Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 40:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የሳፋንም ልጅ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነርሱና ለሰዎቻቸው እንዲህ ብሎ ማለ፦ ለከለዳውያን ትገዙ ዘንድ አትፍሩ፥ በምድር ተቀመጡ ለባቢሎንም ንጉሥ ተገዙ፥ መልካምም ይሆንላችኋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የሳፋን ልጅ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነርሱና ለሰዎቻቸው እንዲህ ሲል ቃል ገባላቸው፤ “ለባቢሎናውያን መገዛት አትፍሩ፤ በምድሪቱ ተቀምጣችሁ የባቢሎንን ንጉሥ አገልግሉ፤ መልካም ይሆንላችኋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የሳፋንም ልጅ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነርሱና ለሰዎቻቸው እንዲህ ብሎ ማለ፦ “ለከለዳውያን ለማገልገል አትፍሩ፤ በምድሪቱ ተቀመጡ ለባቢሎንም ንጉሥ አገልግሉ፥ መልካምም ይሆንላችኋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ገዳልያም እንዲህ ሲል ማለላቸው፦ “በእውነት ቃል ልግባላችሁ፤ ለባቢሎናውያን እጃችሁን ስለ መስጠት ምንም የሚያስፈራችሁ ነገር የለም፤ በዚህች ምድር ሰፍራችሁ ኑሮአችሁን መሥርቱ፤ ለባቢሎን ንጉሥ ገብሩ፤ ለእናንተም ሁሉ ነገር መልካም ይሆንላችኋል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የሳ​ፋ​ንም ልጅ የአ​ኪ​ቃም ልጅ ጎዶ​ል​ያስ ለእ​ነ​ር​ሱና ለሰ​ዎ​ቻ​ቸው እን​ዲህ ብሎ ማለ፥ “ለከ​ለ​ዳ​ው​ያን ትገዙ ዘንድ አት​ፍሩ፤ በም​ድር ተቀ​መጡ፤ ለባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ተገዙ፤ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 40:9
9 交叉引用  

ዕረፍትም መልካም መሆንዋን አየ ምድሪቱም የለማች መሆንዋን ትከሻውን ለመሸከም ዝቅ አደረገ በሥራም ገበሬ ሆነ።


ጎዶልያስም “ከከለዳውያን ሎሌዎች የተነሣ አትፍሩ፤ በአገሩ ተቀመጡ፤ ለባቢሎንም ንጉሥ ተገዙ፤ መልካምም ይሆንላችኋል፤” ብሎ ለእነርሱና ለሰዎቻቸው ማለላቸው።


ነገር ግን ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የሚያደርገውንና የሚገዛለትን ሕዝብ በአገሩ ላይ እተወዋለሁ፥ እነርሱም ያርሱአታል ይቀመጡባትማል።


አሌፍ። ሕዝብ ሞልቶባት የነበረች ከተማ ብቻዋን እንዴት ተቀመጠች! በአሕዛብ መካከል ታላቅ የነበረች እንደ መበለት ሆናለች፥ በአውራጆች መካከል ልዕልት የነበረች ተገዢ ሆናለች።


ከምድረ በዳ ሰይፍ የተነሣ በሕይወታችን እንጀራችንን እናመጣለን።


跟着我们:

广告


广告