Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 50:12 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እናታችሁ እጅግ ታፍራለች፥ የወለደቻችሁም ትጐሰቍላለች፥ እነሆ፥ በአሕዛብ መካከል ኋለኛይቱ ትሆናለች፥ ምድረ በዳና ደረቅ ምድር በረሀም ትሆናለች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እናታችሁ እጅግ ታፍራለች፤ የወለደቻችሁም ትዋረዳለች። እርሷም ምድረ በዳ፣ ደረቅ ምድርና በረሓ፣ ከመንግሥታትም ሁሉ ያነሰች ትሆናለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እናታችሁ እጅግ ታፍራለች፥ የወለደቻችሁም ትዋረዳለች፤ እነሆ፥ በአሕዛብ መካከል ኋለኛይቱ ትሆናለች፤ ምድረ በዳና ደረቅ ምድር በረሀም ትሆናለች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 አሁን ግን ታላቂቱ ከተማችሁ በጣም ታፍራለች፤ እናት አገራችሁም ትዋረዳለች፤ ከመንግሥታት ሁሉ ያነሰች ትሆናለች። ውሃ የማይገኝባት ሆና ወደ ምድረ በዳነት ትለወጣለች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እና​ታ​ችሁ እጅግ ታፍ​ራ​ለች፤ የወ​ለ​ደ​ቻ​ች​ሁም ትጐ​ሰ​ቍ​ላ​ለች፤ እነሆ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ኋለ​ኛ​ዪቱ ትሆ​ና​ለች፤ ምድረ በዳና ደረቅ ምድር፥ በረ​ሀም ትሆ​ና​ለች።

参见章节 复制




ኤርምያስ 50:12
17 交叉引用  

በእነርሱ ላይ እነሣለሁ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ከባቢሎን ስምንና ቅሬታን፥ ዘርንና ትውልድንም እቈርጣለሁ ይላል እግዚአብሔር።


እነሆ፥ የከለዳውያን አገር! ይህ ሕዝብ ሆኖ አይገኝም፥ አሦራውያን ለምድረ በዳ አራዊት ሰጥተውታል፥ ግንቦቻቸውን ሠሩ፥ አዳራሾችዋንም አፈረሱ፥ ባድማም አደረጓት።


እግዚአብሔር ለሕዝቤ ለእስራኤል ያወረስሁትን ርስት ለሚነኩት ክፉዎች ጐረቤቶች ሁሉ እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፥ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅለዋለሁ።


ሰባት የወለደች ደክማለች፥ ነፍስዋንም አውጥታለች፥ ቀን ገና ሳለ ፀሐይዋ ገብታባታለች፥ አፍራለች ተዋርዳማለች፥ የተረፉትንም በጠላቶቻቸው ፊት ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣለሁ።


እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ቤት እንዲህ ይላልና፦ አንተ በእኔ ዘንድ እንደ ገለዓድና እንደ ሊባኖስ ራስ ነህ፥ ነገር ግን በእርግጥ ምድረ በዳ ማንም የማይቀመጥባቸውም ከተሞች አደርግሃለሁ።


ሰባው ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ፥ የባቢሎንን ንጉሥና ያንን ሕዝብ ስለ ኃጢአታቸው እቀጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የከለዳውያንንም ምድር ለዘላለም ባድማ አደርጋታለሁ።


የሜዶን ነገሥታትንም ሁሉ፥ የቀረቡና የራቁ፥ አንዱ ከሌላው ጋር ያሉ የሰሜን ነገሥታትንም ሁሉ፥ በምድር ፊት ላይ ያሉ የዓለም መንግሥታትንም ሁሉ አጠጣኋቸው፥ የሼሻክም ንጉሥ ከእነርሱ በኋላ ይጠጣል።


ስለዚህ፥ እነሆ፥ በአሞን ልጆች ከተማ በረባት ላይ የሰልፍ ውካታን የማሰማበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የፍርስራሽ ክምርም ትሆናለች፥ ሴቶች ልጆችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፥ እስራኤልም የወረሱትን ይወርሳል፥ ይላል እግዚአብሔር።


ከተሞችዋ ባድማና ደረቅ ምድር ምድረ በዳም፥ ሰውም የማይቀመጥበት የሰውም ልጅ የማያልፍበት ምድር ሆኑ።


ስለዚህ፥ እነሆ፥ የተቀረጹትን የባቢሎን ምስሎች የምቀጣበት ዘመን ይመጣል፥ ምድርዋም ሁሉ ታፍራለች፥ ተወግተውም የሞቱት ሁሉ በመካከልዋ ይወድቃሉ።


ላይኛይቱ ኢየሩሳሌም ግን በነጻነት የምትኖር ናት እርስዋም እናታችን ናት።


በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም፦ ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት ተብሎ ተጻፈ።


跟着我们:

广告


广告