Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 6:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ይሰሙኝስ ዘንድ ለማን እናገራለሁ? ለማንስ አስጠነቅቃለሁ? እነሆ፥ ጆሮአቸው ያልተገረዘች ናት ለመስማትም አይችሉም፥ እነሆ፥ የእግዚአብሔር ቃል ለስድብ ሆኖባቸዋል፥ ደስም አያሰኛቸውም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ለማን ልናገር? ማንን ላስጠንቅቅ? ማንስ ይሰማኛል? እነሆ፣ ጆሮዎቻቸው አልተገረዙምና፣ መስማት አይችሉም። በእግዚአብሔር ቃል ይሣለቃሉ፤ ደስም አይሰኙበትም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እንዲሰሙኝስ ለማን እናገራለሁ? ለማንስ አስጠነቅቃለሁ? እነሆ፥ ጆሮአቸው ያልተገረዘ ነው፥ መስማትም አይችሉም፤ እነሆ፥ የጌታ ቃል ለስድብ ሆኖባቸዋል፥ ደስም አያሰኛቸውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እኔም መልሼ እንዲህ አልኩ፦ “እኔ ብነግራቸውና ባስጠነቅቃቸው ማን ሊሰማኝ ይችላል? እነርሱ እልኸኞች ስለ ሆኑ፥ ቃልህን መስማት አይፈልጉም፤ የአንተን ቃል ስነግራቸው በንቀት መሳቂያ ያደርጉኛል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ይሰ​ሙ​ኝስ ዘንድ ለማን እና​ገ​ራ​ለሁ? ለማ​ንስ አዳ​ኛ​ለሁ? እነሆ፥ ጆሮ​አ​ቸው ያል​ተ​ገ​ረ​ዘች ናት፤ ለመ​ስ​ማ​ትም አይ​ች​ሉም፤ እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ለስ​ድብ ሆኖ​ባ​ቸ​ዋል፥ ይሰ​ሙት ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ዱ​ምና።

参见章节 复制




ኤርምያስ 6:10
40 交叉引用  

ሙሴም በእግዚአብሔር ፊት፥ “እነሆ የእስራኤል ልጆች አልሰሙኝም፤ እንዴትስ ፈርዖን ይሰማኛል? ይልቁንም እኔ ከንፈረ ቈላፍ ነኝ” ብሎ ተናገረ።


ብዙ ነገርን ታያላችሁ ነገር ግን አትጠባበቁትም፥ ጆሮአችሁም ተከፍተዋል፥ ነገር ግን አትሰሙም።


የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል?


የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሂድና ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለሚቀመጡ ተናገር እንዲህም በላቸው፦ ቃሌን ትሰሙ ዘንድ ተግሣጽን አትቀበሉምን? ይላል እግዚአብሔር።


እናንተም የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሆይ፥ ስለ ሥራችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳያቃጥል፥ ለእግዚአብሔር ተገረዙ፥ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ።


እናንተ ሰነፎች ልበ ቢሶች፥ ዓይን እያላችሁ የማታዩ፥ ጆሮም እያላችሁ የማትሰሙ ሕዝብ ሆይ፥ ይህን ስሙ።


አሁንም ይህን ነገር ሁሉ ስላደረጋችሁ፥ በማለዳም ተነሥቼ በተናገርኋችሁ ጊዜ ስላልሰማችሁ፥ በጠራኋችሁም ጊዜ ስላልመለሳችሁ፥


ነገር ግን አንገታቸውን አደነደኑ እንጂ አልሰሙኝም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም፥ አባቶቻቸውም ካደረጉት ይልቅ የባሰ አደረጉ።


ነገር ግን የእስራኤል ቤት ሁሉ የጠነከረ ግምባርና የደነደነ ልብ አላቸውና፥ እኔንም መስማት እንቢ ብለዋልና የእስራኤል ቤት አንተን አይሰሙም።


እርሱም በምድር ላይ የመጣውን ሰይፍ ባየ ጊዜ መለከትን ቢነፋ ሕዝቡንም ቢያስጠነቅቅ፥


ነገር ግን ከመንገዱ ይመለስ ዘንድ ኃጢአተኛውን ብታስጠነቅቀው እርሱም ከመንገዱ ባይመለስ፥ በኃጢአቱ ይሞታል አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል።


የቤቴልም ካህን አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዮርብዓም ልኮ፦ አሞጽ፦ ኢዮርብዓም በሰይፍ ይሞታል፥ እስራኤልም ከአገሩ ተማርኮ ይሄዳል ብሎአልና አሞጽ በእስራኤል ቤት መካከል ዐምፆብሃል፥ ምድሪቱም ቃሉን ሁሉ ልትሸከም አትችልም አለ።


ዳሩ ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው፦ እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ?


ከሕግ አዋቂዎችም አንዱ መልሶ፦ መምህር ሆይ፥ ይህን ማለትህ እኛን ደግሞ መስደብህ ነው አለው።


የካህናት አለቆችና ጻፎችም ይህን ምሳሌ በእነርሱ ላይ እንደ ተናገረ አውቀው በዚያች ሰዓት እጃቸውን ሊጭኑበት ፈለጉ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ።


ዓለም እናንተን ሊጠላ አይቻለውም፤ እኔ ግን ሥራው ክፉ መሆኑን እመሰክርበታለሁና እኔን ይጠላኛል።


ከፈሪሳውያንም ከእርሱ ጋር የነበሩት ይህን ሰምተው፦ “እኛ ደግሞ ዕውሮች ነንን?” አሉት።


እናንተ አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሮአችሁም ያልተገረዘ፥ እናንተ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፤ አባቶቻችሁ እንደ ተቃወሙት እናንተ ደግሞ።


ተንበርክኮም፦ “ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ። ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር።


በውስጡ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛልና፥


እግዚአብሔር ግን አስተዋይ ልብ፥ የሚያዩ ዓይኖች፥ የሚሰሙም ጆሮች እስከ ዛሬ ድረስ አልሰጣችሁም።


እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው፤


ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሡበት ዘመን ይመጣልና፤ ነገር ግን ጆሮቻቸውን የሚያሳክክ ስለ ሆነ፥ እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ።


ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፥ በዚህም ዓለምን ኵኦነነ፥ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።


跟着我们:

广告


广告