ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀሥፍምን? ይላል እግዚአብሔር፥ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?


በውኑ ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀሥፍምን? ይላል እግዚአብሔር፥ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?


ምሽግም ሥራባት፥ አፈርም ደልድልባት፥ ሰፈርም አቁምባት፥ በዙሪያዋም የሚያፈርስ ግንድ አድርግባት።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህች ኢየሩሳሌም ናት፥ በአሕዛብም መካከል አድርጌአታለሁ፥ አገሮችም በዙሪያዋ አሉ።


የሰሜንም ንጉሥ ይመጣል፥ አፈርንም ይደለድላል፥ የተመሸገችንም ከተማ ይወስዳል፥ የደቡብም ሠራዊት የተመረጡትም ሕዝቡ አይቆሙም፥ ለመቋቋምም ኃይል የላቸውም።


ለዓመፀኛይቱና ለረከሰች ለአስጨናቂይቱም ከተማ ወዮላት!


ወራት ይመጣብሻልና፥ ጠላቶችሽም ቅጥር ይቀጥሩብሻል ይከቡሻልም በየበኵሉም ያስጨንቁሻል፤


跟着我们:

广告


广告