Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 6:18 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 አሕዛብ ሆይ፥ ስለዚህ ስሙ፥ ማኅበር ሆይ፥ እነዚያ የሚያገኛቸውን እወቁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እንግዲህ ሕዝቦች ሆይ ስሙ፤ እናንተም ምስክሮች ምን እንደሚገጥማቸው አስተውሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 አሕዛብ ሆይ! ስለዚህ ስሙ፤ ማኅበር ሆይ! በእነርሱ ምን እንደሚደርስባቸው እወቁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ስለዚህም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “እናንተ ሕዝቦች ስሙ! በሕዝቤ ላይ የማደርገውንም ሁሉ አስተውሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 አሕ​ዛ​ብና የመ​ን​ጋው ጠባ​ቂ​ዎች ሆይ፥ ስለ​ዚህ ስሙ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 6:18
9 交叉引用  

አሁንም እናንተ በኢየሩሳሌም የምትኖሩ የይሁዳ ሰዎችም ሆይ፥ በእኔና በወይኑ ቦታዬ መካከል እስኪ ፍረዱ።


አሕዛብ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ በሩቅም ላሉ ደሴቶች አውሩና፦ እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስበዋል፥ እረኛም መንጋውን እንደሚጠብቅ ይጠብቀዋል በሉ።


እኔም፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ፥ አንተ ሰይፍ እስከ ነፍስ ድረስ በደረሰ ጊዜ፦ ሰላም ይሆንላችኋል ብለህ ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን እጅግ አታለልህ አልሁ።


ለአሕዛብ አሰሙና፦ እነሆ፥ ጠባቂዎች ከሩቅ አገር ይመጣሉ፥ በይሁዳም ከተሞች ላይ ይጮኻሉ ብላችሁ በኢየሩሳሌም ላይ አውሩ።


እኔም፦ የመለከቱን ድምፅ አድምጡ ብዬ ጠባቆችን ሾምሁባችሁ፥ እነርሱ ግን፦ አናደምጥም አሉ።


ምድር ሆይ፥ ስሚ፥ እነሆ፥ ቃሌን ስላልሰሙ ሕጌንም ስለ ጣሉ፥ በዚህ ሕዝብ ላይ የአሳባቸውን ፍሬ፥ ክፉን ነገር አመጣባቸዋለሁ።


ሕዝቤ ሆይ፥ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ የመከረውን፥ የቢዖርም ልጅ በለዓም የመለሰለትን አሁን አስብ፥ የእግዚአብሔርንም የጽድቅ ሥራ ታውቅ ዘንድ ከሰጢም ጀምሮ እስከ ጌልገላ ድረስ አስብ።


跟着我们:

广告


广告