Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 51:22 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 በአንቺም ሰረገላውንና በላዩ የሚቀመጠውን እሰባብራለሁ፥ በአንቺም ወንድንና ሴትን እሰባብራለሁ፥ በአንቺም ሽማግሌውንና ብላቴናውን እሰባብራለሁ፥ በአንቺም ጐልማሳውንና ቆንጆይቱን እሰባብራለሁ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 በአንቺ ወንዱንና ሴቱን እሰባብራለሁ፤ በአንቺ ሽማግሌውንና ወጣቱን እሰባብራለሁ። በአንቺ ጐረምሳውንና ኰረዳዪቱን እሰባብራለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 በአንቺም ወንድንና ሴትን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም ሽማግሌውንና ብላቴናውን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም ጐልማሳውንና ድንግሊቱን እሰባብራለሁ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 በአንቺ ሴቶችንና ወንዶችን ሽማግሌውንና ወጣቱን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ሰባብሬአለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 በአ​ን​ቺም ወን​ድና ሴትን እበ​ት​ና​ለሁ፤ በአ​ን​ቺም ሽማ​ግ​ሌ​ው​ንና ብላ​ቴ​ና​ውን እበ​ት​ና​ለሁ፤ በአ​ን​ቺም ጐል​ማ​ሳ​ው​ንና ቆን​ጆ​ዪ​ቱን እበ​ት​ና​ለሁ፤

参见章节 复制




ኤርምያስ 51:22
14 交叉引用  

ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጕልማሶቻቸውን በቤተመቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ ጕልማሳውንና ቈንጆይቱን ሽማግሌውንና አሮጌውን አልማረም፤ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።


የተገኘ ሁሉ የተወጋ ይሆናል፥ የተያዘም ሁሉ በሰይፍ ይወድቃል።


ሕፃናቶቻቸውም በፊታቸው ይጨፈጨፋሉ፥ ቤቶቻቸውም ይበዘበዛሉ፥ ሚስቶቻቸውም ይነወራሉ።


ፍላጾቻቸውም ጎበዞችን ይጨፈጭፋሉ፥ የማኅፀንንም ፍሬ አይምሩም፥ ዓይኖቻቸውም ለሕፃናት አይራሩም።


እንዲሁ የአሦር ንጉሥ የግብጽንና የኢትዮጵያን ምርኮ፥ ጐበዛዝቱንና ሽማግሌዎቹን፥ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ ገላቸውንም ገልጦ፥ ለግብጽ ጕስቍልና ይነዳቸዋል።


አሁንም የእስራኤል አምላክ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከይሁዳ ወገን ቅሬታ እንዳይቀርላችሁ፥ ወንድንና ሴትን፥ ብላቴናንና ሕፃንን ከመካከላችሁ ታጠፉ ዘንድ ይህን ታላቅ ክፋት በራሳችሁ ላይ ለምን ታደርጋላችሁ?


ሰይፍ በፈረሶቻቸውና በሰረገሎቻቸው ላይ በመካከልዋም ባሉት በልዩ በልዩ ሕዝብ ሁሉ ላይ አለ፥ እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ፥ ሰይፍም በመዝገብዋ ላይ አለ ለብዝበዛም ይሆናል።


በአንቺም እረኛውንና መንጋውን እሰባብራለሁ፥ በአንቺም አራሹንና ጥማጁን እሰባብራለሁ፥ በአንቺም አለቆችንና ሹማምቶችን አሰባብራለሁ።


ስለዚህ በእግዚአብሔር ቍጣ ተሞልቻለሁ፥ ከመታገሥ ደክሜአለሁ፥ በሜዳ በሕፃናት ላይ በጕልማሶችም ጉባዔ ላይ በአንድነት አፍስሰው፥ ባል ከሚስቱ ጋር ሽማግሌውም ከጎበዙ ጋር ይያያዛልና።


ካፍ። ሕፃኑና ጡት የሚጠባው በከተማይቱ ጐዳና ላይ ሲዝሉ፥ ዓይኔ በእንባ ደከመች፥ አንጀቴም ታወከ፥ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥቃጤ ጉበቴ በምድር ላይ ተዘረገፈ።


ሳን። ብላቴናውና ሽማግሌው በመንገዶች ላይ ተጋደሙ፥ ደናግሎቼና ጐበዛዝቴ በሰይፍ ወድቀዋል፥ በቍጣህ ቀን ገደልሃቸው፥ ሳትራራ አረድሃቸው።


ሽማግሌውንና ጐበዙን ቈንጆይቱንም ሕፃናቶቹንና ሴቶቹን ፈጽማችሁ ግደሉ፥ ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ፥ በመቅደሴም ጀምሩ አላቸው። በቤቱም አንጻር ባሉ ሽማግሌዎች ጀመሩ።


ጉልማሳውን ከድንግል፥ ሕፃኑንም ከሽማግሌ ጋር፥ 2 በሜዳ ሰይፍ፥ በቤትም ውስጥ ድንጋጤ ያጠፋቸዋል።


አሁንም ሄደህ አማሌቅን ምታ፥ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፥ አትማራቸውም፥ ወንዱንና ሴቱን ብላቴናውንና ሕፃኑን በሬውንና በጉን ግመሉንና አህያውን ግደል።


跟着我们:

广告


广告