Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 48:15 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ሞዓብ ፈርሶአል፥ ከተሞቹም ጠፍተዋል፥ የተመረጡትም ጕልማሶች ወደ መታረድ ወርደዋል፥ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነ ንጉሥ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሞዓብ ትጠፋለች፤ ከተሞቿም ይወረራሉ፤ ምርጥ ወጣቶቿም ወደ መታረድ ይወርዳሉ፤” ይላል ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነው ንጉሥ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ወደ ሞአብና ከተሞችዋ አጥፊው ወጥቶአል፥ የተመረጡትም ጉልማሶች ወደ መታረድ ወርደዋል፥ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ የሆነ ንጉሥ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ሞአብና ከተሞችዋማ እነሆ ተደምስሰዋል፤ የሚያስደስቱ ወጣቶችዋም ለመታረድ ወርደዋል። እኔ ንጉሡ ይህን ተናግሬአለሁ ስሜም ‘የሠራዊት አምላክ’ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ሞዓብ ፈር​ሳ​ለች፤ ከተ​ሞ​ቹ​ዋም ጠፍ​ተ​ዋል፤ የተ​መ​ረ​ጡ​ትም ጐል​ማ​ሶ​ችዋ ወደ መታ​ረድ ወር​ደ​ዋል፥ ይላል ስሙ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

参见章节 复制




ኤርምያስ 48:15
17 交叉引用  

እኔ ሕያው ነኝና በተራሮች መካከል እንዳለ እንደ ታቦር፥ በባሕርም አጠገብ እንዳለ እንደ ቀርሜሎስ፥ እንዲሁ በእውነት ይመጣል፥ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የተባለው ንጉሥ።


ሞዓብ ጠፍታለች፥ ልጆችዋም ጩኸትን አሰምተዋል።


ወይፈኖችዋን ሁሉ እረዱ፥ ወደ መታረድም ይውረዱ፥ ቀናቸው፥ የመጐብኘታቸው ጊዜ፥ ደርሶአልና ወዮላቸው!


ተቤዢአቸው ብርቱ ነው፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፥ ምድርንም ያሳርፍ ዘንድ በባቢሎንም የሚኖሩትን ያውክ ዘንድ ሙግታቸውን ፈጽሞ ይምዋገታል።


እንደ ጠቦቶችና እንደ አውራ በጎች እንደ አውራ ፍየሎችም ወደ መታረድ አወርዳቸዋለሁ።


መሳፍንቶችዋንና ጥበበኞችዋንም፥ አለቆችዋንና ሹማምቶችዋን ኃያላኖችዋንም አሰክራለሁ፥ ለዘላለምም አንቀላፍተው አይነቁም፥ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የተባለው ንጉሥ።


አሁንም እኔ ናቡከደነፆር የሰማይን ንጉሥ አመሰግናለሁ፥ ታላቅም አደርገዋለሁ፥ አከብረውማለሁ። ሥራው ሁሉ እውነት፥ መንገዱም ፍርድ ነውና፥ በትዕቢትም የሚሄዱትን ያዋርድ ዘንድ ይችላልና።


በግብጽ እንደ ነበረው ቸነፈርን ሰደድሁባችሁ፥ ጐበዛዝቶቻችሁን በሰይፍ ገደልሁ፥ ፈረሶቻችሁንም አስማረክሁ፥ የሰፈራችሁንም ግማት ወደ አፍንጫችሁ አወጣሁ፥ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር።


እግዚአብሔርም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፥ በዚያ ቀን እግዚአብሔር አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል።


እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ስሜም በአሕዛብ ዘንድ የተፈራ ነውና በመንጋው ውስጥ ተባት እያለው ለጌታ ተስሎ ነውረኛውን የሚሠዋ ሸንጋይ ሰው ርጉም ይሁን።


እነሆ፥ እርሻችሁን ያጨዱት የሠራተኞች ደመወዝ በእናንተ ተቀምቶ ይጮኻል፥ የአጫጆችም ድምፅ ወደ ጌታ ፀባዖት ጆሮ ገብቶአል።


በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት፦ የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ የሚል ስም አለው።


跟着我们:

广告


广告