Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 51:51 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

51 ስድብን ስለ ሰማን አፍረናል፥ ባዕዳን ሰዎችም ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ገብተዋልና ነውር ፊታችንን ከድኖታል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

51 “ባዕዳን ሰዎች ወደ ተቀደሰው፣ ወደ እግዚአብሔር ቤት ስለ ገቡ፣ እኛ ተሰድበናል፤ ዕፍረትም ፊታችንን ሸፍኗል፤ ውርደትም ተከናንበናል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

51 ስድብን ስለ ሰማን አፍረናል፤ ባዕዳን ሰዎችም በጌታ ቤት ውስጥ ወዳሉት ወደ ተቀደሱ ስፍራዎች ገብተዋልና ውርደት ፊታችንን ሸፍኖታል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

51 ‘ስለ ተሰደብን አፈርን፤ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ወደ ተቀደሱ ስፍራዎች ባዕዳን ሰዎች ስለ ገቡ ተዋርደን አንገታችንን ደፋን።’ በሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

51 ስድ​ባ​ች​ንን ስለ ሰማን አፍ​ረ​ናል፤ ባዕ​ዳን ሰዎ​ችም ወደ ቤተ መቅ​ደ​ሳ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ገብ​ተ​ዋ​ልና ውር​ደት ፊታ​ች​ንን ከድ​ኖ​ታል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 51:51
37 交叉引用  

የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ያየው ስለ ባቢሎን የተናገረ ሸክም።


እግዚአብሔርም ያዕቆብን ይምረዋል፥ እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል፥ በአገራቸውም ያኖራቸዋል፥ መጻተኛም ከእርሱ ጋር ይተባበራል፥ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጣበቃል።


በባሕር አጠገብ ስላለው ስለ ምድረ በዳ የተነገረ ሸክም። ዐውሎ ነፋስ ከደቡብ እንደሚወጣ፥ እንዲሁ ከሚያስፈራ አገር ከምድረ በዳ ይወጣል።


አንቺ ድንግል የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ በትቢያም ላይ ተቀመጪ፥ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ ከዚህ በኋላ ቅልጣናምና ቅምጥል አትባይምና ያለ ዙፋን በመሬት ላይ ተቀመጪ።


ታላላቆችም ብላቴኖቻቸውን ወደ ውኃ ሰደዱ፥ ወደ ጕድጓድ መጡ ውኃም አላገኙም፥ ዕቃቸውንም ባዶውን ይዘው ተመለሱ፥ አፈሩም ተዋረዱም ራሳቸውንም ተከናነቡ።


የሜዶን ነገሥታትንም ሁሉ፥ የቀረቡና የራቁ፥ አንዱ ከሌላው ጋር ያሉ የሰሜን ነገሥታትንም ሁሉ፥ በምድር ፊት ላይ ያሉ የዓለም መንግሥታትንም ሁሉ አጠጣኋቸው፥ የሼሻክም ንጉሥ ከእነርሱ በኋላ ይጠጣል።


ከተመለስሁ በኋላ ተጸጸትሁ፥ ከተገሠጽሁም በኋላ ጭኔን ጸፋሁ፥ የብላቴንነቴንም ስድብ ተሸክሜአለሁና አፈርሁ፥ ተዋረድሁም ብሎ ሲያለቅስ ሰማሁ።


የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት አቃጠለ፥ የኢየሩሳሌምንም ቤቶች ሁሉ፥ ታላላቆችን ቤቶች ሁሉ፥ በእሳት አቃጠለ።


ዮድ። አስጨናቂው በከበረ ነገርዋ ሁሉ ላይ እጁን ዘረጋ፥ ወደ ጉባኤህ እንዳይገቡ ያዘዝሃቸው አሕዛብ ወደ መቅደስዋ ሲገቡ አይታለችና።


ሬስ። አቤቱ፥ እይ፥ በማን ላይ እንደዚህ እንዳደረግህ ተመልከት። በውኑ ሴቶች ፍሬያቸውን፥ ያቀማጠሉአቸውን ሕፃናት፥ ይበላሉን? በውኑ ካህኑና ነቢዩ በጌታ መቅደስ ውስጥ ይገደላሉን?


አቤቱ፥ የሆነብንን አስብ፥ ተመልከት ስድባችንንም እይ።


ለእስራኤል ቤት ተናገር እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የኃይላችሁን ትምክሕት፥ የዓይናችሁን አምሮት፥ የነፍሳችሁን ምኞት መቅደሴን አረክሳለሁ፥ ያስቀራችኋቸውም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።


ደግሞም የራብን ስድብ ከአሕዛብ ዘንድ እንዳትሸከሙ የዛፍን ፍሬና የእርሻውን ቡቃያ አበዛለሁ።


ማቅም ይለብሳሉ ድንጋጤም ይሸፍናቸዋል፥ በፊትም ሁሉ ላይ እፍረት ይሆናል፥ ራሳቸውንም ሁሉ ይነጩታል።


እርሱም፦ ቤቱን አርክሱ፥ በተገደሉትም ሰዎች አደባባዮችን ሙሉ ውጡ አላቸው። እነርሱም ወጥተው በከተማይቱ ገደሉ።


ከእርሱም ጋር ሠራዊቶች ይቆማሉ፥ መቅደሱንም ግንቡንም ያረክሳሉ፥ የዘወትሩንም መሥዋዕት ያስቀራሉ፥ የጥፋትንም ርኵሰት ያቆማሉ።


የይስሐቅም የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፥ የእስራኤልም መቅደሶች ባድማ ይሆናሉ፥ በኢዮርብዓምም ቤት ላይ በሰይፍ እነሣለሁ አለ።


አንተን ለጥፋት፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ለማፍዋጫ እሰጥ ዘንድ የዘንበሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቃችኋል፥ በምክራቸውም ሄዳችኋል፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።


ጠላቴም ታያለች፥ እኔንም፦ አምላክህ እግዚአብሔር ወዴት ነው? ያለች በእፍረት ትከደናለች።


跟着我们:

广告


广告