ኤርምያስ 47:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ውኃ ከሰሜን ይነሣል የሚያጥለቀልቅም ፈሳሽ ይሆናል፥ በአገሪቱና በመላዋ ሁሉ፥ በከተማይቱና በሚኖሩባት ላይ ይጐርፋል፥ ሰዎቹም ይጮኻሉ፥ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ በሰሜን በኩል ውሃ እየሞላ ነው፤ ኀይለኛ ጐርፍ ይሆናል፤ አገሪቷንና በውስጧ ያሉትንም ሁሉ፣ ከተሞቿንና ነዋሪዎቻቸውን ያጥለቀልቃል። ሕዝቡም ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፤ የምድሪቱ ነዋሪ ሁሉ ዋይ ዋይ ይላል፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 “ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ውኃ ከሰሜን ይነሣል የሚያጥለቀልቅም ጐርፍ ይሆናል፤ በአገሪቱና በመላዋ ሁሉ፥ በከተማይቱና በሚኖሩባት ላይ ያጥለቀልቃቸዋል፤ ሰዎቹም ይጮኻሉ፥ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ውሃ ከሰሜን በኩል ተነሥቶ በጐርፍ እንደ ተሞላ ወንዝ ይፈስሳል፤ ምድርንና በምድር ላይ ያለውን ሁሉ ከተሞችንና በውስጣቸው የሚኖሩትን ሕዝብ በሙሉ ይሸፍናል። ሕዝቡ ሁሉ ርዳታ ለማግኘት ይጮኻሉ፤ በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ምርር ብለው ያለቅሳሉ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ ውኃ ከሰሜን ይነሣል፥ የሚያጥለቀልቅም ፈሳሽ ይሆናል፤ በሀገሪቱና በመላዋ ሁሉ፥ በከተማዪቱና በሚኖሩባትም ላይ ይጐርፋል፤ ሰዎቹም ይጮኻሉ፤ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ። 参见章节 |