Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 48:32 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 አንቺ የሴባማ ወይን ሆይ፥ ከኢያዜር ልቅሶ ይልቅ ለአንቺ አለቅሳለሁ፥ ቅርንጫፎችሽ ባሕርን ተሻግረዋል፥ ወደ ኢያዜርም ባሕር ደርሰዋል፥ አጥፊው በሰብልሽና በወይንሽ ላይ መጥቶአል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 የሴባማ ወይን ሆይ፤ ለኢያዜር ካለቀስሁት እንኳ ይልቅ አለቅስልሻለሁ፤ ቅርንጫፎችሽ እስከ ባሕሩ ተዘርግተዋል፤ እስከ ኢያዜርም ደርሰዋል፤ ለመከር በደረሰው ፍሬሽና በወይንሽ ላይ፣ አጥፊው መጥቷል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 አንቺ የሴባማ ወይን ሆይ! ከኢያዜር ልቅሶ ይልቅ ለአንቺ አለቅሳለሁ፤ ቅርንጫፎችሽ ባሕርን ተሻግረዋል፥ ወደ ኢያዜርም ባሕር ደርሰዋል፤ አጥፊው በበጋ ፍሬሽና በወይንሽ ላይ መጥቷል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ለያዕዜር ሕዝብ ከማለቅሰው ይበልጥ ለሲብማ ሕዝብ እየጮኽኩ አለቅሳለሁ፤ የሲብማ ከተማ ሆይ! እንቺ ቅርንጫፎችዋ ሙት ባሕርን አልፎ እስከ ያዜር እንደሚደርስ የወይን ተክል ነሽ፤ ነገር ግን በጐመራው ፍሬሽና በወይን ዘለላሽ ላይ አጥፊው መጥቷል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 አንቺ የሴ​ባማ ወይን ሆይ! የኢ​ያ​ዜ​ርን ልቅሶ ለአ​ንቺ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ችሽ ባሕ​ርን ተሻ​ግ​ረ​ዋል፤ ወደ ኢያ​ዜ​ርም ባሕር ደር​ሰ​ዋል፤ ሳይ​በ​ስል በሰ​ብ​ል​ሽና በወ​ይ​ንሽ ላይ ጥፋት መጥ​ቶ​አል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 48:32
13 交叉引用  

እኔም፥ እነሆ፥ ወደ እኛ በሚመጡት ከለዳውያን ፊት እቆም ዘንድ በምጽጳ እኖራለሁ፥ እናንተ ግን ወይንንና የበጋ ፍሬ ዘይትንም አከማቹ፥ በየዕቃችሁም ውስጥ ክተቱ፥ በያዛችኋቸውም ከተሞቻችሁ ተቀመጡ።


ሞዓብ ፈርሶአል፥ ከተሞቹም ጠፍተዋል፥ የተመረጡትም ጕልማሶች ወደ መታረድ ወርደዋል፥ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነ ንጉሥ።


በዲቦን የምትኖሪ ሆይ፥ ሞዓብን የሚያጠፋ ወጥቶብሻልና፥ አምባሽንም ሰብሮአልና ከክብርሽ ውረጂ በጥማትም ተቀመጪ።


እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ፥ አጥፊ ወደ ከተማ ሁሉ ይመጣል አንዲትም ከተማ አትድንም፥ ሸለቆውም ይጠፋል ሜዳውም ይበላሻል።


ሙሴም ሰላዮችን ወደ ኢያዜር ሰደደ፤ መንደሮችዋንም ወሰዱ፥ በዚያም የነበሩትን አሞራውያን አባረሩ።


የሮቤልና የጋድ ልጆችም እጅግ ብዙ እንስሶች ነበሩአቸው፤ እነሆም፥ የኢያዜር ምድርና የገለዓድ ምድር ለእንስሶች የተመቸ ስፍራ እንደ ነበረ ባዩ ጊዜ፥


እግዚአብሔር በእስራኤል ማኅበር ፊት የመታው ምድር፥ አጣሮት፥ ዲቦን፥ ኢያዜር፥ ነምራ፥ ሐሴቦን፥ ኤልያሊ፥ ሴባማ፥ ናባው፥ ባያን፥ ለእንስሶች የተመቸ ምድር ነው፤ ለእኛም ለባሪያዎችህ እንስሶች አሉን።


ዓጥሮትሽፋንን፥ ኢያዜርን፥ ዮግብሃን፥


ቂርያትይምን፥ ስማቸውም የተለወጠውን ናባውን፥ በኣልሜዎንን፥ ሴባማን ሠሩ፤ እነዚህንም የሠሩአቸውን ከተሞች በሌላ ስም ጠሩአቸው።


ሜፍዓት፥ ቂርያታይም፥ ሴባማ፥ በሸለቆውም ተራራ ያለችው ጼሬትሻሐር፥


ድንበራቸውም ኢያዜርና የገለዓድ ከተሞች ሁሉ፥ የአሞንም ልጆች ምድር እኩሌታ በረባት ፊት እስካለችው እስከ አሮዔር ድረስ፥


ሐሴቦንንና መሰምርያዋን፥ ኢያዜርንና መሰምርያዋን፥ አራቱን ከተሞች ሰጡ።


跟着我们:

广告


广告