Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 6:23 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ቀስትንና ጦርን ይይዛሉ፥ ጨካኞች ናቸው፥ ምሕረትንም አያደርጉም፥ ድምፃቸው እንደ ባሕር ይተምማል፥ በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ፥ የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፥ ለሰልፍ እንደ ተዘጋጀ ሰው እያንዳንዳቸው በአንቺ ላይ ተሰለፉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ቀስትና ጦር ይዘዋል፤ ጨካኞችና ምሕረት የለሽ ናቸው፤ ፈረሶቻቸውን ሲጋልቡ፣ ድምፃቸው እንደ ተናወጠ ባሕር ነው፤ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ ለሰልፍ የታጠቁ ሆነው፣ ሊወጉሽ ይመጣሉ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ቀስትንና ጦርን ይይዛሉ፤ ጨካኞች ናቸው፥ ምሕረትንም አያደርጉም፤ ድምፃቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይጮኻል፥ በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ፤ የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ! ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ሰው እያንዳንዳቸው በአንቺ ላይ ተሰለፉ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ቀስታቸውንና ሰይፋቸውን አንሥተዋል፤ እነርሱም ምሕረት የሌላቸው ጨካኞች ናቸው፤ ተቀምጠው የሚጋልቡአቸው ፈረሶች፥ የኮቴአቸው ድምፅ እንደ ባሕር ሞገድ ነው። እነሆ እነርሱ ኢየሩሳሌምን ለመውጋት ተዘጋጅተዋል።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ቀስ​ት​ንና ጦርን ይይ​ዛሉ፤ ጨካ​ኞች ናቸው፤ ምሕ​ረ​ትም አያ​ደ​ር​ጉም፤ ድም​ፃ​ቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይተ​ም​ማል፤ በሰ​ረ​ገ​ላና በፈ​ረ​ሶ​ችም ላይ ይቀ​መ​ጣሉ፤ የጽ​ዮን ሴት ልጅ ሆይ! እንደ እሳት ያጠ​ፉ​ሻል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 6:23
21 交叉引用  

ዛሬ በኖብ ይቆማል፥ በጽዮን ሴት ልጅ ተራራ በኢየሩሳሌም ኮረብታ ላይ እጁን ያንቀሳቅሳል።


ፍላጾቻቸውም ጎበዞችን ይጨፈጭፋሉ፥ የማኅፀንንም ፍሬ አይምሩም፥ ዓይኖቻቸውም ለሕፃናት አይራሩም።


እንደ ባሕር ሞገድ ድምፅ ለሚተምሙ ለወገኖች ብዛት፥ እንደ ኃይለኛም ውኃ ጩኸት ለሚጮኹ አሕዛብ ወዮላቸው!


ግብጻውያንንም በጨካኝ ጌታ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ ጨካኝ ንጉሥም ይገዛቸዋል ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ክፉ ነገር ከሕዝብ ወደ ሕዝብ ይወጣል፥ ጽኑም ዐውሎ ነፍስ ከምድር ዳርቻ ይነሣል።


ልኬ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ ባሪያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፥ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፥ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፥ ለመደነቂያና ለማፍዋጫም ለዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።


ውሽሞችህ ሁሉ ረስተውሃል አይፈልጉህምም፥ በደልህ ታላቅ ስለሆነ ኃጢአትህም ስለ በዛ፥ በጠላት ማቍሰልና በጨካኝ ቅጣት አቍስዬሃለሁና።


እነሆ፥ እንደ ደመና ይወጣል፥ ሰረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ፥ ፈረሶቹም ከንስር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው። ጠፍተናልና ወዮልን።


ለአሕዛብ አሰሙና፦ እነሆ፥ ጠባቂዎች ከሩቅ አገር ይመጣሉ፥ በይሁዳም ከተሞች ላይ ይጮኻሉ ብላችሁ በኢየሩሳሌም ላይ አውሩ።


ከፈረሰኞችና ከቀስተኞች ድምፅ የተነሣ ከተማ ሁሉ ሸሽታለች፥ ወደ ችፍግ ዱርም ይገባሉ በቋጥኝ ላይም ይወጣሉ፥ ከተማ ሁሉ ተለቅቃለች የሚቀመጥባትም ሰው የለም።


የፍላጻቸውም ሰገባ እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፥ ሁሉም ኃያላን ናቸው።


እነሆ፥ ሕዝብ ከሰሜን ይመጣል ታላቅ ሕዝብና ብዙ ነገሥታትም ከምድር ዳርቻ ይነሣሉ።


ቀስትንና ጦርን ይይዛሉ፥ ጨካኞች ናቸው ምሕረትም አያደርጉም፥ ድምፃቸው እንደ ባሕር ይተምማል በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ፥ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፥ ለሰልፍ እንደ ተዘጋጀ ሰው እያንዳንዳቸው በአንቺ ላይ ተሰለፉ።


በእርስዋ ላይ ሰልፍ አዘጋጁ ተነሡ፥ በቀትርም እንውጣ። ቀኑ መሽቶአልና፥ የማታውም ጥላ ረዝሞአልና ወዮልን።


የፈረሰኞቹ ድምጽ ከዳን ተሰማ፥ ከአርበኞች ፈረሶች ማሽካካት የተነሣ ምድር ሁሉ ተንቀጠቀጠች፥ መጡም ምድሪቱንና በእርስዋም ያለውን ሁሉ፥ ከተማይቱንና የተቀመጡባትንም በሉ።


ቍጣዬንም አፈስስብሃለሁ፥ በመዓቴም እሳት አናፋብሃለሁ፥ ማጥፋትንም ለሚያውቁ ለጨካኞች ሰዎች እጅ አሳልፌ እሰጥሃለሁ።


እግዚአብሔር ቍንቍቸውን የማታውቀውን፥ ፊታቸው የደነደነውን፥ ሽማግሌውንም የማያፍሩትን፥ ሕፃኑንም የማይምሩትን ሕዝብ ንስር እንደሚበርር ከሩቅ አገር ከምድር ዳር ያመጣብሃል።


跟着我们:

广告


广告