Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 6:24 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ወሬውን ሰምተናል፥ እጃችን ደክማለች፥ ምጥ ወላድን ሴት እንደሚይዛት ጭንቀት ይዞናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ስለ እነርሱ ወሬ ደርሶናል፤ ክንዶቻችንም ዝለዋል፤ ጭንቀት ይዞናል፤ እንደምታምጥም ሴት ሆነናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ወሬውን ሰምተናል፥ እጃችን ደክማለች፤ ምጥ ወላድን ሴት እንደሚይዛት ጭንቀት ይዞናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 የኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ይላሉ፦ “ወሬውን ስለ ሰማን ክንዳችን ዛለ፤ በምጥ እንደ ተያዘች ሴትም ጭንቀትና ሕመም ተሰምቶናል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ጩኸ​ታ​ቸ​ውን ሰም​ተን፥ እጃ​ችን ደክ​ማ​ለች፤ ወላ​ድን ሴት ምጥ እን​ደ​ሚ​ይ​ዛት ጭን​ቀት ይዞ​ናል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 6:24
19 交叉引用  

ስለዚህ ወገቤ ሕመም ተሞላ፥ እንደምትወልድ ሴት ምጥ ያዘኝ፥ ከሕመሜ የተነሣ አልሰማም፥ ከድንጋጤም የተነሣ አላይም።


ባለፈም ጊዜ ይወስዳችኋል፥ ማለዳ ማለዳ ቀንና ሌሊት ያልፋል፥ ወሬውንም ማስተዋል ድንጋጤ ይሆናል።


ወዳጆችሽ እንዲሆኑ ያስተማርሻቸውን በራስሽ ላይ አለቆች ባደረጋቸው ጊዜ ምን ትያለሽ? እንደ ወላድ ሴት ምጥ አይዝሽምን?


አንቺ በሊባኖስ የምትቀመጪ፥ በዝግባ ዛፍም ውስጥ ጎጆሽን የምትሠሪ ሆይ፥ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ሕማም በያዘሽ ጊዜ እንዴት ታጓሪያለሽ!


ጠይቁ፥ ወንድ ይወልድ እንደ ሆነ ተመልከቱ፥ ስለ ምን ሰው ሁሉ እንደ ወላድ እጁን በወገቡ ላይ አድርጎ ፊቱም ሁሉ ወደ ጥቁረት ተለውጦ አየሁ?


እንደምታምጥ የበኵርዋንም እንደምትወልድ ሴት ድምፅ ሰምቻለሁና፥ የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድካም ይሰልላል፥ እጆችዋንም ትዘረጋለችና፦ ተገድለው ከሞቱት የተነሣ ነፍሴ ዝላለችና ወዮልኝ! አለች።


ከተሞቹ ተይዘዋል፥ አምባዎቹም ተወስደዋል፥ በዚያም ቀን የሞዓብ ኃያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል።


ደማስቆ ደከመች ትሸሽም ዘንድ ዘወር አለች እንቅጥቅጥም ያዛት፥ እንደ ወላድም ሴት ጣርና ምጥ ያዛት።


የባቢሎን ንጉሥ ወሬአቸውን ሰምቶአል፥ እጁም ደክማለች፥ ጭንቀትም ይዞታል፥ ምጥ ወላድ ሴትን እንደሚይዛት ጭንቀት ይዞታል።


እጅ ሁሉ ትደክማለች ጕልበትም ሁሉ እንደ ውኃ ትቀልጣለች።


ንጉሡም ብልጣሶር እጅግ ደነገጠ፥ ፊቱም ተለወጠበት፥ መኳንንቶቹም ተደናገጡ።


እኔ ሰምቻለሁ፥ ልቤም ደነገጠብኝ፥ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፥ መንቀጥቀጥ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፥ በስፍራዬ ሆኜ ተናወጥሁ፥ በሚያስጨንቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።


ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ያን ጊዜ ምጥ እርጕዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል ከቶም አያመልጡም።


跟着我们:

广告


广告