Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 49:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ስለ ኤዶምያስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውኑ በቴማን ጥበብ የለምን? ከብልሃተኞችስ ምክር ጠፍቶአልን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ስለ ኤዶም፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ጥበብ ከቴማን ጠፍቷልን? ምክር ከአስተዋዮች ርቋልን? ጥበባቸውስ ተሟጧልን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ስለ ኤዶምያስ፤ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “በውኑ በቴማን ጥበብ የለምን? ከብልሃተኞችስ ምክር ጠፍቶአልን? ጥበባቸውስ አልቆአልን?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶም የተናገረው ይህ ነው፦ “የቴማን ከተማ ሕዝብ ከዚህ በፊት የነበራቸውን ጥበብ አጥተዋልን? አማካሪዎቻቸውስ ምክር መስጠት አቅቷቸዋልን? የነበራቸውስ ጥበብ የት ደረሰ?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ስለ ኤዶ​ም​ያስ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በውኑ በቴ​ማን ጥበብ የለ​ምን? ከብ​ል​ሃ​ተ​ኞ​ችስ ምክር ጠፍ​ቶ​አ​ልን? ጥበ​ባ​ቸ​ውስ አል​ቆ​አ​ልን?

参见章节 复制




ኤርምያስ 49:7
39 交叉引用  

ዔሳውም ያዕቆብን፦ ከዚህ ከቀዩ ወጥ አብላኝ እኔ እጅግ ደክሜአለሁና አለው ስለዚህ ስሙ ኤዶም ተባለ።


ዔሳው፥ አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት ዔሳውም በልቡ አለ፦ ለአባቴ የልቅሶ ቀን ቀርቦአል ከዚያም በኍላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።


ያዕቆብም ወደ ወንድሙ ወደ ዔሳው ወደ ሴይር ምድር ወደ ኤዶም አገር ከፊቱ መልእክተኞችን ላከ፤


የኤልፋዝም ልጆች እንዚህ ናቸው፤ ቴማን አማር፥ ስፎ፥ ጎቶም፥ ቄኔዝ።


የዔሳው ልጆች አለቆች እነዚህ ናቸው ለዔሳው የበኵር ለኤፋዝ ልጆች ቴማን አለቃ እማር አለቃ ስፎ አለቃ ቄኔዝ አለቃ


በስፍራውም የቴማኒው አገር ሑሳም ነገሠ


ዔሳውም በሴይር ተራራ ተቀመጠ ዔሳውም ኤዶም ነው።


አልእቃ ቄኔዝ፥ አለቃ ቴማን፥ አለቃ ሚብሳር፥


ሦስቱም የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየአገራቸው መጡ፥ እነርሱም ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው በልዳዶስ፥ ነዕማታዊው ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊያዝኑለትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ ለመምጣት ተስማሙ።


ቴማናዊውም ኤልፋዝ መለሰ እንዲህም አለ፦


ስለ ኤዶሚያስ የተነገረ ሸክም። አንዱ ከሴይር፦ ጕበኛ ሆይ፥ ሌሊቱ ምን ያህል ነው? ጕበኛ ሆይ፥ ሌሊቱ ምን ያህል ነው? ብሎ ጠራኝ።


ስለዚህ፥ እነሆ፥ ድንቅ ነገርን በዚህ ሕዝብ መካከል፥ ድንቅ ነገርን ተአምራትንም፥ እንደ ገና አደርጋለሁ፥ የጥበበኞችም ጥበብ ትጠፋለች፥ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትሰወራለች።


እግዚአብሔር ለሕዝቤ ለእስራኤል ያወረስሁትን ርስት ለሚነኩት ክፉዎች ጐረቤቶች ሁሉ እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፥ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅለዋለሁ።


እነርሱም፦ ሕግ ከካህን፥ ምክርም ከጠቢብ፥ ቃልም ከነቢይ አይጠፋምና ኑ፥ በኤርምያስ ላይ አሳብን እናስብ። ኑ፥ በምላስ እንምታው፥ ቃሉንም ሁሉ አናድምጥ አሉ።


ኤዶምያስንም፥ ሞዓብንም፥ የአሞንም ልጆች፥


ድዳንንም፥ ቴማንንም፥ ቡዝንም፥ ጠጕራቸውንም የሚቈርጡትን ሁሉ፥


ልኬ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ ባሪያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፥ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፥ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፥ ለመደነቂያና ለማፍዋጫም ለዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።


ስለዚህ እግዚአብሔር በኤዶምያስ ላይ የመከረባትን ምክር፥ በቴማንም በሚኖሩ ሰዎች ላይ ያሰባትን አሳብ ስሙ፥ በእውነት የመንጋ ትንንሾች ይጐተታሉ፥ በእውነት ማደሪያቸውን ባድማ ያደርግባቸዋል።


ጥበበኞች አፍረዋል ደንግጠውማል ተማርከውማል፥ እነሆ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ጥለዋል፥ ምን ዓይነት ጥበብ አላቸው?


ሳን። በዖፅ ምድር የምትኖሪ የኤዶምያስ ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበልሽ ሐሤትም አድርጊ፥ ጽዋው ደግሞ ወደ አንቺ ያልፋል፥ አንቺም ትሰክሪአለሽ ትራቈቻለሽም።


ኤዶምያስና ነገሥታቶችዋ አለቆችዋም ሁሉ በዚያ አሉ፥ በሰይፍ ከተገደሉት ጋር በኃይላቸው ተኝተዋል፥ ካልተገረዙትና ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ይተኛሉ።


ወደ መልካሚቱም ምድር ይገባል፥ ብዙ አገሮችም ይወድቃሉ፥ ነገር ግን ኤዶምያስና ሞዓብ ከአሞንም ልጆች የበለጡት ከእጁ ይድናሉ።


በአገራቸው ንጹሑን ደም አፍስሰዋልና በይሁዳ ልጆች ላይ ስላደረጉት ግፍ ግብጽ ምድረ በዳ፥ ኤዶምያስም በረሃ ይሆናል።


እግዚአብሔር ከቴማን፥ ቅዱሱም ከፋራን ተራራ ይመጣል። ክብሩ ሰማያትን ከድኖአል፥ ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል።


ኤዶማዊ ወንድምህ ነውና አትጸየፈው፤ ግብፃዊውንም በአገሩ ስደተኛ ነበርህና አትጸየፈው።


跟着我们:

广告


广告