Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 6:15 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ርኩስን ነገር ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም፥ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፥ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ስለ ጸያፉ ተግባራቸው ዐፍረዋል እንዴ? የለም! በጭራሽ አላፈሩም፤ ዕፍረት ምን እንደ ሆነ እንኳ አያውቁም፤ ስለዚህ ከወደቁት ጋራ ይወድቃሉ፤ በምቀጣቸውም ጊዜ ይዋረዳሉ፤” ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ርኩስን ነገር ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም፤ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፤ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥” ይላል ጌታ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ይህን ሁሉ አጸያፊ ነገር ሠርተው ኀፍረት ተሰምቶአቸው ነበርን? እንኳንስ ሊያፍሩ ቀርቶ ዐይናቸው እንኳ ሰበር አላለም፤ ስለዚህ ሌሎች እንደ ወደቁ እነርሱም ይወድቃሉ፤ እኔ በምቀጣቸው ጊዜ ፍጻሜአቸው ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ርኩስ ነገ​ርን ስለ ሠሩ አፍ​ረ​ዋ​ልን? ምንም አላ​ፈ​ሩም፤ ውር​ደ​ት​ንም አላ​ወ​ቁም፤ ስለ​ዚ​ህም ከሚ​ወ​ድቁ ጋር ይወ​ድ​ቃሉ፤ በጐ​በ​ኘ​ኋ​ቸው ጊዜ ይዋ​ረ​ዳሉ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

参见章节 复制




ኤርምያስ 6:15
29 交叉引用  

በነጋውም ታላቂቱ ታናሺቱን አለቻት፤ እነሆ ትናንት ከአባቴ ጋር ተኛሁ ዛሬ ሌሊት ደግሞ የወይን ጠጅ እናጠጣው አንቺም ግቢና ከእርሱ ጋር ተኚ ከአባታችንም ዘር እናስቀር።


አሁንም ሂድ፥ ይህንም ሕዝብ ወደ ነገርሁህ ምራ፤ እነሆ መልአኬ በፊትህ ይሄዳል፤ ነገር ግን በምግአበኝበት ቀን ኃጢአታቸውን አመጣባቸዋለሁ አለው።


ከእስረኞች በታች ያጐነብሳሉ፥ ከተገደሉትም በታች ይወድቃሉ። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፥ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።


የፊታቸውም እፍረት ይመሰክርባቸዋል፥ እንደ ሰዶምም ኃጢአታቸውን ያወራሉ፥ አይሠውሩአትም። በራሳቸው ላይ ክፉ ነገርን ሠርተዋልና ለነፍሳቸው ወዮ!


ስለዚህ እግዚአብሔር በስሜ ትንቢት ስለሚናገሩ ነቢያት፦ በዚህች አገር ሰይፍና ራብ አይሆንም ስለሚሉ ስላላክኋቸው ነቢያት እንዲህ ይላል፦ እነዚያ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ።


አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ይገድሉኝ ዘንድ በላዬ የመከሩትን ምክር ሁሉ ታውቃለህ፥ በደላቸውን ይቅር አትበል፥ ኃጢአታቸውንም ከፊትህ አትደምስስ፥ በፊትህም ይውደቁ፥ በቍጣህ ጊዜ እንዲሁ አድርግባቸው።


ስለዚህ መንገዳቸው በጨለማ እንዳለች እንደ ድጥ ስፍራ ትሆንባቸዋለች፥ እነርሱም ፍግምግም ብለው ይወድቁባታል፥ እኔም በምጐበኛቸው ዓመት ክፉ ነገርን አመጣባቸዋለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር።


ስለዚህ ካፊያ ተከለከለ፥ የኋለኛውም ዝናብ ጠፋ፥ የጋለሞታም ሴት ፊት ነበረብሽ፥ ታፍሪም ዘንድ እንቢ ብለሻል።


እስከ ዛሬ ድረስ አልተዋረዱም አልፈሩምም፥ በእናንተና በአባቶቻችሁም ፊት ባኖርሁት ሕጌና ሥርዓቴ አልሄዱም።


በውኑ ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀሥፍምን? ይላል እግዚአብሔር፥ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?


በውኑ ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀሥፍምን? ይላል እግዚአብሔር፥ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?


አስጸያፊ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም፥ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፥ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።


ጥበበኞች አፍረዋል ደንግጠውማል ተማርከውማል፥ እነሆ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ጥለዋል፥ ምን ዓይነት ጥበብ አላቸው?


ገለባም በሌለበት ጭቃ የመረጋችሁትን ቅጥር አፈርሳለሁ ወደ ምድርም እጥለዋለሁ፥ መሠረቱም ይታያል። እርሱም ይናዳል በመካከሉም ትጠፋላችሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።


እነርሱ ፊታቸው የተጨማተረ ልባቸውም የደነደነ ልጆች ናቸው። እኔ ወደ እነርሱ እልክሃለሁ፥ አንተም፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በላቸው።


ደምዋ በውስጥዋ አለ። በተራቈተ ድንጋይ ላይ አደረገችው እንጂ በአፈር ይከደን ዘንድ መሬት ላይ አላፈሰሰችውም፥ መዓቴን አወጣ ዘንድ፥


በቀንም ትሰናከላለህ፥ ነቢዩም ከአንተ ጋር በሌሊት ይሰናከላል፥ እናትህንም አጠፋታለሁ።


የበቀል ወራት መጥቶአል፥ የፍዳም ወራት ደርሶአል፥ እስራኤልም ያውቃል፥ ከኃጢአትህና ከጠላትነትህ ብዛት የተነሣ ነቢዩ ሰንፎአል፥ መንፈስም ያለበት ሰው አብዶአል።


ስለዚህ ሌሊት ይሆንባችኋል እንጂ ራእይ አይሆንላችሁም፥ ጨለማም ይሆንባችኋል እንጂ አታምዋርቱም፥ ፀሐይም በነቢያት ላይ ትገባለች፥ ቀኑም ይጠቁርባቸዋል።


ከእነርሱም ሁሉ የተሻለው እርሱ እንደ አሜከላ ነው፥ ከሁሉም ቅን የሆነው እንደ ኵርንችት ነው፥ ጠባቆችህ የሚጐበኙበት ቀን መጥቶአል፥ አሁን ይሸበራሉ።


እናንተ እፍረት የሌላችሁ ሕዝብ ሆይ፥ ትእዛዝ ሳይወጣ፥ ቀኑም እንደ ገለባ ሳያልፍ፥ የእግዚአብሔርም ቍጣ ትኵሳት ሳይመጣባችሁ፥ የእግዚአብሔርም ቍጣ ቀን ሳይደርስባችሁ ተሰብሰቡ፥ ተከማቹም።


እግዚአብሔር በውስጥዋ ጻድቅ ነው፥ ክፋትን አያደርግም፥ ፍርዱን በየማለዳው ወደ ብርሃን ያወጣል፥ ሳያወጣውም አይቀርም፥ ዓመፀኛው ግን እፍረትን አያውቅም።


በዚያም ቀን ነቢያቱ ሁሉ ትንቢትን ሲናገሩ እያንዳንዱ ስለ ራእዩ ያፍራል፥ ያታልሉም ዘንድ የማቅ ልብስ አይለብሱም።


ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ አለ።


መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው።


跟着我们:

广告


广告