Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 48:13 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የእስራኤልም ቤት ይታመንባት ከነበረው ከቤቴል እንዳፈረ፥ እንዲሁ ሞዓብ ከካሞሽ ያፍራል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 የእስራኤል ቤት፤ በቤቴል ታምኖ እንዳፈረ ሁሉ፣ ሞዓብም በካሞሽ ያፍራል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የእስራኤልም ቤት መተማመኛቸው በነበረችው በቤቴል እንዳፈረ፥ እንዲሁ ሞዓብ በካሞሽ ያፍራል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እስራኤላውያን ይታመኑበት በነበረው በቤቴል በተተከለው ጣዖት እንዳፈሩ፥ ሞአባውያንም ከሞሽ ተብሎ በሚጠራው ጣዖታቸው ያፍራሉ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ይታ​መ​ን​ባት ከነ​በ​ረው ከቤ​ቴል እን​ዳ​ፈረ፥ እን​ዲሁ ሞአብ ከካ​ሞሽ ታፍ​ራ​ለች።

参见章节 复制




ኤርምያስ 48:13
21 交叉引用  

ጥለውኛልና፥ ለሲዶናውያንም አምላክ ለአስታሮት፥ ለሞዓብም አምላክ ለካሞሽ፥ ለአሞንም ልጆች አምላክ ለሚልኮም ሰግደዋልና፥ አባቱም ዳዊት እንዳደረገ በፊቴ ቅን ነገር ያደርጉ ዘንድ፥ ሥርዐቴንና ፍርዴንም ይጠብቁ ዘንድ በመንገዴ አልሄዱምና።


በዚያን ጊዜም ሰሎሞን ለሞዓብ ርኵሰት ለካሞሽ፥ ለአሞንም ልጆች ርኵሰት ለሞሎክ በኢየሩሳሌም ፊት ለፊት ባለው ተራራ ላይ መስገጃ ሠራ።


ኤልያስም “ከበኣል ነቢያት አንድ ሰው እንዳያመልጥ ያዙ!” አላቸው። ያዙአቸውም፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ በዚያ አሳረዳቸው።


ስለዚህም የእግዚአብሔር ቍጣ በአሜስያስ ላይ ነደደና “ሕዝባቸውን ከአንተ እጅ ያላዳኑትን የአሕዛብን አማልክት ስለ ምን ፈለግሃቸው?” የሚል ነቢይ ሰደደበት።


ሞዓም መጥቶ በኮረብታ መስገጃ ላይ በደከመና ለጸሎት ወደ መቅደሱ በገባ ጊዜ አያሸንፍም።


በዚያን ቀን ሰው ይሰግድላቸው ዘንድ ያበጁአቸውን የብሩንና የወርቁን ጣዖቶቹን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይጥላል።


ሁሉም ያፍራሉ ይዋረዱማል፥ ጣዖታትንም የሚሠሩ በአንድነት ወደ ውርደት ይሄዳሉ።


እናንተ ከአሕዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ፥ ተሰብስባችሁ ኑ በአንድነትም ቅረቡ፥ የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ እውቀት የላቸውም።


ስለዚህ፥ እነሆ፥ የሚያገላብጡትን የምልክበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እነርሱም ያገላብጡታል፥ ጋኖቹንም ባዶ ያደርጋሉ፥ መስቴዎቹንም ይሰብራሉ።


እንዴት ተገለበጠ! በእፍረትም የተነሣ ሞዓብ ጀርባውን እንዴት መለሰ! ብላችሁ አልቅሱ። ሞዓብም በዙሪያው ላሉት ሁሉ መሳቂያና ድንጋጤ ይሆናል።


ሞዓብ ሆይ፥ ወዮልህ! የካሞሽ ወገን ጠፍቶአል፥ ወንዶች ልጆችህ ተማርከዋልና፥ ሴቶች ልጆችህም ወደ ምርኮ ሄደዋልና።


በሥራሽና በመዝገብሽ ታምነሻልና አንቺ ደግሞ ትያዢያለሽ፥ ካሞሽም ከካህናቱና ከአለቆቹ ጋር በአንድነት ይማረካል።


አምላክህ ካሞሽ የሚሰጥህን አትወርስምን? እኛም አምላካችን እግዚአብሔር ከፊታችን ያስወጣቸውን የእነርሱን ምድር እንወርሳለን።


跟着我们:

广告


广告