Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 51:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ድምጹን ባሰማ ጊዜ ውኆች በሰማይ ይታወካሉ፥ ከምድርም ዳር ደመናትን ከፍ ያደርጋል፥ ለዝናብም መብረቅን ያደርጋል፥ ነፋስንም ከቤተ መዛግብቱ ያወጣል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ድምፁን ባንጐደጐደ ጊዜ በሰማይ ውሆች ይናወጣሉ፤ ጉሙን ከምድር ዳርቻ ወደ ላይ እንዲወጣ ያደርገዋል፤ መብረቅን ከዝናብ ጋራ ይልካል፤ ነፋስንም ከግምጃ ቤቱ ያወጣል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ድምጹን ባሰማ ጊዜ ውኆች በሰማይ ይታወካሉ፥ ከምድርም ዳር ደመናትን ከፍ ያደርጋል፤ ለዝናብም መብረቅን ያደርጋል፥ ነፋስንም ከቤተ መዛግብቱ ያወጣል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 በሰማይ ያለው ውሃ በእርሱ ትእዛዝ ይናወጣል፤ እርሱ ደመናትን ከምድር ዳርቻ ያመጣል፤ ከዝናብ ጋርም መብረቅ እንዲበርቅ ያደርጋል፤ ከማከማቻው በማውጣት ነፋስ እንዲነፍስ ያደርጋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ድም​ፁን ባሰማ ጊዜ ውኆች በሰ​ማይ ይታ​ወ​ካሉ፤ ከም​ድ​ርም ዳር ደመ​ና​ትን ያወ​ጣል፤ ለዝ​ና​ብም ጊዜ መብ​ረ​ቅን ያደ​ር​ጋል፤ ነፋ​ስ​ንም ከቤተ መዛ​ግ​ብቱ ያወ​ጣል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 51:16
24 交叉引用  

እግዚአብሔርም ኖኅን፤ በመርከብም ከእርሱ ጋር የነበረውን አራዋቱን ሁሉ፤ እንስሳውንም ሁሉ አሰበ።


በውኑ ወደ በረዶው ቤተ መዛግብት ገብተሃልን? የበረዶውንስ ቅንጣት ቤተ መዛግብት አይተሃልን?


እንደ እግዚአብሔር ክንድ ያለ ክንድ አለህን? ወይስ እንደ እርሱ ባለ ድምፅ ታንጐደጕዳለህን?


ሙሴም በግብፅ አገር ላይ በትሩን ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም የምሥራቅን ነፋስ ያን ቀን ሁሉና ሌሊቱን ሁሉ አመጣ፤ ማለዳም በሆነ ጊዜ የምሥራቁ ነፋስ አንበጣዎቹን አመጣ።


እግዚአብሔርም ከምዕራብ ዐውሎ ነፋሱን አስወገደ፤ አንበጣዎቹንም ወስዶ በኤርትራ ባሕር ውስጥ ጣላቸው፤ አንድ አንበጣም በግብፅ ዳርቻ ሁሉ አልቀረም።


ሙሴም በባሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ሌሊቱን ሁሉ ጽኑ የምሥራቅ ነፋስ አምጥቶ ባሕሩን አስወገደው፤ ባሕሩንም አደረቀው፤ ውኃውም ተከፈለ።


ሁሉንም የሚችል አምላክ እንደሚናገረው ያለ ጽምፅ እንዲሁ የኪሩቤል ክንፎች ድምፅ እስከ ውጭው አደባባይ ድረስ ተሰማ።


የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር። እስራኤልን ከግብጽ ምድር፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?


跟着我们:

广告


广告