Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 40:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 አሁንም፥ እነሆ፥ በእጅህ ካለችው ሰንሰለት ዛሬ ፈታሁህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ቢታይህ፥ ና፥ እኔም በመልካም አይሃለሁ፥ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ባይታይህ ግን፥ ተቀመጥ፥ እነሆ፥ አገሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት፥ ትሄድ ዘንድ መልካም መስሎ ወደሚታይህ ደስ ወደሚያሰኝህም ስፍራ ሂድ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እነሆ፤ ዛሬ የእጅህን ሰንሰለት ፈታሁልህ። ከፈለግህ ከእኔ ጋራ ወደ ባቢሎን ና፤ እኔም እንከባ ከብሃለሁ፤ ካልፈለግህ ግን አትምጣ። እነሆ፤ አገሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት፤ ወደ ቀናህ ሂድ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 አሁን ደግሞ፥ እነሆ፥ በእጅህ ካለው ሰንሰለት ዛሬ ፈታሁህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ቢታይህ፥ ና፥ እኔም በበጎ ዐይን እመለከትሀለው፤ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ባይታይህ ግን፥ ቅር፤ እነሆ ተመልከት፥ አገሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት፤ ለመሄድ መልካም መስሎ ወደሚታይህ ትክክልም ነው ብለህ ወደምታስበው ስፍራ ወደዚያ ሂድ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እነሆ እኔ በእጅህ ላይ ያለውን ሰንሰለት ፈትቼ ነጻ አደርግሃለሁ፤ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን ለመውረድ ብትፈልግ እንደ ወደድክ አድርግ፤ እኔም ለአንተ እንክብካቤ አደርግልሃለሁ፤ ወደዚያ ለመሄድ ካልፈለግህ ግን መቅረት ትችላለህ፤ እነሆ አገሪቱ በሞላ በፊትህ ስለ ሆነች ወደ መረጥከው ቦታ መሄድ ትችላለህ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 አሁ​ንም እነሆ በእ​ጅህ ካለ​ችው ሰን​ሰ​ለት ዛሬ ፈታ​ሁህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢ​ሎን መም​ጣት መል​ካም መስሎ ቢታ​ይህ፥ ና፤ እኔም በመ​ል​ካም አይ​ሃ​ለሁ፤ ከእኔ ጋር ወደ ባቢ​ሎን መም​ጣት መል​ካም መስሎ ባይ​ታ​ይህ ግን፥ ተቀ​መጥ፤ ተመ​ል​ከት፥ እነሆ፥ ሀገ​ሪቱ ሁሉ በፊ​ትህ ናት፤ ትሄድ ዘንድ መል​ካም መስሎ በሚ​ታ​ይ​ህና ደስ በሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህም ስፍራ ተቀ​መጥ።”

参见章节 复制




ኤርምያስ 40:4
8 交叉引用  

ምድር ሁሉ በፊትህ አይደለችምን? ከእኔ ትለይ ዘንድ እለምንሃለሁ አንተ ግራውን ብትወስድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ አንተም ቀኙን ብትወስድ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።


አቢሜሌክም፤ እነሆ ምድሬ በፊትህ ናት፤ በወደድኸው ተቀመጥ አለ።


አንተም ለባሪያዎችህ፦ ወደ እኔ አምጡት እኔም አየዋለሁ አልህ።


የግብፅ ምድር በፊትህ ናት በመልካሙ ምድር አባትህንና ወንድሞችህን አኑራቸው በጌሤም ምድር ይኑሩ ከእነርሱም ውስጥ እውቀት ያላቸውን ሰዎች ታውቅ እንደ ሆነ በእንስሶቼ ላይ አለቆች አድርጋቸው


ንጉሡም ሐማን፦ ደስ የሚያሰኝህን ነገር ታደርግባቸው ዘንድ ብሩም ሕዝቡም ለአንተ ተሰጥቶሃል አለው።


ኤርምያስም፦ ሐሰት ነው፥ ወደ ከለዳውያን መኰብለሌ አይደለም አለ፥ እርሱ ግን አልሰማውም፥ የሪያም ኤርምያስን ይዞ ወደ አለቆች አመጣው።


ጋሜል። እንዳልወጣ በዙሪያዬ ቅጥር ሠራብኝ፥ ሰንሰለቴን አከበደ።


跟着我们:

广告


广告