Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 48:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ከእንግዲህ ወዲህ የሞዓብ ትምክሕት የለም፥ በሐሴቦን ላይ፦ ኑ ሕዝብ እንዳትሆን እናጥፋት ብለው ክፉ ነገር አስበውባታል። መድሜን ሆይ፥ አንቺ ደግሞ ትጠፊአለሽ ሰይፍም ያሳድድሻል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ከእንግዲህ ሞዓብ አትከበርም፤ ሰዎች በሐሴቦን ተቀምጠው፣ ‘ኑ ያቺን አገር እናጥፋት’ ብለው ይዶልቱባታል። መድሜን ሆይ፤ አንቺም ደግሞ ጸጥ ትደረጊያለሽ፤ ሰይፍም ያሳድድሻል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ከእንግዲህ ወዲህ የሞዓብ ትምክሕት የለም፤ በሐሴቦን ሆነው፦ ኑ ሕዝብ እንዳትሆን እናጥፋት፥ ብለው ክፉ ነገር አስበውባታል። መድሜን ሆይ! አንቺ ደግሞ በጸጥታ ትዋጫለሽ ሰይፍም ያሳድድሻል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የሞአብ ክብር ያልፋል፤ ሰዎች ሐሴቦንን ለመጣል ያሤራሉ፤ ‘ኑ ከእንግዲህ በሕዝብነት እንዳትታወቅ እናጥፋት’ ይላሉ፤ እናንተም የማድሜን ሰዎች ሆይ! ሰይፍ ስለሚያሳድዳችሁ ጸጥ እንድትሉ ትደረጋላችሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የሞ​አብ ፈውስ የለም፤ በሐ​ሴ​ቦን ላይ፥ “ኑ ሕዝብ እን​ዳ​ት​ሆን እና​ጥ​ፋት” ብለው ክፉ ነገ​ርን አስ​በ​ው​ባ​ታል። ፈጽሞ ትተ​ዋ​ለች፤ ከኋ​ላዋ ሰይፍ ይመ​ጣ​ልና።

参见章节 复制




ኤርምያስ 48:2
20 交叉引用  

ስለ ሞዓብ የተነገረ ሸክም። የሞዓብ ኤር በሌሊት ፈርሶ ጠፋ፥ ቂር የሚባልም የሞዓብ ምሽግ በሌሊት ፈርሶ ጠፋ።


ልቤ ስለ ሞዓብ ጮኸ፥ ከእርስዋ የሚሸሹ ወደ ዞዐር ወደ ዔግላት ሺሊሺያ ኮበለሉ፥ በሉሒት ዓቀበት ላይ እያለቀሱ ይወጣሉ፥ በሖሮናይምም መንገድ የዋይታ ጩኽት ያነሣሉ።


አሁን ግን እግዚአብሔር፦ በሦስት ዓመት ውስጥ እንደ ምንደኛ ዓመት የሞዓብ ክብርና የሕዝቡ ሁሉ ብዛት ይዋረዳል፥ ቅሬታውም እጅግ ያነሰና የተጠቃ ይሆናል ይላል።


የእግዚአብሔርም እጅ በዚህ ተራራ ላይ ታርፋለች፥ ጭድም በጭቃ ውስጥ እንደሚረገጥ እንዲሁ ሞዓብ በሥፍራው ይረገጣል።


የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፦ የዚህን ቍጣ የወይን ጠጅ ጽዋ ከእጄ ውሰድ አንተንም የምሰድድባቸውን አሕዛብን ሁሉ አጠጣቸው።


ከእግዚአብሔርም እጅ ጽዋውን ወሰድሁ፥ እግዚአብሔርም እኔን የሰደደባቸውን አሕዛብ ሁሉ አጠጣኋቸው።


ይህ ሕግ ከፊቴ ቢወገድ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚያን ጊዜ ደግሞ የእስራኤል ዘር በፊቴ ሕዝብ እንዳይሆን ለዘላለም ይቀራል።


ይህ ሕዝብ፦ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሁለቱን ወገን ጥሎአቸዋል ያለውን ነገር አትመለከትምን? እንዲሁ በፊታቸው ከእንግዲህ ወዲህ ሕዝብ እንዳይሆን ሕዝቤን አቃልለዋል።


አንተ ባሪያዬ ያዕቆብ ሆይ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ አንተንም ያሰደድሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁና፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፥ በመጠን እቀጣሃለሁ፥ ያለ ቅጣትም አልተውህም።


በዙሪያው ያላችሁ ሁሉ ስሙንም የምታውቁ ሁሉ፦ ብርቱው በትር፥ የከበረው ሽመል፥ እንዴት ተሰበረ! ብላችሁ አልቅሱለት።


ሞዓብም በእግዚአብሔር ላይ ኰርቶአልና ሕዝብ ከመሆን ይጠፋል።


የሸሹ ደክመው ከሐሴቦን ጥላ በታች ቆመዋል፥ እሳት ከሐሴቦን ነበልባልም ከሴዎን ወጥቶአል የሞዓብንም ማዕዘን የሤትንም ልጆች አናት በልቶአል።


ሐሴቦን ሆይ፥ ጋይ ፈርሳለችና አልቅሺላት፥ እናንተም የረባት ሴቶች ልጆች ሆይ፥ ሚልኮም ካህናቱና አለቆቹም በአንድነት ይማረካሉና ጩኹ፥ ማቅም ታጠቁ፥ አልቅሱም፥ በቅጥሮችም መካከል ተርዋርዋጡ።


በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውን በሚሹአት ፊት ኤላምን አስደነግጣለሁ፥ ክፉ ነገርን እርሱም ጽኑ ቍጣዬን አመጣባቸዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እስካጠፋቸውም ድረስ በኋላቸው ሰይፍ እሰድድባቸዋለሁ፥


የሮቤልም ልጆች ሐሴቦንን፥ ኤልያሊን፥


跟着我们:

广告


广告