Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 47:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ከኃይለኞች ፈረሶች ከኮቴያቸው መጠብጠብ ድምፅ፥ ከሰረገሎቹም መሽከርከር፥ ከመንኰራኵሮቹም መትመም የተነሣ አባቶች በእጃቸው ድካም ምክንያት ፊታቸውን መልሰው ወደ ልጆቻቸው አይመለከቱም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከፈረስ ኮቴ ድምፅ፣ ከጠላት ሠረገላ ጩኸትና ከሠረገላው ሽክርክሪት ፍትጊያ ድምፅ የተነሣ፣ አባቶች ልጆቻቸውን ለመርዳት ወደ ኋላ መለስ አይሉም፤ እጃቸውም ስንኩል ይሆናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ከኃይለኞች ፈረሶቹ የኮቴያቸው ድምፅ፥ ከሰረገሎቹም መንጐድ፥ ከመንኰራኵሮቹም መትመም የተነሣ አባቶች በእጃቸው ድካም ምክንያት ወደ ልጆቻቸው ዘወር ብለው አይመለከቱም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ከሚጋልቡ ፈረሶች ኮቴ ድምፅ፥ ከጠላት መንኰራኲር ድምፅ፥ ከሠረገሎቻቸው መትመም የተነሣ አባቶች ኀይላቸው በመድከሙ ምክንያት ልጆቻቸውን እንኳ ለመርዳት ወደ ኋላ አይመለሱም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ከኀ​ይ​ለ​ኞች ፈረ​ሶች ከኮ​ቴ​ያ​ቸው መጠ​ብ​ጠብ ድምፅ፥ ከሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹም መሽ​ከ​ር​ከር፥ ከመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ቹም መት​መም የተ​ነሣ አባ​ቶች በእ​ጃ​ቸው ድካም ምክ​ን​ያት ወደ ልጆ​ቻ​ቸው አይ​መ​ለ​ሱም።

参见章节 复制




ኤርምያስ 47:3
14 交叉引用  

ፍላጾቻቸው ተስለዋል፥ ቀስቶቻቸውም ሁሉ ተለጥጠዋል፥ የፈረሶቻቸውም ኮቴ እንደ ቡላድ የሰረገሎቻቸውም መንኮራኵር እንደ ዐውሎ ነፋስ ይቈጠራል።


ፈረሶች ሆይ፥ ውጡ፥ ሰረገሎችም ሆይ፥ ንጐዱ፥ ጋሻም የሚያነግቡ የኢትዮጵያና የፉጥ ኃያላን፥ ቀስትንም ይዘው የሚስቡ የሉድ ኃያላን ይውጡ።


ቀስትንና ጦርን ይይዛሉ፥ ጨካኞች ናቸው ምሕረትም አያደርጉም፥ ድምፃቸው እንደ ባሕር ይተምማል በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ፥ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፥ ለሰልፍ እንደ ተዘጋጀ ሰው እያንዳንዳቸው በአንቺ ላይ ተሰለፉ።


የፈረሰኞቹ ድምጽ ከዳን ተሰማ፥ ከአርበኞች ፈረሶች ማሽካካት የተነሣ ምድር ሁሉ ተንቀጠቀጠች፥ መጡም ምድሪቱንና በእርስዋም ያለውን ሁሉ፥ ከተማይቱንና የተቀመጡባትንም በሉ።


በመሣሪያና በሰረገላ በመንኰራኵርም በአሕዛብም ጉባኤ ይመጡብሻል፥ ጋሻና አላባሽ ጋሻ ራስ ቍርም ይዘው በዙሪያሽ ይዘጋጁብሻል፥ ፍርድንም እሰጣቸዋለሁ፥ እንደ ፍርዳቸውም ይፈርዱብሻል።


የብረት ጥሩር የሚመስልም ጥሩር ነበራቸው፥ የክንፋቸውም ድምፅ ወደ ጦርነት እንደሚጋልቡ እንደ ብዙ ፈረሶች ሰረገላዎች ድምፅ ነበረ።


ከኃያላን ግልቢያ ብርታት የተነሣ የፈረሶች ጥፍሮች ተቀጠቀጡ።


跟着我们:

广告


广告