Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 48:40 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ እንደ ንስር ይበርራል ክንፉንም በሞዓብ ላይ ይዘረጋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ እንደ ንስር ተወርውሮ ይወርድበታል፤ ክንፎቹንም በሞዓብ ላይ ይዘረጋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ጌታ እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ እንደ ንስር ይበርራል ክንፉንም በሞዓብ ላይ ይዘረጋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ክንፉን ዘርግቶ ወደ ታች እንደሚወረወር ንስር በሞአብ ላይ የሚያንዣብብ ጠላት መምጣቱን እግዚአብሔር ተናገረ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “እነሆ እንደ ንስር ይበ​ር​ራል፤ ክን​ፉ​ንም በሞ​አብ ላይ ይዘ​ረ​ጋል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 48:40
11 交叉引用  

በምዕራብም በኩል በፍልስጥኤማውያን ጫንቃ ላይ እየበረሩ ይወርዳሉ፥ የምሥራቅንም ልጆች በአንድነት ይበዘብዛሉ፥ በኤዶሚያስና በሞአብም ላይ እጃቸውን ይዘረጋሉ፥ የአሞንም ልጆች ለእነርሱ ይታዘዛሉ።


እየጎረፈም ወደ ይሁዳ ይገባል፥ እያጥለቀለቀም ያልፋል፥ እስከ አንገትም ይደርሳል፥ አማኑኤል ሆይ፥ የክንፉ መዘርጋት የአገርህን ስፋት ትሞላለች።


እነሆ፥ እንደ ደመና ይወጣል፥ ሰረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ፥ ፈረሶቹም ከንስር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው። ጠፍተናልና ወዮልን።


እነሆ፥ እንደ ንስር ወጥቶ ይበራል ክንፉንም በባሶራ ላይ ይዘረጋል፥ በዚያም ቀን የኤዶምያስ ኃያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል።


ቆፍ። አሳዳጆቻችን ከሰማይ ንስር ይልቅ ፈጣኖች ሆኑ፥ በተራሮች ላይ አሳደዱን፥ በምድረ በዳ ሸመቁብን።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ታላቅ ክንፍ ረጅምም ማርገብገቢያ ያለው ላባም የተሞላ፥ መልከ ዝንጕርጕር ታላቅ ንስር ወደ ሊባኖስ መጣ፥ የዝግባንም ጫፍ ወሰደ።


መጀመሪያይቱ አንበሳ ትመስል ነበር፥ የንስርም ክንፍ ነበራት፥ ክንፎችዋም ከእርስዋ እስኪነቀሉ ድረስ አይ ነበር፥ ከምድርም ከፍ ከፍ ተደረገች፥ እንደ ሰውም በሁለት እግር እንድትቆም ተደረገች፥ የሰውም ልብ ተሰጣት።


መለከትን ወደ አፍህ አቅርብ፥ ቃል ኪዳኔን ተላልፈዋልና፥ በሕጌም ላይ ዐምፀዋልና በእግዚአብሔር ቤት ላይ እንደ ንስር ይመጣል።


ፈረሶቻቸውም ከነብር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው፥ ከማታም ተኵላ ይልቅ ጨካኞች ናቸው፥ ፈረሰኞቻቸውም ይንሳፈፋሉ፥ ከሩቅም ይመጣሉ፥ ለመብልም እንደሚቸኵል ንስር ይበርራሉ።


እግዚአብሔር ቍንቍቸውን የማታውቀውን፥ ፊታቸው የደነደነውን፥ ሽማግሌውንም የማያፍሩትን፥ ሕፃኑንም የማይምሩትን ሕዝብ ንስር እንደሚበርር ከሩቅ አገር ከምድር ዳር ያመጣብሃል።


跟着我们:

广告


广告