Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 49:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እነሆ፥ በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ ዘንድ ፍርሃትን አመጣብሻለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እያንዳንዳችሁም በፊታችሁ ወዳለው ስፍራ ትሰደዳላችሁ፥ የሚሸሹትንም የሚሰበስብ የለም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ ዘንድ፣ ሽብር አመጣብሻለሁ፤” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ “እያንዳንዳችሁ ትሰደዳላችሁ፤ በሽሽት ላይ ያሉትንም የሚሰበስብ አይገኝም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እነሆ፥ በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ ዘንድ በአንቺ ላይ ፍርሃትን አመጣብሻለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ እያንዳንዳችሁም በፊታችሁ ወዳለው ስፍራ ትሰደዳላችሁ፥ የሚሸሹትንም የሚሰበስብ የለም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እኔ ከሁሉም አቅጣጫ ሽብር አመጣባችኋለሁ፤ ሁላችሁም ትሸሻላችሁ፤ ሁሉም ወደፊቱ ሸሽቶ ስለሚበታተን የሸሹትን ስደተኞች የሚሰበስብ አይገኝም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እነሆ በዙ​ሪ​ያሽ ካሉት ሁሉ ዘንድ ፍር​ሀ​ትን አመ​ጣ​ብ​ሻ​ለሁ፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም በፊ​ታ​ችሁ ወዳ​ለው ስፍራ ትሰ​ደ​ዳ​ላ​ችሁ፤ የሚ​ሸ​ሹ​ት​ንም የሚ​ሰ​በ​ስብ የለም።

参见章节 复制




ኤርምያስ 49:5
16 交叉引用  

እነሆ፥ በላዩ መንፈስን እሰድዳለሁ፤ ወሬንም ይሰማል፤ ወደ ምድሩም ይመለሳል፤ በምድሩም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርገዋለሁ፤’ በሉት፤” አላቸው።


የሚያስደነግጥ ድምፅ በጆሮው ነው፥ በደኅንነቱም ሳለ ቀማኛ ይመጣበታል።


ምክርን ምከሪ፥ ፍርድን አድርጊ፥ በቀትር ጊዜ ጥላሽን እንደ ሌሊት አድርጊ፥ የተሰደዱትን ሸሽጊ፥ የሸሹትን አትግለጪ።


መበለቶቻቸውም ከባሕር አሸዋ ይልቅ በዝተውብኛል፥ በብላቴኖች እናት ላይ በቀትር ጊዜ አጥፊውን አምጥቻለሁ፥ ጣርንና ድንጋጤን በድንገት አምጥቼባታለሁ።


እነሆ፥ ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እሰድዳለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እነርሱም ያጠምዱአቸዋል፥ ከዚያም በኋላ ብዙ አዳኞችን እሰድዳለሁ፥ እነርሱም ከየተራራውና ከየኮረብታው ሁሉ ከየድንጋዩም ስንጣቂ ውስጥ ያድኑአቸዋል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ ለራስህና ለወዳጆችህ ሁሉ ፍርሃት አደርግሃለሁ፥ እነርሱም በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ ዓይኖችህም ያያሉ፥ ይሁዳንም ሁሉ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ እርሱም ወደ ባቢሎን ያፈልሳቸዋል በሰይፍም ይገድላቸዋል።


ፈርተው ወደ ኋላ ሲመለሱ፥ ኃያላኖቻቸውም ሲደበደቡ ወደ ኋላቸውም ሳይመለከቱ ፈጥነው ሲሸሹ ለምን አየሁ? በዚህና በዚያ ድንጋጤ አለ፥ ይላል እግዚአብሔር።


ድንኳናቸውንና መንጋቸውን ይወስዳሉ፥ መጋረጆቻቸውንና ዕቃቸውን ሁሉ ግመሎቻቸውንም ለራሳቸው ይወስዳሉ፥ በዙሪያቸውም ሁሉ ጥፋትን ጥሩባቸው።


የጠላት ሰይፍና ድንጋጤ ከብበዋችኋልና ወደ ሜዳ አትውጡ በመንገድም ላይ አትሂዱ።


ሳምኬት። እናንተ ርኩሳን፥ ራቁ፥ ርቃችሁም ሂዱ፥ አትንኩ ብለው ጮኹባቸው። በሸሹና በተቅበዘበዙ ጊዜ፥ በአሕዛብ መካከል፦ በዚህ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖሩም ተባለ።


እያንዳንዳችሁ በየፊታችሁ በተነደለ ስፍራ ትወጣላችሁ፥ በሬማንም ትጣላላችሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።


ሰዎቹንም እንዲህ አለቻቸው፦ እግዚአብሔር ምድሪቱን እንደ ሰጣችሁ፥ እናንተንም መፍራት በላያችን እንደ ወደቀ፥ በምድሪቱም የሚኖሩት ሁሉ ከፊታችሁ እንደ ቀለጡ አወቅሁ።


跟着我们:

广告


广告