Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 42:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 የምትፈሩት ሰይፍ በዚያ በግብጽ ምድር ያገኛችኋል፥ ስለ እርሱም የምትደነግጡበት ራብ በዚያ በግብጽ ይደርስባቸኋል፥ በዚያም ትሞታላችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የፈራችሁት ሰይፍ በዚያ ያገኛችኋል፤ የሠጋችሁበት ራብ እስከ ግብጽ ድረስ ተከትሏችሁ ይመጣል፤ በዚያም ትሞታላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የምትፈሩት ሰይፍ በዚያ በግብጽ ምድር ይደርስባችኋል፥ የሚያስደነግጣችሁም ራብ በዚያ በግብጽ ይከተላችኋል፥ በዚያም ትሞታላችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ያ የምትፈሩት ጦርነት ይደርስባችኋል፤ የምትፈሩትም ራብ ተከትሎአችሁ ይሄዳል፤ በዚያም በግብጽ ትሞታላችሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እና​ንተ የም​ት​ፈ​ሩት ሰይፍ በዚያ በግ​ብፅ ምድር ያገ​ኛ​ች​ኋል፤ ስለ እር​ሱም የም​ት​ደ​ነ​ግ​ጡ​በት ራብ በዚያ በግ​ብፅ ይደ​ር​ስ​ባ​ች​ኋል፤ በዚ​ያም ትሞ​ታ​ላ​ችሁ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 42:16
13 交叉引用  

ለባቢሎን ንጉሥም ለናቡከደነፆር የማይገዛውን፥ ከባቢሎንም ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የማያደርገውን ሕዝብና መንግሥት፥ ያን ሕዝብ በእጁ እስካጠፋው ድረስ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም እቀጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።


እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ በአገሩ ላይ የሾመውን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ስለ ገደለው ከለዳውያንን ፈርተዋልና።


እናንተ ግን፦ በዚህች ምድር አንቀመጥም ብትሉ የአምላካችሁንም የእግዚአብሔርን ቃል ባትሰሙ፥


እነሆ፥ ለመልካም ሳይሆን ለክፋት እተጋባቸዋለሁ፥ በግብጽም ምድር ያሉት የይሁዳ ሰዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በራብ ያልቃሉ።


ሰይፍን ፈርታችኋል እኔም ሰይፍን አመጣባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ለባሪያዎቼስ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? እነርሱም ተመልሰው፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ያደርግብን ዘንድ እንዳሰበ እንዲሁ አድርጎብናል አሉ።


እንዲሁ ብንተወው ሁሉ በእርሱ ያምናሉ፤ የሮሜም ሰዎች መጥተው አገራችንን ወገናችንንም ይወስዳሉ” አሉ።


ነገር ግን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ባትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ ባትጠብቅ ባታደርግም፥ እነዚህ መርገሞች ሁሉ ይመጡብሃል ያገኙህማል።


እግዚአብሔር በክሳት፥ በንዳድም፥ በጥብሳትም፥ በትኩሳትም፥ በድርቅም፥ በዋግም፥ በአረማሞም ይመታሃል፤ እስክትጠፋም ድረስ ያሳድዱሃል።


የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቃል ስላልሰማህ፥ ያዘዘህንም ትእዛዙንና ሥርዓቱን ስላልጠበቅህ፥ እስክትጠፋ ድረስ እነዚህ መርገሞች ሁሉ ይወርዱብሃል፥ ያሳድዱህማል፥ ያገኙህማል።


跟着我们:

广告


广告