Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 6:22 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሕዝብ ከሰሜን አገር ይመጣል፥ ታላቅ ሕዝብም ከምድር ዳርቻ ይነሣል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ሰራዊት፣ ከሰሜን ምድር እየመጣ ነው፤ ከምድር ዳርቻም፣ ታላቅ ሕዝብ እየተነሣሣ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ሕዝብ ከሰሜን አገር ይመጣል፥ ታላቅ ሕዝብም ከምድር ዳርቻዎች ይነሣል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በሰሜን በኩል ከሚገኝ አገር ወራሪ ይመጣል፤ በሩቅ ያለ ታላቅ ሕዝብም ለጦርነት ተዘጋጅቶአል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ሕዝብ ከሰ​ሜን ሀገር ይመ​ጣል፤ ታላቅ ሕዝ​ብም ከም​ድር ዳርቻ ይነ​ሣል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 6:22
18 交叉引用  

የወሬን ድምፅ ስሙ፥ እነሆም፥ የይሁዳን ከተሞች ባድማና የቀበሮ ማደሪያ ያደርጋቸው ዘንድ ከሰሜን ምድር ጽኑ ሽብር መጥቶአል።


ዓይናችሁን አንሥታችሁ እነዚህን ከሰሜን የሚመጡትን ተመልከቱ፥ ለአንቺ የተሰጠ መንጋ፥ የተዋበ መንጋሽ፥ ወዴት አለ?


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ክፉ ነገር ከሕዝብ ወደ ሕዝብ ይወጣል፥ ጽኑም ዐውሎ ነፍስ ከምድር ዳርቻ ይነሣል።


ልኬ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ ባሪያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፥ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፥ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፥ ለመደነቂያና ለማፍዋጫም ለዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ የሚያስፈራ ድምፅ ሰምተናል፥ የፍርሃት ነው እንጂ የሰላም አይደለም።


ለአሕዛብ አሰሙና፦ እነሆ፥ ጠባቂዎች ከሩቅ አገር ይመጣሉ፥ በይሁዳም ከተሞች ላይ ይጮኻሉ ብላችሁ በኢየሩሳሌም ላይ አውሩ።


ከሰሜን ክፉ ነገርንና ጽኑ ጥፋትን አመጣለሁና ወደ ጽዮን ዓላማን አንሡ፥ ሽሹ፥ አትዘግዩ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ውኃ ከሰሜን ይነሣል የሚያጥለቀልቅም ፈሳሽ ይሆናል፥ በአገሪቱና በመላዋ ሁሉ፥ በከተማይቱና በሚኖሩባት ላይ ይጐርፋል፥ ሰዎቹም ይጮኻሉ፥ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ።


የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እነሆ፥ ሕዝብን ከሩቅ አመጣባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ኃያል ጥንታዊ ሕዝብ ነው፥ ቋንቋቸውንም የማታውቀው የሚናገሩትንም የማታስተውለው ሕዝብ ነው።


የፍላጻቸውም ሰገባ እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፥ ሁሉም ኃያላን ናቸው።


እናንተ የብንያም ልጆች፥ ክፉ ነገር ታላቅም ጥፋት ከሰሜን ይጐበኛልና ከኢየሩሳሌም ውስጥ ሽሹ፥ በቴቁሔ መለከቱን ንፉ፥ በቤትሐካሪም ላይ ምልክት አንሡ።


ቍጣዬንም አፈስስብሃለሁ፥ በመዓቴም እሳት አናፋብሃለሁ፥ ማጥፋትንም ለሚያውቁ ለጨካኞች ሰዎች እጅ አሳልፌ እሰጥሃለሁ።


ስለዚህ፥ ኦሖሊባ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፍስሽ ከእነርሱ የተለየች ውሽሞችሽን አስነሣብሻለሁ፥ በዙሪያሽም በአንቺ ላይ አመጣቸዋለሁ።


እነሆ፥ የእነርሱ ያልሆነውን መኖሪያ ይወርሱ ዘንድ በምድር ስፋት ላይ የሚሄዱትን መራሮችንና ፈጣኖችን ሕዝብ ከለዳውያንን አስነሣለሁ።


እግዚአብሔር ቍንቍቸውን የማታውቀውን፥ ፊታቸው የደነደነውን፥ ሽማግሌውንም የማያፍሩትን፥ ሕፃኑንም የማይምሩትን ሕዝብ ንስር እንደሚበርር ከሩቅ አገር ከምድር ዳር ያመጣብሃል።


跟着我们:

广告


广告