Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 48:44 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 በሞዓብ ላይ የመጐብኘትን ዓመት አመጣበታለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በፍርሃት የሸሸ በጕድጓድ ውስጥ ይወድቃል፥ ከጕድጓድም የወጣ በወጥመድ ይያዛል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 “ከሽብር የሚሸሽ ሁሉ፣ ጕድጓድ ውስጥ ይገባል፤ ከጕድጓዱም የሚወጣ፣ በወጥመድ ይያዛል፤ በሞዓብ ላይ፣ የቅጣቱን ዓመት አመጣለሁና፣” ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 በሞዓብ ላይ የመጐብኘትን ዓመት አመጣበታለሁና፥ ይላል ጌታ፤ ከአስፈሪውም ነገር የሸሸ በጉድጓድ ውስጥ ይወድቃል፥ ከጉድጓድም ውስጥ የሚወጣ በወጥመድ ይያዛል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 “ከሽብር የሚያመልጠው፥ ጒድጓድ ውስጥ ይገባል፤ ከጒድጓድ ዘሎ የሚወጣውም ሁሉ በወጥመድ ይያዛል፤ ሞአብን የምቀጣበትን ቀን አመጣባታለሁ” ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 እር​ስ​ዋን በም​ጐ​በ​ኝ​በት ዓመት በሞ​አብ ላይ ይህን አመ​ጣ​ለሁ፤ በፍ​ር​ሀት የሸሸ በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ ይወ​ድ​ቃል፤ ከጕ​ድ​ጓ​ድም የወጣ በወ​ጥ​መድ ይያ​ዛል፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

参见章节 复制




ኤርምያስ 48:44
22 交叉引用  

ከአዛሄልም ሰይፍ ያመለጠውን ሁሉ፥ ኢዩ ይገድለዋል፤ ከኢዩም ሰይፍ ያመለጠውን ሁሉ ኤልሳዕ ይገድለዋል።


በተጐበኛችሁበት ቀን፥ መከራም ከሩቅ በሚመጣበት ዘመን ምን ታደርጉ ይሆን? ለረድኤትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ክብራችሁንስ ወዴት ትተዉታላችሁ?


በምድር ላይ የምትኖር ሆይ፥ ፍርሃትና ገደል ወጥመድም በአንተ ላይ አሉ።


የሰማይ መስኮቶች ተከፍተዋልና፥ የምድርም መሠረት ተናውጣለችና ከፍርሃት ድምጽ የሸሸ በገደል ይወድቃል፥ ከገ ደልም የወጣ በወጥመድ ይያዛል።


እነርሱ ምናምንቴና የቀልድ ሥራ ናቸው፥ በተጐበኙ ጊዜ ይጠፋሉ።


በምጐበኛቸውም ዓመት በዓናቶት ሰዎች ላይ ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁና ማንም ከእነርሱ የሚቀር የለም።


እነሆ፥ ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እሰድዳለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እነርሱም ያጠምዱአቸዋል፥ ከዚያም በኋላ ብዙ አዳኞችን እሰድዳለሁ፥ እነርሱም ከየተራራውና ከየኮረብታው ሁሉ ከየድንጋዩም ስንጣቂ ውስጥ ያድኑአቸዋል።


ስለዚህ መንገዳቸው በጨለማ እንዳለች እንደ ድጥ ስፍራ ትሆንባቸዋለች፥ እነርሱም ፍግምግም ብለው ይወድቁባታል፥ እኔም በምጐበኛቸው ዓመት ክፉ ነገርን አመጣባቸዋለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር።


በእርስዋም ያሉ የተቀጠሩ ሠራተኞች እንደ ሰቡ ወይፈኖች ናቸው፥ የጥፋታቸው ቀንና የመጐብኘታቸው ጊዜ መጥቶባቸዋልና ተመለሱ፥ በአንድነትም ሸሹ፥ አልቆሙምም።


ጥበባቸውስ አልቆአልን? እናንተ በድዳን የምትኖሩ ሆይ፥ የዔሳውን ጥፋት፥ የምጐበኝበትን ጊዜ፥ አመጣበታለሁና ሽሹ፥ ወደ ኋላ ተመለሱ፥ በጥልቅም ውስጥ ተቀመጡ።


ባቢሎን ሆይ፥ አጥምጄብሻለሁ አንቺም ሳታውቂ ተይዘሻል፥ ከእግዚአብሔር ጋር ስለ ተዋጋሽ ተገኝተሻል ተይዘሽማል።


ወይፈኖችዋን ሁሉ እረዱ፥ ወደ መታረድም ይውረዱ፥ ቀናቸው፥ የመጐብኘታቸው ጊዜ፥ ደርሶአልና ወዮላቸው!


እነርሱም ምናምንቴና የቀልድ ሥራ ናቸው፥ በተጐበኙ ጊዜ ይጠፋሉ።


አስጸያፊ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም፥ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፥ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።


ድንጋጤና ቍጣ፥ ጥፋትና ቅጥቃጤ ሆነብን።


የበቀል ወራት መጥቶአል፥ የፍዳም ወራት ደርሶአል፥ እስራኤልም ያውቃል፥ ከኃጢአትህና ከጠላትነትህ ብዛት የተነሣ ነቢዩ ሰንፎአል፥ መንፈስም ያለበት ሰው አብዶአል።


ከአንበሳ ፊት እንደ ሸሸ ድብም እንዳገኘው ሰው፥ ወይም ወደ ቤት ገብቶ እጁን በግድግዳ ላይ እንዳስደገፈና እባብ እንደ ነደፈው ሰው ነው።


ከእነርሱም ሁሉ የተሻለው እርሱ እንደ አሜከላ ነው፥ ከሁሉም ቅን የሆነው እንደ ኵርንችት ነው፥ ጠባቆችህ የሚጐበኙበት ቀን መጥቶአል፥ አሁን ይሸበራሉ።


跟着我们:

广告


广告