Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 48:20 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ሞዓብም ፈርሶአልና አፈረ፥ አልቅሱ ጩኹም፥ ሞዓብ እንደ ተዘረፈ በአርኖን አጠገብ አውሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ሞዓብ በመፍረሱ ተዋርዷል፤ ዋይ በሉ፤ ጩኹ፤ የሞዓብን መደምሰስ፣ በአርኖን አጠገብ አስታውቁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ሞዓብም ፈርሶአልና አፈረ፤ አልቅሱ ጩኹም፤ ሞዓብ እንደ ጠፋ በአርኖን አጠገብ አውጁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ሞአብ ፈራርሳ በዕፍረት ስለ ወደቀች ዋይ ዋይ ብላችሁ አልቅሱላት፤ ባድማ መሆንዋንም በአርኖን ወንዝ አጠገብ ተናገሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 “ሞአብ ፈር​ሳ​ለ​ችና አፈ​ረች፤ አል​ቅሱ፥ ጩኹም፤ ሞአብ እንደ ጠፋች በአ​ር​ኖን አውሩ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 48:20
10 交叉引用  

ጩኸት የሞዓብን ዳርቻ ሁሉ ዞረ፥ ልቅሶዋም ወደ ኤግላይምና ወደ ብኤርኢሊም ደረሰ።


እንደሚበርር ወፍ እንደተበተኑም ጫጩቶች እንዲሁ የሞዓብ ሴቶች ልጆች በአርኖን መሻገሪያዎች ይሆናሉ።


በአርኖን ቈላ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር ከሸለቆውም ውስጥ ካለችው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ድረስ ማናቸይቱም ከተማ አልጠነከረችብንም፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉን አሳልፎ ሰጠን።


በአርኖን ሸለቆ ዳር ካለችው ከአሮዔር፥ በሸለቆውም መካከል ካለችው ከተማ ጀምሮ የሜድባን ሜዳ ሁሉ እስከ ዲቦን ድረስ፥


እስራኤልም በቃዴስ ተቀመጠ። በምድረ በዳም በኩል ሄዱ፥ የኤዶምያስንና የሞዓብንም ምድር ዞሩ፥ ከሞዓብ ምድርም በምሥራቅ በኩል መጡ በአርኖንም ማዶ ሰፈሩ፥ አርኖንም የሞዓብ ድንበር ነበረና የሞዓብን ድንበር አላለፉም።


跟着我们:

广告


广告