Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 52:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ከፊቱም አውጥቶ እስኪጥላቸው ድረስ ይህ በእግዚአብሔር ቍጣ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሆኖአልና፥ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እንግዲህ ይህ ሁሉ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሊደርስ የቻለው ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ነበር፤ በመጨረሻም ከፊቱ አስወገዳቸው። በዚህ ጊዜ ሴዴቅያስ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በእርግጥ ከጌታ ቁጣ የተነሣ ከፊቱ አውጥቶ እስኪጥላቸው ድረስ ይህ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሆነ፤ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ስለዚህም እግዚአብሔር በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሕዝብ ላይ ተቈጥቶ ከፊቱ አስወገዳቸው። ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ከፊ​ቱም አው​ጥቶ እስ​ኪ​ጥ​ላ​ቸው ድረስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ላይ ሆኖ​አ​ልና፤ ሴዴ​ቅ​ያ​ስም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 52:3
19 交叉引用  

እነሆ ዛሬ ከምድር ፊት አሳደድኽኝ፤ ከፊትህም እሰወራለሁ፤ በምድርም ላይ ኮብላይና ተቅበዝባዥ እሆናለሁ፤ የሚያገኘንም ሁሉ ይገድለኚል።


ቃየንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ ከዔድንም ወደ ምሥራቅ በኖድ ምድር ተቀመጠ።


ደግሞም የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ ዳዊትም፦ ሂድ፥ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር ብሎ በላያቸው አስነሣው።


አንተን የወደደ፥ በእስራኤልም ዙፋን ያስቀመጠህ አምላክ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን! እግዚአብሔር እስራኤልን ለዘላለም ወድዶታልና፥ ስለዚህ ጽድቅና ፍርድ ታደርግ ዘንድ ንጉሥ አድርጎ አስነሣህ።”


ስለዚህም እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ እጅግ ተቈጣ፤ ከፊቱም ጣላቸው፤ ከይሁዳም ነገድ ብቻ በቀር ማንም አልቀረም።


እግዚአብሔርም የእስራኤልን ዘር ሁሉ ጠላ፤ አስጨነቃቸውም፤ ከፊቱም እስኪጥላቸው ድረስ በበዝባዦች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው።


ከፊቱ አውጥቶ እስኪጥላቸው ድረስ ይህ ነገር በእግዚአብሔር ቍጣ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሆኖአልና፤ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።


ደግሞም በእግዚአብሔር አምሎት በነበረው በንጉሡ በናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ፤ ወደ እስራኤልም አምላክ ወደ እግዚአብሔር እንዳይመለስ አንገቱን አደነደነ ልቡንም አጠነከረ።


በአባቶችህ ታሪክ መጽሐፍ ምርመራ ይደረግ፤ በዚያም በታሪክ መጽሐፍ ይህች ከተማ ዓመፀኛ እንደ ሆነች፥ ነገሥታትንና አውራጃዎችንም እንደ ጐዳች፥ ከጥንቱም ሽፍትነት በእርስዋ እንደ ተጀመረ ታገኛለህ፤ ታውቃለህም፤ ስለዚህም ይህች ከተማ ፈርሳ ነበር።


ንጉሥሽ ሕፃን የሆነ፥ መኳንንቶችሽም ማልደው የሚበሉ፥ አንቺ አገር ሆይ፥ ወዮልሽ!


ግብጻውያንንም በጨካኝ ጌታ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ ጨካኝ ንጉሥም ይገዛቸዋል ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


እነሆ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ድጋፍንና ብርታትን፥ የእንጀራን ድጋፍ ሁሉ የውሃውንም ድጋፍ ሁሉ፥


እኔ፦ ለሰልፍ የሆነው ምክርህና ኃይልህ ከንቱ ነገር ነው አልሁ፥ አሁንም በእኔ ላይ ያመፅኸው በማን ተማምነህ ነው?


እግዚአብሔርም እንደዚህ አለኝ፦ ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አይዘነብልም፥ ከፊቴ ጣላቸው፥ ይውጡ።


የኤፍሬምንም ዘር ሁሉ፥ ወንድሞቻችሁን ሁሉ እንደ ጣልሁ፥ እንዲሁ ከፊቴ እጥላችኋለሁ።


跟着我们:

广告


广告