Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 41:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በመካከላቸውም እስማኤልን፦ በሜዳ የተሸሸገ ስንዴና ገብስ ዘይትና ማርም አለንና አትግደለን የሚሉት አሥር ሰዎች ተገኙ። እርሱም ተዋቸው፥ ከወንድሞቻቸውም ጋር አልገደላቸውም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከተገደሉት ጋራ የነበሩ ዐሥር ሰዎች ግን እስማኤልን፣ “እባክህ አትግደለን! በዕርሻችን ውስጥ የሸሸግነው ስንዴና ገብስ፣ የወይራ ዘይትና ማር ስላለን እባክህን አትግደለን” አሉት። እርሱም ተዋቸው፤ ከሌሎቹም ጋራ አልገደላቸውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በመካከላቸውም እስማኤልን፦ “በእርሻ ውስጥ የተሸሸገ ስንዴና ገብስ ዘይትና ማርም አለንና አትግደለን” የሚሉት ዐሥር ሰዎች ተገኙ። እርሱም ተዋቸው፥ ከወንድሞቻቸውም ጋር አልገደላቸውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ከእነዚያ ሰማኒያ ሰዎች መካከል በተለይ ዐሥሩ ሰዎች “እባክህ አትግደለን! እኛ በእርሻ ውስጥ የደበቅነው ብዙ ስንዴ፥ ገብስ፥ የወይራ ዘይትና ማር. አለን” ብለው እስማኤልን ለመኑት። እርሱም ምሕረት አደረገላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በዚ​ያም የተ​ገኙ ዐሥር ሰዎች ቀር​በው እስ​ማ​ኤ​ልን እን​ዲህ አሉት፥ “በሜ​ዳው ድልብ አለ​ንና፥ ገብ​ስና ስንዴ፥ ዘይ​ትና ማርም አለ​ንና አት​ግ​ደ​ለን፤” እር​ሱም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው መካ​ከል እነ​ር​ሱን መግ​ደል ተወ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 41:8
9 交叉引用  

ሰይጣንም መልሶ እግዚአብሔርን፦ ቁርበት ስለ ቁርበት ነው፥ ሰው ያለውን ሁሉ ስለ ሕይወቱ ይሰጣል።


በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት እሰጥሃለሁ።


እስማኤልም ከጎዶልያስ ጋር የገደላቸውን የሰዎች ሬሳ ሁሉ የጣለበት ጕድጓድ ንጉሡ አሳ የእስራኤልን ንጉሥ ባኦስን ስለ ፈራ የሠራው ጕድጓድ ነበረ፥ የናታንያም ልጅ እስማኤል የገደላቸውን ሞላበት።


ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጕኦድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?


ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?


跟着我们:

广告


广告