Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 5:18 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ነገር ግን በዚያ ዘመን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ፈጽሜ አላጠፋችሁም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 “ይሁን እንጂ፣ በዚያ ዘመን እንኳ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ፈጽሜ አላጠፋችሁም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ነገር ግን በዚያ ዘመን፥ ይላል ጌታ፥ ፈጽሜ አላጠፋችሁም።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይህም ሁሉ ሲሆን በእነዚያ ቀኖች እንኳ ሕዝቤን ጨርሼ አላጠፋም፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ነገር ግን “በዚያ ዘመን ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ፈጽሜ አላ​ጠ​ፋ​ች​ሁም።”

参见章节 复制




ኤርምያስ 5:18
10 交叉引用  

አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና፥ ይላል እግዚአብሔር፥ አንተንም የበተንሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፥ በመጠን እቀጣሃለሁ፥ ያለ ቅጣትም ከቶ አልተውህም።


እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ምድር ሁሉ ባድማ ትሆናለች፥ ነገር ግን ፈጽሜ አላጠፋትም።


ወደ ቅጥርዋ ወጥታችሁ አፍርሱ፥ ነገር ግን ፈጽማችሁ አታጥፉ፥ ለእግዚአብሔር አይደሉምና ቅርንጫፍዋን ውሰዱ።


መከርህንና እንጀራህን ይበላሉ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህንም ይበሉአቸዋል፥ በጎችህንና ላሞችህንም ይበላሉ፥ ወይንህንና በለስህንም ይበላሉ፥ የምትታመናቸውን የተመሸጉ ከተሞችን በሰይፍ ይደበድባሉ።


እንዲህም ይሆናል፥ እናንተ፦ አምላካችን እግዚአብሔር ይህን ነገር ሁሉ ስለምን አደረገብን? ብትሉ፥ አንተ፦ እንደ ተዋችሁኝ በአገራችሁም ሌሎችን አማልክት እንዳመለካችሁ፥ እንዲሁ ለእናንተ ባልሆነ አገር ለሌሎች ሰዎች ትገዛላችሁ ትላቸዋለህ።


ትንቢትንም በተናገርሁ ጊዜ የበናያስ ልጅ ፈላጥያ ሞተ፥ እኔም በግምባሬ ተደፍቼ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! በውኑ የእስራኤልን ቅሬታ ፈጽመህ ታጠፋለህን? ብዬ በታላቅ ድምፅ ጮኽሁ።


ነገር ግን ዓይኔ ራራችላቸው እኔም አላጠፋኋቸውም፥ በምድረ በዳም ፈጽሜ አልፈጀኋቸውም።


ሲገድሉም እኔ ብቻዬን ቀርቼ ሳለሁ በግምባሬ ተደፍቼ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! መዓትህን በኢየሩሳሌም ላይ ስታፈስስ የእስራኤልን ቅሬታ ሁሉ ታጠፋለህን? ብዬ ጮኽሁ።


አቤቱ፥ የተቀደስህ አምላኬ ሆይ፥ አንተ ከዘላለም ጀምሮ አልነበርህምን? እኛ አንሞትም፥ አቤቱ፥ ለፍርድ ሠርተኸዋል፥ ለተግሣጽም አድርገኸዋል።


跟着我们:

广告


广告